General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
#Happeningnow

#አሁን

ቅዳሜ፡- ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

በኮሌጁ እንደ ክላስተር ግምገማዊ ስልጠና ለአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች እየተሰጠ ነው!!

በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር  ባሉ ኮሌጆች ለሚገኙ የአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ግምገማዊ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በዚህ መድረክ ላይ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የኮልፌ ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ እና የአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪል ኮሌጅ ሰራተኞች እየተሳተፉ ሲሆን ግምገማዊ ስልጠናው ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የቀረበ ነው፡፡ 

የግምገማዊ ስልጠናው መሠረታዊ ዓላማ የሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር፣ ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና የሃገርን ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ለመፍጠር እንዲሁም ከትርክት የዘለለ በምክንያት እና በእውነት የሚያምን ፐብሊክ ሰርቪስ ለመፍጠር ነው ተብሏል፡፡

ለግምገማዊ ስልጠናው  የመወያያ ሰነድ በማቅረብ እና በቡድን ውይይት እንዲዳብር በማድረግ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር መታሰቡን ከመድረኩ ሰምተናል፡፡

ለሰራተኞቹ እየተሰጠ ባለው ግምገማዊ ስልጠና የቡድን ውይይቱ በከተማ አስተዳደሩ እና በክፍለ ከተማ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች  እየተመራ ይገኛል፡፡
  
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍92
የፌዴራል ስራና ክህሎት ሚኒስትር ባዘጋጀው የዲኖች እና አሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ለለአስተባባሪዎች በZoom ኦሬንቴሽን ተሰቷቸዋል። በመሆኑም:-
1. ሰልጠናው ከ22/12/2016 እስከ 03/13/2016 ድረስ ይካሄዳል።
2. ሀሉም ሰልጣኞች በ21/12/2016 በተመደበላቸው ሰልጠና ማዕከላት አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ እና ለስልጠናው አስፈለጊ የሆኑ ቁሶች (Laptop) በመያዝ ቀድመው መድረስ አለባቸው።
3. የስልጠና ቦታ ቀጣይ በዝርዝር የሚገለፅ ሆኖ አዲስ አበባ በሚገኙ AAU, AASTU, and KTU (Kotebe Teachers University) ይሆናል።
4. መኝታ፣ የህክምና አገልግሎት፣ ሶፍት፣ ሳሙና እና የመስተንግዶ አገልግሎት በማዕከሉ ይሸፈናል።
5. በመመሪያው መሰረት ውሎ አበል ይከፈላል።
6. የመወያያ ርዕሶች አዲዲሱ እሳቤ፣ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ፣ ልል ክህሎት፣ blended learning፣ public entrepreneurship እና pedagogy ናቸው።
ማሳሰቢያ፦
በ21/12/2016 ሁሉም ሰልጣኝ በተመደቡበት ማዕከል መገኘት እና በ22/12/2016 ጥዋት 2:30 በክብት ሚኒስትር በሚሰጠው ገለፃ ላይ መገኘት አለባችሁ!

ፍቃድ መስጠት፣ መቅረት፣ እና ስልጠናውን ማቋረጥ የተከለከሉ ናቸው!!

ዲኖች የሁሉንም አሰልጣኞች አቴዳንስ ለቢሮው በየጊዜው ማሰወቅ አለባችሁ!

መልካም ቀን!
👍22😢31🙏1
የተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ እናሳውቃለን
7👍3😢1
እሁድ፡- ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

በኮሌጁ እንደ ክላስተር ኮሌጆች ለአስተዳደር ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ግምገማዊ ስልጠና ተጠናቀቀ!!

በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር ማለትም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና በኮልፌ አንዱስትሪያል ኮሌጅ ለሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የ2 ቀን ግምገማዊ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ፡፡

ግምገማዊ ስልጠናው ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ስለ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና አዳዲስ እሳቤዎች ዘረመል እና እንደ ከተማ የ2016 በጀት ዓመት የቴክኒክ እና ኮሌጆች አፈፃፀም በሰነድ ቀርቦ የቡድን ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በሰነዱ ገለፃ እና በቡድን ውይይቱ ወቅት ዓለም አቀፋዊ ጂኦፖለቲክስ እና ሀገራዊ ጉዳዮች እንዲሁም ከተማ አቀፍ እና ተቋማዊ ጉልህ አዎንታዊ እና አሉታዊ ሁነቶች ተነስተው ማጠቃለያ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር  ተሞክሯል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍5👎1
እሁድ፡- ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

                እጅግ ያሳዝናል!!

                   ዜና እረፍት!!!!!

የኮሌጃችን የቢዝነስ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ የነበረቺው አሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ህይወቷ በድንገት አለፈ፡፡

አሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም በየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው ዕለት ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ልትለይ ችላለች፡፡

አሰልጣኝ ትደነቅ በአካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ ሙያ ተመርቃ የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ/ም ኮሌጃችንን በመቀላቀል ህይወቷ በሞት እስካለፈችበት ድረስ የቢዝነስ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ ነበረች፡፡

አሰልጣኝ ትደነቅ ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ እናትም ነበረች፡፡

የአሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ሰርዓተ ቀብር ነገ ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ላይ በቦሌ አራብሳ ቅ/ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር የሚፈፀም መሆኑን እየገለጽን ለእርሷ እረፍተ ነፍስን ለቤተሰበቿ፣ ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
😢115👍128🙏6
Forwarded from Am
Nege yemijemirew siltena bota block 58 sihon sime zirzirachu ይሄ new
👍2👌1