General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ፦ ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

"በቀጣይም የጀመርነዉን  በማጠናከር አቅም እስካለ፤ ሁኔታዎች እስከፈቀዱ የምናልፋቸዉ ጉዳዮች እና የማንፈታቸዉ ችግሮች የሉም፡፡
አቶ ጃንጥራር አባይ

ከመዲናዋ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ከተዉጣጡ አስተዳደር ሰራተኞች እና አሰልጣኝ መምህራን ጋር በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ ዉይይት ተካሄደ::

"የበቃ አሰልጣኝ፤ክህሎት የጨበጠ ወጣት፤ለሃገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሃሳብ  ከሀገራዊው ለውጥ ማግሥት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሚና ዙሪያ ውይይት ተካሔዷል።

በዉይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ #ጃንጥራር #አባይ ለተሳታፊዎች እንደተናሩት መንግስት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ እንደ ሃገርም ሆነ በከተማ አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊ፤ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ በርካታ አስደማሚ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ሁሉን አካታችና አሳታፊ ስርዓት የማስፈን፤ ዘላቂና ስር-ነቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስርዓት የመዘርጋት፤ ሁሉንም ፍትሃዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰዉ ተኮር ስራዎችን የማፅናት እና የሃገርና የዜጎች ክብርና ነፃነት የማስጠበቅ ስራዎች በብዙ ሰዉ ሰራሽ እና ተፈጥራዊ ተግዳሮቶች ታልፈዉ የተመዘገቡ ስለመሆናቸዉ ከተጨባጭ ማሳያዎች ጋር አያይዘዉ አቅርበዋል፡፡

በእነዚህ የብልፅግና ጉዞ የለዉጥ ዓመታት ዉስጥ በሁለተናዊ የልማት ስራዎች ስኬቶቻችን ላይ በሙያዉ ብቁ የሆነ ወርቃማ እጆች ያሉት ትዉልድ በማፍራት እና አሻራቸዉን በማኖር ረገድ   የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ግንባር ቀደም ሚና እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡

በሌላ በኩልም ተሳታፊዎች ላነሷቸው የቤት፤ የጥማጥቅም እና የማትጊያ እንዲሁም ሌሎች የአሰራር እና አደረጃጀት ስራዎች አቶ ጃንጥራር ሲመልሱ ከተማ አስተዳደሩ ለእነዚህ ጥያቄዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ደረጃ በደረጃ በጥናትና በእቅድ እየፈታ መምጣቱን አስታዉሰዉ በቀጣይም ይህን በማጠናከር  አቅም እስካለ፤ ሁኔታዎች እስከፈቀዱ የምናልፋቸዉ ጉዳዮች እና የማንፈታቸዉ ችግሮች የሉም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም አሁንም ከያዝነዉ አዳጊ ፍላጎት አኳያ ጎታች የሆኑትን ጉዳዮች ለማስቀረት ሁሉም ተቋማት በአደረጃጀት በአሰራር በማዘመን እና ራስን በሙያዉ ብቁ በማድረግ በኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታዉ የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት ተቀናጅተዉ በትጋት እንዲወጡ በማለት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸዉ ከተማ አስተዳደሩ ለሙያ ተቋማት በሰጠው ትኩረት አዋጆችን፤ ደንብና መመሪያዎችን እንዲሁም የሪፎርም ስራዎችን ወደ መሬት በማዉረድ በርካታ ትርጉም ያላቸዉ ተጨባጭ ለዉጥ በሃገርና በትዉልድ ላይ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡

በልማት ስራዎች፤ በቴክኖሎጂ ሽግግር፤ ሃብት በመፍጠር እና ምርታማነት በማሳደግ እና ትዉልድን በመቅረፅ ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባና በተቋሙ አካለት የተነሱ ጥያቄዎች በጥናት ተደግፈዉ የወረዱ ደንብና መመሪያዎች እንዲሁም የተጀመዉ የሪፎርም ስራ በተገቢዉ የሚመልሰዉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የዉይይቱ ተሳታፊዎች  በበኩላቸዉ በከተማዋ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በጥራትና በፍትነት መሰራታቸዉንና ሁሉን አካታች መሆናቸዉ እንዲሁም ለቴክኒክና ሙያ ተቋማት መንግስት የሰጠዉ ትኩረት እንዳስደሰታቸዉ ገልፀዉ ዉይይቱ የበለጠ መግባባት የተፈጠረበትና ችግሮችን በጋራ እየፈቱ ዘላቂ ልማትና እድገትን ለማረጋገጥ ያስቻለ ነዉ ሲሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ