General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ፡- ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም                 

ኮሌጁ ከፑራቶስ ጋር በመተባበር ዘመናዊ ቤኬሪ ስኩል ከፈተ!!

ኮሌጁ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዳቦ፣ ኬክና ቸኮሌት ምርት ግብዓት አቅራቢ ከሆነው ፑራቶስ አ.ማ ጋር በመተባበር በዘርፉ ምርት ዝግጅት ላይ የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ። 

ከ100 ሀገራት በላይ የምርቱ አቅራቢ የሆነው የቤልጄሙ ካምፓኒ ፑራቶስ የምግብ ኢንዱስትሪ አ.ማ በአፍሪካ 2ኛ እንደ ምስራቅ አፍሪካና ኢትዮጵያ ደግሞ የመጀመሪያ የሆነውን የዳቦና ኬክ ምርት ዝግጅት ማሰልጠኛ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፈተ።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የኢፊዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሀ መሀመድ፣ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አበራ ብሩ፣ በኢትዮጵያና በጅቡቲ የቤልጅየም አምባሳደር፣ የፕራቶስ ድርጅት የአፍሪካና የኢትዮጰያ ተጠሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ለሰለጠኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር የግሉ ዘርፍ የሚኖረው ሚና የበለጠ ማደግ ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ  ፑራቶስና ጀነራል ዊንጌት አርአያነት ያለው ትልቅ ትብብር በማድረግ ያሳዩት ተግባር ሌሎችም  በትጋት እንዲከተሉት የሚያደርግ ተግባር ነው ያሉት ክብርት ወ/ሮ #ነቢሀ መሐመድ ናቸው።

በሌላ በኩል የጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ #መለሰ ይግዛው በበኩላቸው ስልጠናው በዘርፉ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት በጥራት ለኢንዱስትሪው በማቅረብ ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።

ፑራቶስ በአውሮፓዊቷ ሀገር ቤልጅየም ብራስልስ መቀመጫው ያደረገው  የዳቦ፣ ኬክና ቸኮሌት ምርት ግብዓት አቅራቢ ድርጅት ሲሆን 25 ሰልጣኞችን ይዞ እንደ አፍሪካ ሁለተኛውን ማሰልጠኛ በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››