General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
Registration ይህንን በማየት ማከናወን ትችላላቹ
ሰኞ:- ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ∙ም

    ከ3ሺ 300 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞች በ2 ሳምንት ተመዘገቡ!!

ኮሌጁ የ2017 ዓ.ም አዳዲስ ሰልጣኞችን  ከጥቅም 15 ቀን 2017 ዓ∙ም ጀምሮ በበየነ መረብ /online/  እና በሀርድ ኮፒ ለ2 ሳምንታት የመዘገበ ሲሆን በዚህም 3365 የሚሆኑ አዳዲስ ሰልጣኞችን መዝግቧል።

ኮሌጁ አሁን ላይ በISO 9001:2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ፤ የስልጠና ጥራቱን ለማሳደግ ከግዙፍ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራቱ  እና ባለው ተቋማዊ ዘርፈ ብዙ ፋሲሊቲዎች ለስልጠና ጥራቱ ትኩረት መስጠቱ ተመራጭነቱን ይበልጥ ስላሰፋው ከፍተኛ ተመዝጋቢ ካላቸው የመዲናችን ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ ይሰለፋል።

ውድ አዳዲስ ተመዝጋቢዎች! በመሉ እምነት እኛን ተማምናችሁ መርጣችሁን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን።

የምዝገባ ቀናትን በተመከለተ ምንም እንኳን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ቢታቀድም በተለያየ ምክኒያት ምዝገባቸውን ላላጠናቀቁ አመልካቾች ተጨማሪ 4 ቀናት ዕድል ተመቻችቷል።                                                    
ስለሆነም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ባሉበት ሆነው በበየነ መረብ /online/ ወይም በኮሌጁ በአካል በመገኘት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ስናበስርዎት በታላቅ ደስታ ነው።      

የሙያ ምርጫን በተመለከተ በማታና በቅዳሜና እሁድ ለምትሰለጥኑ በፍላጎታችሁ የምትስተናገዱ ሲሆን ለቀን አመልካቾች ደግሞ ከቢዝነስ፣ ከአይሲቲ፣ ከአውቶሞቲቭ እና ከፉሽን ዲዛይን ዲፓርትመንቶች ውጪ ባሉ ሙያዎች እንደ ምርጫችሁ ትስተናገዳላችሁ።  

ስለሆነም በተቀመጡበት ቀሪ ቀናት ፈጥነው እንዲመዘገቡ እየመከርን ከዚያ በኋላ የመመዝገቢያ ሰንደቁ /ሊንኩ/ የሚዘጋ መሆኑን እንገልፃለን።

   "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ውድ ተመዝጋቢዎች

Registration ላይ

DOB(Date of Birth) ስታስገቡ በሀበሻ እንዲሁም Date of commencement(1ኛ ክፍል የገባቹበት ዓ.ም) በሀበሻ ይሁን
የቤት ቁጥር የሌላቹ New በሉት::