General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ፡- ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወር /AMN/ ጋር በትብብር ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ!!


የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ /AMN/ በትብብር ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

የሚዲያው የስራ ኃላፊዎች ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ተገኝተው ተቋማዊ ጉብኝት እና የስራ ውይይት ካደረጉ በኋላ በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ችለዋል፡፡
ኮሌጁ ከተለያዩ ሚዲዎች ጋር አብሮ ሲሰራ ቢቆይም ከሚዲያ አንፃር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሞ በጋራ ለመስራት በዚህ መልኩ ስምምነት ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያ ነው ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ #መለስ ይግዛው ናቸው። ዲን አክለውም ከበርካታ አገር አቀፍና ዓለም ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ ያለ ሲሆን አገልግሎቶቻችን ተደራሽ ለማድረግ ከእናንተና መሰል መገናኛ ብዙሃን ጋር ተባብረን መስራት ግድ ይለናል ብለዋል።

በሌላ በኩል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የገበያ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ #መሀመድ ናስር በበኩላቸው ስምምነቱ የብዙሃን ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በስሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች የቴክኒክ እና ሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችለዋል ብለዋል።

ሚዲያ አንጋፋ በሆነው በዚህ ኮሌጅ የሚከናወኑ የልማትና የፈጠራ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በዜናና በዶክመንተሪ ሽፋን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍21👎32👌1
እሁድ:- ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ለውጦችና በተፈጠሩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ወይይት ተካሄደ!!

ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ለውጦችና በተከሰቱ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከኮሌጁ አሰልጣኞች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

"የበቃ አሰልጣኝ ክህሎት የጨበጠ ወጣት ለሀገር ብልፅግና!" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውን ውይይት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ #ጥራቱ #በየነ ከማዕከል በገለፃ አቅረበዋል።

ክቡር አቶ ጥራቱ በገለፃቸው እንደ ሀገር የመጡ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የወጪ ግንኙነት ፖሊሲና ዲፕሎማሲ ስኬቶችን እንዲሁም ሀገራዊ ለውጡን የፈተኑ ውስጣዊና ወጫዊ ተግዳሮቶችን አብራርተዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ብቁ ባለሙያ በማፍራትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለሀገራዊ ብልፅግና ያላቸው ሚና ትልቅ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በገለፃው የመዲናቱ ኮሌጆች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ በጥንካሬና በክፍተት ማሳየት ተችሏል፡፡

በቀረበው ገለፃ መሰረት ከኮሌጁ አሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች እየተነሱ ሲሆን የውይይት መድረኩን በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ #አቶ #መሀመድ #ልጋኒ እና የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ #መለሰ #ይግዛው እየመሩት ይገኛሉ፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍113