Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የኢትዮጵያ አይዶል አሸናፊዋ በቦንጋ አቀባበል ተደረገላት

#Ethiopia | በኢትዮጵያ አይዶል ሁለተኛ ዙር በድምፃዊያን ዘርፍ አሸናፊ የሆነችው ብዙዓየሁ ሰሎሞን በትውልድ አካባቢዋ ቦንጋ ከተማ ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016ዓ.ም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የከተማው ነዋሪ ፣ የከተማው አስተዳደር እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

የቦንጋ ከተማ አስተዳዳሪ ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ ድምፃዊት ብዙዓየሁ ከራሷ አልፋ አከባቢውን እና የአከባቢውን ማህበረሰብ በኪነ-ጥበብ ማስተዋወቅ በመቻሏ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ወደፊትም ለምታደርገው ጥረት ይሆን ዘንድ በቦንጋ ከተማ የ300 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት መስራያ የሚሆን የመሬት ስጦታ እንደተበረከተላት ተናግረዋል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው ካፋ የብዙ እውቅ ሰዎች መፍለቂያ መሆኗን በመናገር ብዙዓየሁ ሰሎሞንን ከእነዚህ አንዷ ናት ብለዋል።

አያይዘውም ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች ምስጋና አቅርበው ድምፃዊቷ ላደረገችው አስተዋጽኦ የሚያንሳት ቢሆንም በማለት የ100,000 (መቶ ሺህ ) ብር ሽልማት አበርክተውላታል።

በክብረአብ ፈለቀ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ዋግ ኽምራ የጥበብ ልጆቿን ሞሸረች!

* 1 ሚሊዮን ብር እና ለሦስቱም ድምፃዊያን 150 ካ.ሜትር መኖሪያ ቦታ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

#Ethiopia | "የዋግ ኽምራዎቹ ጥበበኞች! በባለ አገሩ አይዶል በዓለም አደባባይ ምርጥ ብቃታቸውን ያስመሰከሩት አሸናፊዎች ባለ ልዩ ተሰጥኦ ድምፃዊያን ውድድሩን በ1ኛነት ያሸነፈው አክሊሉ አስፋው፣ በ2ኛነት ያሸነፈው ብሩክ ሙሉጌታ እና ተማረ ሳሙኤል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሠቆጣ ከተማ የደመቀ አቀባበል ተደርጓላቸዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይሉ ግርማይ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የዛሬዋ ቀን ለዋግ ህዝብ ልዩ ነው። እኛ ኽምራዊያን የጥበብ ሰዎች መሆናችንን ያዬነበት ዕለት ነው ብለዋል።

ወጣቶቹ እንዲበረታቱና እዚህ እንዲደርሱ አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ አካላትን በብሔረሰብ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ጀማሪ የኪነ ጥበብ ሰዎችም እንዲበረታቱና እንደ ዛሬው ሁሉ የጥበበኞቹ ልጆች መሆናችን ከፍ ብሎ እንዲታይ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር ከወረዳዎችና ጋር በመተባበር 1ሚሊዮን ብር እና የሠቆጣ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለሦስቱም ድምፃዊያን 150 ካ.ሜትር መኖሪያ ቦታ ሽልማት በማበርከት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ስለ ቴዲ አፍሮ ቤዛ ስለተሰኘው (ህብረ ዜማ) ያልተሰሙ መረጃዎች

ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከተለያዩ የውስጥ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት

1, ሙዚቃው ከዛሬ 5 አመት በፊት የተሰራ ሲሆን አሁን ላይ ግን እንደአዲስ ትናንሽ ማስተካከያዎች እንደተደረጉለት።

2, ቤዛ (ህብረዜማ) በተሰኘው በአጠቃላይ ከ 30 የሚበልጡ ባለሙያዎች እንደተሳተፉስ ያውቃሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
እማማ አፍሪካ ~ ማሪያ ማኬባ

#Ethiopia | የነጻነት ታጋይዋና አፓርታይድን በሙዚቃ ሥራዎቿ በመታገል የምትታወቀው ማሪያ ማኬባ 92ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ሥራዋን በመዘከር እየታሰበ ነው

እማማ አፍሪካ በሚል ድንቅ ዘፈኗ የምታወቀው ማሪያ ማኬባ ከኢትዮጵያዊቷ ሜሪ አርሚዴ ጋር እንዳቀነቀነች የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።

የሩሲያ ዜና አገልግሎት የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛው ማሐመድ ኖህ ሁስማን የማሪያ ማኬባ 92ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ሥራዋን በመዘከር አክብሯል።

ማሪያ የፓርታይድን በመታገልና ለጥቁሮች ነፃነት ድምጽ በመሆን በርካታ የጥበበብ ሥራዎችን ያቀረበች የአፍሪካ የነፃነት ታጋይ ነበረች። በብዙ ኢትዮጵያውያንም እማማ አፍሪካ በሚለው መዝሙር አከል ዘፈኗ ትታወቃለች።

በ72 ዓመቷ ሕይወታ ያለፈው ማሪያ ማኬባ የእሷ ተወዳጅ ዘፈን "ፓታ ፓታ" (1967) የነጻነት ዜማውን በመያዝ በደቡብ አፍሪካ መዝሙር ሆነ።

ከእውቁ አሜሪካዊው ዘፋኝ በላፎንቴ “ Evening with Belafonte/Makeba” ጋር በትብብር በሠሩት አልበማቸው የግራሚ ሽልማት አግኝታለች።

ይህች እውቅ የአፍሪካ ፈርጥ የነፃነት ታጋይ ዛሬ 92 ዓመታ በሥራዎቿ እየተሰበ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍2
የባላገሩ ምርጥ አሸናፊዎች ልዩ የክብር አምባሳደር ሹመት ተሰጣቸው።

#Ethiopia
የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) ለአርቲስት ብሩክ ሙሉጌታ ፣ለአርቲስት አክሊሉ አስፋው ፣ለአርቲስት ተማረ ሳሙኤል የባላገሩ ውድድር በአሸናፊነት በማጠናቀቃቸው የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) ባስመዘገቡት ትልቅ ድል ከፍተኛ የሆነ ደስታ የተሰማው መሆኑን ገልፆ ለሶስቱም አርቲስቶች የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) "ልዩ የክብር አምባሳደር" አድርጎ ሾሟቸዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊ ዳኜ ዋለ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል‼️

የድምጻዊ ዳኜ ዋለ "ወንድ ልጅ ቆረጠ " የተሰኘው ሙዚቃ በዩቲዩብ በተለቀቀ 72 ሰዓታት( 3 ቀናት ) ብቻ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተመልካች አግኝቷል።

"ወንድ ልጅ ቆረጠ"ሙዚቃ ግጥምና ዜማው በራሱ በዳኜ ዋለ የተሰራ ሲሆን ባሳለፍነው አርብ የካቲት 22 2016 ዓ.ም "Dagne Walle የጨነቀለት" በተሰኘው ዩቲዩብ ቻናል መለቀቁ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ዩቲዩብ ላይ ከዚህ ቀደም በሶስት ቀናት ብቻ ከሁለት ሚሊዮን በላይ እይታ ያገኘ ሙዚቃ እንደሌለ ያነጋገራናቸው ባለሞያዎች ተናገረዋል።

ይህም የዳኜ ዋለን "ወንድ ልጅ ቆረጠ" ሙዚቃን ባለ አዲስ ሪከርድ ያደርገዋል ተብሏል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍2🎉1
ድምፃዊት ዘቢባ ግርማነብሰ ጡር ሆና በሰራችው በአዲስ ስራ ተመለሰች

#Ethiopia ከዚህ በፊት በሰራቻቸው በተለያዩ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎቿ ተወዳጅነትን ያተረፈችው ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በዃላ በድጋሜ በአዲስ ስራ ተመልሳለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ከአሁኑ ዘመን ዜመኞች የታምር ግዛው አድናቂ ነኝ"
                             
ዳዊት ይፍሩ

አንጋፋው የሙዚቃ አቀናባሪ ዳዊት ይፍሩ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የዘፈን ምርጫ የኔ ምርጥ ከተሰኘው መሰናዶ  ጋር በነበራቸው ቆይታ   የምንጊዜም  ምርጥ የሚሉዋቸውን የሙዚቃ ሥራዎችን ይፋ አድርገዋል። 

በተለያዩ ዘመናት በተቀነቀኑ  በርካታ የሙዚቃ ሥራዎች ላይ አሻራቸውን  ያሳረፉት አንጋፋው የሙዚቃ ሰው ዳዊት ይፍሩ  ከኢትዮጵያ ቅኝቶች  የቀረበ የነፍስ ዝምድና እንዳላቸው ይጠቅሳሉ፡፡

የመረበሽና እና የመከፋት ስሜት ሲሰማቸው የትዝታ ቅኝት ሙዚቃዎችን አዘውትረው እንደሚያደምጡ አልሸሸጉም። አንጋፋው አቀናባሪ  ከአራቱ ቅኝቶች ለአንቺሆዬ የተለየ ስሜትና አድናቆት እንዳላቸው  ነግረውናል።  

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የጠላሽ ይጠላ፤ የትዝታው ንጉሥ ማህሙድ አህመድ  ትዝታ ጋረደው፣ የሙሉቀን መለሰ ምነው ከረፈደ፣ ከያኔ ዘመን የመዚቃ ሥራዎች ትልቅ ቦታ የሚሰጡዋቸው ሥራዎች ስለመሆናቸው ነግረውናል።

"ከአሁኑ ዘመን ዜመኞች ግን የታምር ግዛው አድናቂ ነኝ" በማለት ይገልፃሉ፡፡ "ምነዋ የሚለው ሥራዋ ከመልዕክቱ ጀምሮ አጠቃላይ የቅንብር ሥራው ይማርከኛል፣ ከወጣቶቹ አብዝቼ ማደንቃት እሷን ነው"  በማለት ተናግረዋል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
1👍1
የዳኜ ዋለ አዲስ ሙዚቃ ላይ የሚሰሙ አንዳንድ ቃላት ትርጓሜ ፦

💥 አግምጫለሁ - አኩርፌያለሁ

💥 ቀንጃ - አጣማጅ/ አጣማሪ (በሬ)

💥 እየነደደኝ - እየተናደድሁ

💥 ቋንጃ - የእግር መታጠፊያ ፣ በጉልበት ተቃራኒ ያለ

💥 እየበሰጨኝ - እየተበሳጨሁ

💥 እየበገነኝ - ብግን ፣ እርር እያልኩ

💥 ያረመጠው- ረመጥ ስርወ-ቃሉ ሲሆን በአመድ የተሸፈነ እሳት ማለት ነው። በሌላ ቦታ "የአመድ እሳት" ተብሎም ይጠራል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
🔥2
"ካቀናበርኳቸው ሥራዎች ''ህመሜ'' የተሰኘውን የፀደንያ ገ/ማርቆስ ሙዚቃ ን አብልጬ እወደዋለሁ"

የመዚቃ አቀነባሪ አቤል ጳዉሎስ

በዘመኑ የተሠሩ ዝነኛ ዜማዎቹን ግጥማቸውን ከሙዚቃው ጋር ግሩም አድርጎ አወዳጅቷቸዋል። ከድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን እስከ ፀደንያ ገ/ማርቆስ ሙዚቃዎች ደረስ ደማቅ የቅንብር አሻራውን በብዙሃኑ የአልበም ሥራዎች ላይ አሳርፏል፡፡

ወጣቱ የሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጳውሎስ ቆየት ያሉ ሥራዎችን የማዳመጥ ልምድ እንዳለው የሚናገረው የሙዚቃ ባለሙያው አቤል ጳውሎስ፣ የቴዎድሮስ ታደሰ "የባህር ፈርጥ ነሽ" የተሰኘውን ተወዳጅ ሙዚቃ ቀዳሚው ስፍራ ላይ አስቀምጧል።

በዚህ ሥራ ላይ የሙያ አጋሩ አበጋዝ ክብረወርቅ የሙዚቃ ቅንብር ተጨምሮበት የቴዎድሮስ ታደሰ የአዘፋፈን ዘዬ ለዜማው ልዩ ውበት እንዳጎናፀፈው አጫውቶናል፡፡

በቀጣይነት የአቤል ሙሉጌታን ተገርሜ ሙዚቃ የምርጫዎቹ አካል አድርጎ በመዘርዝሩ ውስጥ አካቶታል።

አቀናባሪው በጥሩ ዝግጅት ተጠንቅቆ ለሚሠራቸው የራሱ ቅንብሮች የሚሰጠው ቦታ የተለየ ስለመሆኑ ካነሳልን በኋላ የራሱ የቅንብር ውጤት የሆነውን "ህመሜ" የተሰኘውን የፀደንያ ገ/ማርቆስ ሙዚቃ በተለየ መንገድ ከሥራዎቹ መካከል አብልጦ እንደሚወደው አስታውቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍2
ዛሬ ማርች 8 የሴቶች ቀን ነው።
ከወጣት ሴት ዘፋኞች እርሶ የማን አድናቂ ኖት?
Anonymous Poll
32%
ቬሮኒካ አዳነ
11%
ተአምር ግዛው
11%
ራሄል ጌቱ
0%
ሃና ግርማ
5%
ዘቢባ ግርማ
0%
ሜላት ቀለመወርቅ
26%
ሄዋን ገብረወልድ
16%
ሌላ (Others)