ማክሰኞ፡- ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም
የአይ ሲቲ ዲፓርትመንት ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞች ስለስልጠና ክፍሉ ገለፃ ሰጠ!!
በኮሌጁ ከሚገኙ 12 ዲፓርትመንቶች አንዱ የሆነው አይ ሲ ቲ /Information Communication Technology/ ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞች በስልጠናው ዙሪያ ገለፃ ሰጠ፡፡
ዲፓርትመንቱ ለአዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች ስለ ስልጠናው ካሪኩለም፣ ስለ ተቋማዊ አሰራር ህግና መመሪያ፣ ስለስልጠና አሰጣጡ ስኬጁል፣ ስለ ኢንዱስትሪው ትብብር ስልጠና ትግበራ ሂደት፣ ስለ ግሬዲንግ የውጤት አሰጣጥ ስርዓትና መሰለ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ማብራሪያ እንደተሰጠ ሰምተናል፡፡
አይ ሲ ቲ ዲፓርትመንት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰልጣኞች ተቀብለው ከሚያስተናግዱ የስልጠና ዘርፎች አንዱ ሲሆን ዌብ ዲዛይንና ዳታ ቤዝ አድሚኒስትሬሽን እና ሃርድ ዌርና ኔትወርኪንግ ሲስተም የሚባሉ 2 የስልጠና ሙያዎችን ስልጠና የሚሰጥ የስልጠና ክፍል ነው፡፡
Credit:- መረጃው የአይሲቲ ዲፓርትመንት ነው::
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

Forwarded from admasu Ye Abiye Lij
ለመፅሃፍት አንባቢያን በሙሉ
Aladi's Collection ከ General Wingate Polytechnic College Student Council ጋር በመተባበር ለመፅሀፍ አንባቢ ወዳጆች አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል ። ከነገ ዕሮብ ህዳር 11 /2017ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን እስከ አርብ 13/2017ዓ.ም ድረስ ከ3:00 ጀምሮ ያነበባችሁት እጃችሁ ላይ ያሉትን መፅሀፎች ይዛችሁ በመምጣት በምትኩ ማንበብ የፈለጋችሁትን ማንኛውንም መፅሀፍ መቀየር እንደምትችሉ ስንገልፅ በደስታ ነው።
👉 ከእናንተ የሚጠበቀው የምትቀይሩት መፅሀፍ የፊት ገፁ ያልተቀደደ እንዲሁም በውስጡ ያሉት ገፆች ያልጎደሉ ሙሉ መሆን አለባቸው።
👉 ከ ፖለቲካ ሀይማኖት እንዲሁም የትምህርት መፅሀፎች በስተቀር ሁሉንም አይነት የመፅሀፍ ዘውጎች ያካተተ ስለሆነ በፈለጋችሁት አይነት መቀየር ትችላላችሁ ።
📍ቦታ የኮሌጁ ላይብረሪ ውስጥ ከ 3:00 ጀምሮ
©️GWPTC Student Council

አርብ፡- ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም
ኮሌጁ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወር /AMN/ ጋር በትብብር ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ /AMN/ በትብብር ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
የሚዲያው የስራ ኃላፊዎች ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ተገኝተው ተቋማዊ ጉብኝት እና የስራ ውይይት ካደረጉ በኋላ በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ችለዋል፡፡
ኮሌጁ ከተለያዩ ሚዲዎች ጋር አብሮ ሲሰራ ቢቆይም ከሚዲያ አንፃር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሞ በጋራ ለመስራት በዚህ መልኩ ስምምነት ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያ ነው ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ #መለስ ይግዛው ናቸው። ዲን አክለውም ከበርካታ አገር አቀፍና ዓለም ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ ያለ ሲሆን አገልግሎቶቻችን ተደራሽ ለማድረግ ከእናንተና መሰል መገናኛ ብዙሃን ጋር ተባብረን መስራት ግድ ይለናል ብለዋል።
በሌላ በኩል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የገበያ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ #መሀመድ ናስር በበኩላቸው ስምምነቱ የብዙሃን ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በስሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች የቴክኒክ እና ሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችለዋል ብለዋል።
ሚዲያ አንጋፋ በሆነው በዚህ ኮሌጅ የሚከናወኑ የልማትና የፈጠራ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በዜናና በዶክመንተሪ ሽፋን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

የኮሌጁ የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!
የኮሌጁ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡
በዕለቱ በዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች በኮሌጁ የተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ሪፖርቶች ቀርበው ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በሩብ ዓመቱ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ፣ ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በአግባቡ ከማሰልጠን አንፃር እና ተጓዳኝ ስራዎችን ከመከወን ረገድ ያሉ እምርታዊ ለውጦች እና የነበሩ ክፍተቶች ለውይይት ቀርበው አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በእቅድ አፈፃፀም ግምገማው ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በኮሌጁ ያሉ ጥንካሬ እና ክፍተቶችን ›አንስተው መድረኩ በቀጣይ የስራ አቅም እና ተነሳሽነት እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"