Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የኤፍሬም ታምሩ የቀደሙ ስራዎች ምርጫዎቼ ናቸው።
ከወጣቶቹ ዜመኞች ደግሞ ዳዊት ፅጌን እመርጣለሁ!

ድምፃዊ ደመረ ለገሰ
በባህልና በሰርግ ሙዚቃዎቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘው ድምፃዊ ደመረ ለገሰ የምንግዜም የሙዚቃ ምርጫዎቹን አስታውቋል።

የቅኝት ምርጫው በማስቀደም ሲጀመር፣ አብዛኞቹ የሰርግና የባህል ሙዚቃዎች የሚቀነቀኑበት የአንቺሆዬ ቅኝትን የምርጫው አካል አድርጎታል።
የኤፍሬም ታምሩ የቀደሙ ስራዎች ቀልቤን የሚስቡ ዘመን አይሽሬ ምርጫዎቼ ናቸው ብሏል በተለይ ሰው መሰረቱን አብልጦ ይወደዋል።

ከአሁኑ ዘመን ሙዚቃዎች የዳዊት ፅጌ ባየው የተሰኘውን ዜማ መርጧል።

ድምፃዊ ደመረ ለገሰ በደስታ ጊዜው የይሁኔን የባህል ሙዚቃዎች መርጦ ያዳምጣል።
በሀዘን ሰሜት ሲገኝ ለስላሳ የትዝታ ሙዚቃዎች ከምርጫው መዘርዝር ውስጥ ተካተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊ ሔኖክ መሐሪ

ድምፃዊ፣ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ነው፤ ሔኖክ መሐሪ።

ሙዚቃን ከልቡ የሚወደው ሔኖክ ከነጠላ ዜማዎቹ በተጨማሪ "ከመሀሪ ብራዘርስ" ጋር በመሆን ቀዳሚ አልበሙን ለአድማጭ አድርሷል። በተለየ መልኩ የተወደደለትን "አዝማች" የተሰኘ አልበም በ2013 አስደምጦናል።

ከአመታ በፊት ‹‹እውድሻለሁ›› በተሰኘው ዘፈኑ በ”ምርጥ የአር ኤንድ ቢ” እና የ”ሶል” አፍሪካዊ ድምፃዊ በመሆን፣ የ”ኦልአፍሪካ ሚዩዚክ አዋርድ” (አፍሪማ 2016) አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡በሙዚቃ ላይ ያተኮረ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አለው፡፡

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የሙያተኞች መብት እንዲከበር፣የተቸገሩ የጥበብ ሰዎች ድጋፍ እንዲያገኙ አብዝቶ የሚሰራ ሙዚቀኛ ነው፡፡

በሕይወቴ ውስጥ ለውጥን ሊያመላክቱ የሚችሉ መፅሐፍትን ፈልጌ አነባለሁ የሚለው ሔኖክ፤ ያለፉ ባለስልጣናትን የህይወት መንገድና ታሪክ የሚያወሱ ስራዎችንም ባለው ጊዜ ሁሉ ሳምንት ሶስት ቀን ከአንድ ሰዓት እስከ 1:30 የሚሆን ጊዜዬን ለንባብ እሰጣለሁ። መፅሐፍ ጥሩ ጓደኛ እንደሆነ አምናለሁ። በዚህም በእጅጉ ተጠቅሜያለሁ ባይ ነው።

ለዛሬ የሙዚቃ ባለሙያው ሔኖክ መሃሪ ሶስት ምርጥ መፅሃፍት የሚከተሉት ናቸው።

1 The purpose driven life by Rick Warren
2 ጥላሁን ገሰሰ የህይወቱ ታሪክና ምስጢር - ዘከሪያ መሀመድ
3 በአሉ ግርማ ህይወቱ እና ስራዎቹ - እንዳለ ጌታ ከበደ

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
👍2
አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ...!

በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር አስራ ሰባተኛ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት ዕረቡ መጋቢት 18 ያካሂዳል። በዕለቱም የምንወደው ወጣቱ ድምጻዊ ሳሚ ዳን የክብር እንግዳችን ሆኖ በመሀከላችን ይገኛል። እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ።

#ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
አርቲስት ዘቢባ ግርማ በአማኑኤል ሆስፒታል

#Ethiopia : አርቲስት ዘቢባ ግርማ አንድ ጊዜ አማኑኤል ሆስፒታል መጥታ ነበር ። ኮቪድ ሲገባ ህክምና ውስጥ ለምንሰራ ሰዎች ከባድ ነበር። በጊዜው አማኑኤል ሆስፒታል ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ነበሩ። የማስክ ችግር ነበር። ወረርሽኙ ወደ ሆስፒታል ከገባ ከባድ ስለሚሆን በስጋት ውስጥ ነበርን። ለአእምሮ ህክምና የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ ነበር። ያው as usual.

ነሐሴ 26/2012 ዓ.ም አርቲስት ዘቢባ ከብሬማን ፕሮዳክሽን ጋር ወደ አማኑኤል ሆስፒታል መጡ። 10,000 (አስር ሺህ) የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ድጋፍ አበረከቱ። አርቲስት ዘቢባ ሙዚቃዎቿን በማቅረብ ህሙማንን በማዝናናት ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈች።

በዛ ከባድ ጊዜ ስለአእምሮ ህመም በማሰብ ላደረጉት ድጋፍ ብሬማን ፕሮዳክሽን እና ዘቢባ ግርማን እናመሰግናለን። ዘቢባ የአጥር ወፍ አትስማሽ !!!
Via : ዶ/ር ዮናስ ላቀው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ደስታን ደጋሹ ጭንቄን ተካፋይ
ችምችም ያለው ሰፈር ናፍቆኝ ሊቀር ነወ ወይ ?"
                                        እሱባለው ይታየው
👍1
"ኤልያስ መልካ
ድንቅ የጥበብ ሰው! ዛሬም አብረን የሰራናቸው ስራዎች ስሰማ በትዝታ ተዋጥኩ፡፡
መቼም አትረሳም ኤልያስዬ…….. ነፍስ ይማር"

ኩኩ ሰብስቤ ዛሬ እንደፃፈችው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍3
ዝነኛው የሙዚቃ አቀንቃኝ ኤኮን በሀገራችን ልብስ ሽክ ብሏል!!!

#Ethiopia #Akon #Waliya_Entertainemnt
👍1
🇮🇱 💔…ድምፃዊት ሳባ የኔሁን በእሥራኤል አገር በመኪና አደጋ ሕይወቷ ማለፉ ተሰምቷል።

ከመምቷ 20 ሠዓት ቀደም ብላ በመኪና እየሄደች የሚያሳይ ቪድዮ በፌስቡክ ገጿ አጋርታ ነበር።

https://www.facebook.com/share/v/Rx927QhDjbWv5SjD/?mibextid=oFDknk

ያሳዝናል 😥😥

ሳባ ትላንት ከ 20 ሰዐታት በፊት እዚሁ ፌስቡክ ላይ Live ነበረች።

ዝንጥ ብላ ፣ ረጋ ያለ ሙዚቃ እየሰማች ፣ ደስታዋን ለሰዎች እያጋራች። በወቅቱ በጣም ትንሽ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ደስታዋን ሲካፈሉና ፍቅራቸውን ሲገልፁ ነበር።

አሁን ከ 20 ሰዐታት በኋላ ይሄው የሳባ የትላንቱ Live Video በጣም ባዘኑ የነፍስ ይማር ኮሜንቶች ተጥለቅልቋል ...

ይህቺ ናት ሕይወት 💔

ሳቂታዋ፣ ፈገግተኛዋ፣ ተጫዋቿን ሳባን ሞት ጨክኖ ወስዷታል። ሞት እንዲህ ነው እንግዲህ። ሞት ወደ ሌላ እየገሰገሰ እግረ መንገዱን ያንኳኳል ያንተን ቤት እንዲል ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም። በጣም ያሳዝናል።

ድምጻዊት ሳባ የኔሁን በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ሁሉንም አሳዝኗል:: ለቤተሰቦች: ወዳጅና አድናቂዎቿ መጽናናትን እንመኛለን

ነፍስ ይማር 💔
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የኤፍሬም አማረ "ሰይ" የተሰኘው ሙዚቃ 50 ሚሊዮን እይታ አገኘ

የትግርኛ ሙዚቃ አቀንቃኙ ኤፍሬም አማረ "ሰይ" የተሰኘ የሙዚቃ ስራው በአምስት አመት ውስጥ 50 ሚሊዮን እይታን በዩቲዩብ ማግኘት ችሏል። ይህም በትግርኛ ሙዚቃ የመጀመሪያ ያደርጓል። በኢትዮጵያ ሙዚቃ ትልቁ የዩቲዩብ እይታ ያለው የአቢ ላቀው "የኔ ሐበሻ" የተሰኘው ሙዚቃ ሲሆን በስምንት አመት ውስጥ 81 ሚሊዮን እይታን አግኝቷል።
***

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የኢትዮጵያ አይዶል የምዕራፍ 3 ውድድር ነገ ይጀምራል፡፡ ተወዳዳሪዎችን እናስተዋውቃችሁ፡፡
*****
ምህረት ረታ እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደኩት አዳማ ከተማ ሲሆን በቢዝነስ ማኔጅመንት በዲግሪ መረሃ ግብር የአራተኛ አመት ተማሪ ነኝ፡፡ ሙዚቃ የጀመርኩት በቤት ውስጥ የተለያዩ ድምፃዊያን ሙዚቃዎችን በመስማትና በማንጎራጎር ነው፡፡ ከዛም አዳማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተሠብ መምሪያ የሙዚቃ ክበብ ውስጥ በመሥራት ቆይቻለሁ፡፡ እራሴን በሙዚቃው ከፍ ለማድረግ በማሰብ በኢትዮጵያ አይዶል የምዕራፍ 3 ተወዳዳሪ ሆኜ ቀርቤያለሁ፡፡

#etvውድድሩ ነገ እሁድ ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በመዝናኛ ቻናል ቴሌቭዥን፣ ዩቱብና የፌስቡክ ገጽ ይተላለፋል፡፡ የሚወዱትን ተወዳዳሪ በ8600 SMS በዕለቱ የሚሰጣቸውን ኮድ በማስቀደም መምረጥ ይችላሉ፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
አርቲስት እናኑ ደጉ አረፈች ።
ቀብር ቀብር ዛሬ 8:00 ሰአት ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ነው
**
***
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንቁ የባህል ድምፃዊ ብሎም በሀገራችን ካሉ ቱባ የባሕል ሙዚቃዎችን ከሚጫወቱ ጥቂት ድምፃውያን መካከል አንዷ የነበረችው አርቲስት እናኑ ደጉ ሁለት ኩላሊቶቿ ስራ በማቆማቸው በህክምና ስትረዳ ቆይታ በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች ። ቀብር ዛሬ 8:00 ሰአት ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ከቤተሰቦቿ መረጃ ደርሶኛል ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
መሀሪ ብራዘርስ ባንድ አባላት የወላጅ አባታቸውን የሙዚቃ ስራዎች ዳግም ለአድማጭ ሊደርሱ ነው።

መሀሪ ብራዘርስ ባንድ አባላት የወላጅ አባታቸውን የሙዚቃ ስራዎች ዳግም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ለማድረስ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ሙዚቀኛ ሔኖክ መሀሪ ገለፀ።

የወላጅ አባታቸውን እና ሁለገብ ሙዚቀኛ የነበሩትን መሀሪ አብርሃ ስራዎችን የባንዱ መሪ ሔኖክ መሀሪ በድምፅ እንደሚጫወት ሙዚቀኛው ተናግሯል።

በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ እና ተደማጭ የነበሩ ስራዎች ተመርጠው በባንዱ እየተሰሩ መሆናቸውን የገለፀው ድምፃዊው ሙሉ የአልበም ሰራው በቅርቡ ተጠናቆ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ለማድረስ መታቀዱን ለመሰንበቻ ተናግሯል።

ከእዚህ በተጨማሪ የስምንት ወጣት ድምፃውያን ስራዎች በመሀሪ ባንድ ፕሮዲውሰርነት እየተሰሩ ይገኛሉ ሲል በተጨማሪነት አስታውቋል ።

ከተመሰረተ 17ዓመታት እያለፈው የሚገኘው መሀሪ ብራዘርስ ባንድ የተለያዩ ሙዚቀኞችን በማጀብ ትልልቅ የሙዚቃ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ ይታወቃል።

ሙዚቀኛ ሔኖክ መሀሪ ከእዚህ ቀደም በአፍሪማ መድረክ ቀርቦ ማሸነፍን ጨምሮ በኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ ተጋብዘው የሙዚቃ ስራዎችን ማቅረብ ከቻሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ድምፃውያን መካከል ይጠቀሳል።