ማክሰኞ፦ ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም
"በቀጣይም የጀመርነዉን በማጠናከር አቅም እስካለ፤ ሁኔታዎች እስከፈቀዱ የምናልፋቸዉ ጉዳዮች እና የማንፈታቸዉ ችግሮች የሉም፡፡
አቶ ጃንጥራር አባይ
ከመዲናዋ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ከተዉጣጡ አስተዳደር ሰራተኞች እና አሰልጣኝ መምህራን ጋር በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ ዉይይት ተካሄደ::
"የበቃ አሰልጣኝ፤ክህሎት የጨበጠ ወጣት፤ለሃገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሃሳብ ከሀገራዊው ለውጥ ማግሥት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሚና ዙሪያ ውይይት ተካሔዷል።
በዉይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ #ጃንጥራር #አባይ ለተሳታፊዎች እንደተናሩት መንግስት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ እንደ ሃገርም ሆነ በከተማ አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊ፤ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ በርካታ አስደማሚ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ሁሉን አካታችና አሳታፊ ስርዓት የማስፈን፤ ዘላቂና ስር-ነቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስርዓት የመዘርጋት፤ ሁሉንም ፍትሃዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰዉ ተኮር ስራዎችን የማፅናት እና የሃገርና የዜጎች ክብርና ነፃነት የማስጠበቅ ስራዎች በብዙ ሰዉ ሰራሽ እና ተፈጥራዊ ተግዳሮቶች ታልፈዉ የተመዘገቡ ስለመሆናቸዉ ከተጨባጭ ማሳያዎች ጋር አያይዘዉ አቅርበዋል፡፡
በእነዚህ የብልፅግና ጉዞ የለዉጥ ዓመታት ዉስጥ በሁለተናዊ የልማት ስራዎች ስኬቶቻችን ላይ በሙያዉ ብቁ የሆነ ወርቃማ እጆች ያሉት ትዉልድ በማፍራት እና አሻራቸዉን በማኖር ረገድ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ግንባር ቀደም ሚና እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡
በሌላ በኩልም ተሳታፊዎች ላነሷቸው የቤት፤ የጥማጥቅም እና የማትጊያ እንዲሁም ሌሎች የአሰራር እና አደረጃጀት ስራዎች አቶ ጃንጥራር ሲመልሱ ከተማ አስተዳደሩ ለእነዚህ ጥያቄዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ደረጃ በደረጃ በጥናትና በእቅድ እየፈታ መምጣቱን አስታዉሰዉ በቀጣይም ይህን በማጠናከር አቅም እስካለ፤ ሁኔታዎች እስከፈቀዱ የምናልፋቸዉ ጉዳዮች እና የማንፈታቸዉ ችግሮች የሉም ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም አሁንም ከያዝነዉ አዳጊ ፍላጎት አኳያ ጎታች የሆኑትን ጉዳዮች ለማስቀረት ሁሉም ተቋማት በአደረጃጀት በአሰራር በማዘመን እና ራስን በሙያዉ ብቁ በማድረግ በኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታዉ የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት ተቀናጅተዉ በትጋት እንዲወጡ በማለት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸዉ ከተማ አስተዳደሩ ለሙያ ተቋማት በሰጠው ትኩረት አዋጆችን፤ ደንብና መመሪያዎችን እንዲሁም የሪፎርም ስራዎችን ወደ መሬት በማዉረድ በርካታ ትርጉም ያላቸዉ ተጨባጭ ለዉጥ በሃገርና በትዉልድ ላይ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡
በልማት ስራዎች፤ በቴክኖሎጂ ሽግግር፤ ሃብት በመፍጠር እና ምርታማነት በማሳደግ እና ትዉልድን በመቅረፅ ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባና በተቋሙ አካለት የተነሱ ጥያቄዎች በጥናት ተደግፈዉ የወረዱ ደንብና መመሪያዎች እንዲሁም የተጀመዉ የሪፎርም ስራ በተገቢዉ የሚመልሰዉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ በከተማዋ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በጥራትና በፍትነት መሰራታቸዉንና ሁሉን አካታች መሆናቸዉ እንዲሁም ለቴክኒክና ሙያ ተቋማት መንግስት የሰጠዉ ትኩረት እንዳስደሰታቸዉ ገልፀዉ ዉይይቱ የበለጠ መግባባት የተፈጠረበትና ችግሮችን በጋራ እየፈቱ ዘላቂ ልማትና እድገትን ለማረጋገጥ ያስቻለ ነዉ ሲሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ረቡዕ:- ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ኮሌጁ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የትብብር ስልጠናና የስራ ትስስር ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ አካሄደ!!
ኮሌጁ ከዚህ ቀደም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የትብብር ስልጠና እና የስራ ትስስር ምን እንደሚመስል ያሳየና በቀጣይም ኢንዱስትሪ መር ስልጠናን ከማጠናከር አንፃር የተቃኘ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች፣ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ አጋር ከሆኑ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ሞደል ከሆኑ ኢንተርፕራይዞች የመጡ እንግዶች ተሳትፈዋል።
የውይይቱ ዓላማም ኢንዱስትሪው ከቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ጋር ያለውን ወሳኝ ግንኙነት ለማጠናከር፣ የትብብር ስልጠናን ውጤታማ ለማድረግ፣ የተመራቂ ሰልጣኞችን የስራ ትስስር አጠናክሮ ለመቀጠል፣ በኢንዱስትሪዎች እና በኮሌጁ ያለውን ሀብት በጋራ ለመጠቀም ያለመ ነው፡፡
በዕለቱ ኮሌጁ በአዲሱ የስልጠና እሳቤ መሰረት ወደ ስራ የገባባቸውና በዕቅድ የያዛቸው ጉዳዮች እንዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለው የስራ ትስስር በገለፃ ቀርቧል፤ በቀጣይ የስራ ግንኙነታችን ምን ይምሰል? በሚለው ዙሪያም ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም ለሰልጣኞች በተመቻቹ የትብብር ስልጠና፣ በተፈጠሩ የስራ ትስስር እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በመጡ ለውጦች ዙሪያ ለተሳታፊ ድርጅቶች የምስጋና እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ሐሙስ:- ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የኬንያ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አደረገ!!
ከኬንያ ኪሲሙ ናሽናል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመጣ ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አካሄደ፡፡
ልዑካኑ የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር እና ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት /EASTRIP/ ከሚተገበርባቸው 5ቱ የኬንያ ተቋማት መካከል በጋርመንትና ቴክስታይል ዘርፍ እንደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሌጅ ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ስፔሻሊስቶች እንዲሁም የኮሌጁ ዲኖችና የተለያየ ዘርፍ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
ልዑካኑ በቆይታቸው ተቋማዊ የልምድ ልውውጥ ውይይት፣ የወርክሾፖች ጉብኝትና አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ስራ ተከናውኗል፡፡
በመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ መሰረት በቀጣይ የሰራተኞች ልምድ ልውውጥ፣ የጋራ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እና የጥናትና ምርምር ስራ ለማከናወን ታቅዷል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››