Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የትዳር አጋር የሆነችው አርቲስት አምለሰት ሙጬ የለንደን ካፌ የምግብ ዝግጅት እና አቅርቦት አገልግሎት ድርጅት የብራንድ አምባሳደር ሆና ተሾመች፡፡

የለንደን ካፌ ሳተላይት ሬስቶራንት እና የምግብ ዝግጅት በኤንኤችዋይ አስመጪ እና ላኪ ሥር በመሆን በሬስቶራንቱ ንግድ ከ20 ዓመታት በላይ ቆይቷል ፡፡

ድርጅቱም በአጠቃለይ 6 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን 2ቱ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ውስጥ ይገኛል። 4ቱ ደግሞ ማስፋፍያ ተደርጎባቸው በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች እና ተዛማጅ ቅጂዎች የጋራ አስተዳደር ማህበር ለአባላቱ አስቸኳይ ጥሪ አስተላልፏል ።

አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ለሙዚቀኞች !

የፊታችን ሰኞ የካቲት 9 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከ 6:00 ድረስ ካዛንቺስ በሚገኘው የኢትዮጵያ አዕምሮ ንብረት ጥበቃ ባለሥልጣን መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ሥራው በቅርቡ ስለሚጀመረው የሙዚቃ ሮያሊቲ ክፍያ የአሰባሰብ ሁኔታውንና የክፍፍል ድርሻን በተመለከተ ፣ እንዲሁም የመብት ጥሰትን ለማስከበር በአዲስ መልኩ ስለተደራጀው የሕግ ድጋፍን አስመልክቶ አጠቃላይ የሥራ ሪፖርት ይቀርባል። በመሆኑም የማኅበራችን አባል የሆናችሁና ፣ ጉዳዮ በቀጥታ የሚመለከታችሁ አካላቶች በሙሉ በዕለቱ በቦታው እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ጊልዶ ካሳ የሚሰራቸው ዘፈኖች በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተመልካች አላቸው ተባለ!!

የሙዚቃ አቀናባሪው ጊልዶ ካሳ የሰራቸው የሙዚቃ ቅንብሮች በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተጠቃሚ በሆነው በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካች ካላቸው ሙዚቃዎች መካከል እንደሚመደብ ከሰዋሰው የህዝብ ግኑኝነት አዳነ አረጋ ፋስት መረጃ ተመልክቷል።

ባለፉት ጥቂት አመታት ባብዛኛ በጊልዶ ካሳ ግጥም እና ዜማ እንዲሁም ቅንብር የተሰሩ ስራዎች (የተወሰኑት ብቻ በቅንብር የተሳተፈባቸው ናቸው)

- ያሬድ ነጉ እና ሚለን (ቢራቢሮ) 31 ሚሊየን ቪው
- ሙሉአለም እና ኤፍሬም (ተሸንፊያለው) 25 ሚሊየን ቪው
- ሳንቾ (አታሳዩኛ) 20 ሚሊየን ቪው
- ማይኮ እና አስጌ (አኩኩሉ) 16 ሚሊየን ቪው
- ያሬድ ነጉ (ዞራ ዞራ) 14 ሚሊየን ቪው
- ሳንቾ (ታናሞ) 9.4 ሚሊየን ቪው
- ሚኪ ጎንደርኛ እና ሳንቾ (ሌባ) 10 ሚሊየን ቪው
- ዳጊ ዲ (በቃ) 16 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ (ላገባ ነው) 13 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ እና ሶል (ሲመሽ) 6.8 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ እና ሄኖክ (ብሶብኛል) 7 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ እና እንየው (ቢቻልሽ) 7 ሚሊየን ቪው
- ዳዊት መንግስቱ (ንገሪኝ) 6 ሚሊየን ቪው
- ፀገነት ሀ/ማርያም (ማሂላንዶ) 7.7 ሚሊየን ቪው
- ቤቲ ጂ እና አስጌ (ዞኖ ዞካ) 7.7 ሚሊየን ቪው
- ሳሚ ጎ (ኢትዮ ሼክ) 8.6 ሚሊየን ቪው
- ቡሪክ (ከኔ በላይ) 4.8 ሚሊየን ቪው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
👍1
ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ:-

ሳላውቅ ያስከፋኋችሁ ወገኖች በእግዚአብሔር ስም እና ሆዴ ውስጥ ባለችው ልጄ ስም ይቅርታ
እጠይቃችኋለሁ።

ሰው ግን አልተረዳኝም።
በርካታ የስድብ መሃት እየወረደብኝ ነው።
ሆድሽ ውስጥ ያለውን ልጅ አያሳቅፍሽ ሁሉ ያሉኝ አሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከየተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አዳዲስ ስራዎች በቅርቡ ሊታተሙ ነው።

መስከረም 17 ቀን 2015አም በድንገታዊ ህመም ህይወቱ ያለፈው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ሲሰራቸው የተበሩት የሙዚቃ ስራዎች ከተለያዩ አቀናባሪዎች እየተሰበሰቡ እንደሆነ እና በቅርቡ ለአድማጮቹ ሊደርሱ እንደሆነ ዋልያ ኢንተርቴይመንት መረጃውን ተሰምቷል።

5 የሚሆኑ የሙዚቃ አቀናባሪዎች ጋር እየተሰሩ የነበሩ 17 የሚደርሱ የሙዚቃ ስራዎች እስካሁን እንደተሰበሰቡ የጉዳዩ አስተባባሪ የሆኑት የግጥም እና የዜማ ደራሲ ዘላለም መኩሪያ ለዋልያ ኢንተርቴይመንት መረጃውን አድርሰዋል።

አብዛኞቹ ሙዚቃዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን የተወሰኑት ግን የሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ስራ እየተሰራላቸው ይገኛል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ለኢትዮጵያ ለሀገር እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ ያሉት

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ( ዘፋኞች) የሙዚቃችን Copy Rights መብታችን ይጠበቅ

ሙዚቃችን እየተሰረቀ ና እየተቆራረጠ መፖሰት ይቁም::

የሙዚቃ መብታችን ሙሉ በሙሉ ይከበር በሚል ዙሪያ

* አመርቂ
* የኢትዮጵያን የድሀውን ማህብረሰብ ኑሮ የሚቀይር ና
* ለሀገር እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ውይይት በተሳካ ሁኔታ አካሄዱ::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የኤፍሬም ታምሩ የቀደሙ ስራዎች ምርጫዎቼ ናቸው።
ከወጣቶቹ ዜመኞች ደግሞ ዳዊት ፅጌን እመርጣለሁ!

ድምፃዊ ደመረ ለገሰ
በባህልና በሰርግ ሙዚቃዎቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘው ድምፃዊ ደመረ ለገሰ የምንግዜም የሙዚቃ ምርጫዎቹን አስታውቋል።

የቅኝት ምርጫው በማስቀደም ሲጀመር፣ አብዛኞቹ የሰርግና የባህል ሙዚቃዎች የሚቀነቀኑበት የአንቺሆዬ ቅኝትን የምርጫው አካል አድርጎታል።
የኤፍሬም ታምሩ የቀደሙ ስራዎች ቀልቤን የሚስቡ ዘመን አይሽሬ ምርጫዎቼ ናቸው ብሏል በተለይ ሰው መሰረቱን አብልጦ ይወደዋል።

ከአሁኑ ዘመን ሙዚቃዎች የዳዊት ፅጌ ባየው የተሰኘውን ዜማ መርጧል።

ድምፃዊ ደመረ ለገሰ በደስታ ጊዜው የይሁኔን የባህል ሙዚቃዎች መርጦ ያዳምጣል።
በሀዘን ሰሜት ሲገኝ ለስላሳ የትዝታ ሙዚቃዎች ከምርጫው መዘርዝር ውስጥ ተካተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊ ሔኖክ መሐሪ

ድምፃዊ፣ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ነው፤ ሔኖክ መሐሪ።

ሙዚቃን ከልቡ የሚወደው ሔኖክ ከነጠላ ዜማዎቹ በተጨማሪ "ከመሀሪ ብራዘርስ" ጋር በመሆን ቀዳሚ አልበሙን ለአድማጭ አድርሷል። በተለየ መልኩ የተወደደለትን "አዝማች" የተሰኘ አልበም በ2013 አስደምጦናል።

ከአመታ በፊት ‹‹እውድሻለሁ›› በተሰኘው ዘፈኑ በ”ምርጥ የአር ኤንድ ቢ” እና የ”ሶል” አፍሪካዊ ድምፃዊ በመሆን፣ የ”ኦልአፍሪካ ሚዩዚክ አዋርድ” (አፍሪማ 2016) አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡በሙዚቃ ላይ ያተኮረ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አለው፡፡

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የሙያተኞች መብት እንዲከበር፣የተቸገሩ የጥበብ ሰዎች ድጋፍ እንዲያገኙ አብዝቶ የሚሰራ ሙዚቀኛ ነው፡፡

በሕይወቴ ውስጥ ለውጥን ሊያመላክቱ የሚችሉ መፅሐፍትን ፈልጌ አነባለሁ የሚለው ሔኖክ፤ ያለፉ ባለስልጣናትን የህይወት መንገድና ታሪክ የሚያወሱ ስራዎችንም ባለው ጊዜ ሁሉ ሳምንት ሶስት ቀን ከአንድ ሰዓት እስከ 1:30 የሚሆን ጊዜዬን ለንባብ እሰጣለሁ። መፅሐፍ ጥሩ ጓደኛ እንደሆነ አምናለሁ። በዚህም በእጅጉ ተጠቅሜያለሁ ባይ ነው።

ለዛሬ የሙዚቃ ባለሙያው ሔኖክ መሃሪ ሶስት ምርጥ መፅሃፍት የሚከተሉት ናቸው።

1 The purpose driven life by Rick Warren
2 ጥላሁን ገሰሰ የህይወቱ ታሪክና ምስጢር - ዘከሪያ መሀመድ
3 በአሉ ግርማ ህይወቱ እና ስራዎቹ - እንዳለ ጌታ ከበደ

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
👍2
አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ...!

በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር አስራ ሰባተኛ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት ዕረቡ መጋቢት 18 ያካሂዳል። በዕለቱም የምንወደው ወጣቱ ድምጻዊ ሳሚ ዳን የክብር እንግዳችን ሆኖ በመሀከላችን ይገኛል። እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ።

#ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
አርቲስት ዘቢባ ግርማ በአማኑኤል ሆስፒታል

#Ethiopia : አርቲስት ዘቢባ ግርማ አንድ ጊዜ አማኑኤል ሆስፒታል መጥታ ነበር ። ኮቪድ ሲገባ ህክምና ውስጥ ለምንሰራ ሰዎች ከባድ ነበር። በጊዜው አማኑኤል ሆስፒታል ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ነበሩ። የማስክ ችግር ነበር። ወረርሽኙ ወደ ሆስፒታል ከገባ ከባድ ስለሚሆን በስጋት ውስጥ ነበርን። ለአእምሮ ህክምና የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ ነበር። ያው as usual.

ነሐሴ 26/2012 ዓ.ም አርቲስት ዘቢባ ከብሬማን ፕሮዳክሽን ጋር ወደ አማኑኤል ሆስፒታል መጡ። 10,000 (አስር ሺህ) የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ድጋፍ አበረከቱ። አርቲስት ዘቢባ ሙዚቃዎቿን በማቅረብ ህሙማንን በማዝናናት ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈች።

በዛ ከባድ ጊዜ ስለአእምሮ ህመም በማሰብ ላደረጉት ድጋፍ ብሬማን ፕሮዳክሽን እና ዘቢባ ግርማን እናመሰግናለን። ዘቢባ የአጥር ወፍ አትስማሽ !!!
Via : ዶ/ር ዮናስ ላቀው