General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሐሙስ፡- ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሲሰለጥኑ የነበሩ ከ5ሺ በላይ ሰልጣኞች በሚሊኒየም አዳራሽ ተመረቁ!!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 14 የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሲሰለጥኑ የቆዩ 5180 ሰልጣኞች ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ  በድምቀት የተመረቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 835ዎቹ በጀነራል  ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰለጥኑ የነበሩ ናቸው።

በዕለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ  አቶ ጥራቱ በየነን  ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የኮሌጆች አመራር፣ አሰልጣኞች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የመዲናይቱ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለተመራቂዎች ‹‹የእንኳን ደስ አላችሁ!!›› መልካም ምኞታቸውን ገልጸው ‹‹የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ በተለይ በክህሎትና በስነ ምግባር የታነፀ፣ የስራ ባህልን መመሪያው ያደረገና በአስተሳሰብ የዳበረ፣ ትጉህ የሆነና ተለውጦ የሚለውጥ የሰው ኃይል ስለሚስፈልግ እጆቻችሁን ለስራ አዕምሯችሁን ለለውጥ  ማዘጋጀት አለባችሁ፤ ችግሮችን የተሻገሩ የተጉና የሰሩ ናቸው›› ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ/ም በተካሄደው የክህሎት ውድድር የተሻለ ወጤት ላስመዘገቡ እና ልዩ ልዩ ቴክኖሎጂዎችን ለፈጠሩ ሰልጣኞች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸው መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍14👏21🙏1
ሐሙስ፡- ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም                                                                                                                  
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት አመራር አካላት በኮሌጁ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ!!

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

‹‹የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ›› በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደ  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ የተጠሪ ተቋማቱ እና የኮሌጁ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የኮሌጁ ተመራቂ ሰልጣኞች በቦታው በመገኘት ግቢውን በልዩ ልዩ እጽዋት የማልበስ ስራ ላይ ተሳትፈዋል።

የዚህ ዓመት ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ መርሃ ግብር አካል በሆነው የችግኝ ተከላ ንቅናቄ መሰረት በዛሬው ዕለት በኮሌጁ ከ6000 በላይ ችግኞች መትከል የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 4ሺው /66.6 በመቶው/  ቡና፣ አቡካዶ፣ አፕልና ሌሎችን ጨምሮ የአትክልት እና ፍራፍሬ  እፅዋት ናቸው፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍184👌1
አርብ፡- ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም                                                                                                                 

‹‹የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ!!

በዛሬው ዕለት ‹‹የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል በተያዘው ዕቅድ መሰረት የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞችም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡ 

በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የጥላ ዛፎች፣ የውበት አበባዎች እና የአትክልትና ፍራፍሬ ዕጽዋቶች በኮሌጁ ቅጽረ ግቢ ተተክለዋል፡፡

በተያየዘ ዜና በትናንትና ዕለት ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም  የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደዋል፡፡

በተካሄደው  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ የተጠሪ ተቋማቱ እና የኮሌጁ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የኮሌጁ ተመራቂ ሰልጣኞች በቦታው በመገኘት ግቢውን በልዩ ልዩ እጽዋት የማልበስ ስራ ላይ ተሳትፈዋል።

         ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍5