General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
በዚህ ሳምንት

አርብ፡- ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በኮሌጁ ተካሄደ!!

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር 37ኛው የምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ከትናንት ህዳር 5 ቀን 2017 ጀምሮ ለሁለት ቀናት ያህል በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተካሂዷል፡፡

በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ም/ዋና ፀሐፊ እና የስርዖተ ፆታ ዘርፍ ተጠሪ መ/ርት ደስታዬ ታደሰ፣ የአዲስ ከበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ ከበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ሀብተየስ ዲሮ፣ የከተማ ከውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊ አቶ ሰብስባቸው መንግስቴ እና ሌሎች ከመምህራን ማኅበሩ ጋር በተጓዳኝ የሚሰሩ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች በዕለቱ ተገኝተዋል፡፡

የማኅብሩ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት የትግበራ እቅድ በማህበሩ ፕሬዝዳንት መ/ር ድንቅዓለም ቶሎሳ ለምልዓተ ጉባኤው ቀርቦ እንዲገመገምና እንዲፀድቅ ተደርጓል፡፡

ከዚህ ባሻገርም የኡዲት ሪፖርትና እቅድ በመ/ርት ስመኝ ገብሬ አማካኝነት ለአባላቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ በመዲናይቱ መምህራን እንደራሲዎች ፀድቀዋል፡፡

ምክር ቤቱ በ37ኛው ጉባኤ ላይ የመምህራንን ጥቅማ ጥቅም ከማስከበር አንፃር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ጥያቄ ቀርቦላቸው መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡ ከመምህራን ጥቅማ ጥቅማ ጋር በተያያዘ በተለይ የቤት መስሪያ ቦታ ሁኔታን በተመለከተ የህብረት ስራ ምክትል ኮሚሽነሩ ሀብተየስ ዲሮ ቦታውን ለማመቻቸት ብዙ ርቀት መኬዱንና የመምህራንን አቅም ያገናዘበ ወለድ ያለው ባንክ ጋር ድርድር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ባላቸው የስራ ኃላፊነት በከተማይቱ ለሚገኙ መምህራን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደረጉ ተቋማት በማህበሩ እውቅና ተሰጥቷቸውና ባለ15 ነጥብ ያለው የአቋም መገለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ምክር ቤት 81 አባላት ያሉት ሲሆን 33ሺ ለሚደረሱ የመድናይቱ መምህራን እንደራሲዎች ሆነው እንዲያገለግሉ ከየክፍለ ከተማዎቹ የተመረጡ መምህራን ናቸው፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ለሁሉም የቀን አዲስ ገቢ ሰልጣኞች

ከ16/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የስልጠና ልብስ(ጋወንና ቱታ) ሳይለብሱ ወደ ግቢም ሆነ ወደ ስልጠና ክፍል መግባት የማይቻል መሆኑን አውቃችሁ ከላይ በተገለፀው መሰረት አዘጋጅታችሁ በመልበስ የምትመጡ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ እናሳውቃለን።

ኮሌጁ
ውድ አዲስ ገቢ ሰልጣኞች

መታወቅያ(ID) እስኪዘጋጅላቹ ድረስ የክፍያ ደረሰኛቹን ይዛቹ መምጣትን አትርሱ።

ኮሌጁ
ሰኞ፡- ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም                 

ኮሌጁ ከፑራቶስ ጋር በመተባበር ዘመናዊ ቤኬሪ ስኩል ከፈተ!!

ኮሌጁ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዳቦ፣ ኬክና ቸኮሌት ምርት ግብዓት አቅራቢ ከሆነው ፑራቶስ አ.ማ ጋር በመተባበር በዘርፉ ምርት ዝግጅት ላይ የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ። 

ከ100 ሀገራት በላይ የምርቱ አቅራቢ የሆነው የቤልጄሙ ካምፓኒ ፑራቶስ የምግብ ኢንዱስትሪ አ.ማ በአፍሪካ 2ኛ እንደ ምስራቅ አፍሪካና ኢትዮጵያ ደግሞ የመጀመሪያ የሆነውን የዳቦና ኬክ ምርት ዝግጅት ማሰልጠኛ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፈተ።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የኢፊዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሀ መሀመድ፣ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አበራ ብሩ፣ በኢትዮጵያና በጅቡቲ የቤልጅየም አምባሳደር፣ የፕራቶስ ድርጅት የአፍሪካና የኢትዮጰያ ተጠሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ለሰለጠኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር የግሉ ዘርፍ የሚኖረው ሚና የበለጠ ማደግ ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ  ፑራቶስና ጀነራል ዊንጌት አርአያነት ያለው ትልቅ ትብብር በማድረግ ያሳዩት ተግባር ሌሎችም  በትጋት እንዲከተሉት የሚያደርግ ተግባር ነው ያሉት ክብርት ወ/ሮ #ነቢሀ መሐመድ ናቸው።

በሌላ በኩል የጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ #መለሰ ይግዛው በበኩላቸው ስልጠናው በዘርፉ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት በጥራት ለኢንዱስትሪው በማቅረብ ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።

ፑራቶስ በአውሮፓዊቷ ሀገር ቤልጅየም ብራስልስ መቀመጫው ያደረገው  የዳቦ፣ ኬክና ቸኮሌት ምርት ግብዓት አቅራቢ ድርጅት ሲሆን 25 ሰልጣኞችን ይዞ እንደ አፍሪካ ሁለተኛውን ማሰልጠኛ በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››