Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የባላገሩየባላገሩ ምርጥ የፍፃሜ ተወዳዳሪዎች

1, ቅዱስ ዳምጤ - BM01
2, ሄኖክ አበበ - BM02
3, ርብቃ ጌታቸው - BM03
4, እስማኤል መሃመድ - BM04
5, ብሩክ ሙሉጌታ  - BM05
6, በሱፍቃድ መዝገቡ - BM06
7, አክሊሉ አስፋው - BM07

እርሶ የማን አድናቂ ኖት?
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ኩኩ ሰብስቤ በሙያ አጋሯ ጌታቸው ካሳ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ የሀዘን መልዕክት አስተላለፈች።

"ተወዳጁ እና አንጋፋው የሙያ አጋሬ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፉ በሰማሁ ጊዜ የተሰማኝ ሀዘን ጥልቅ ነው! ጌታቸው ካሳ ዛሬ ቢያልፍም ዘመን በማይሽረው ድንቅ ስራዎቹ ሁሌም ከእኛ ጋር ይኖራል ! ለቤተሰቡና ለወዳጅ አድናቂዎቹ መፅናናትን እመኛለሁ ! ነፍስህ በሰላም እንድታርፍ ፀሎቴ ነው !"

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kuku_sebsibe
የአንጋፋው ሙዚቀኛ ጌታቸው ካሳ ህልፈት አስመልክቶ የተለያዩ አድናቂዎችና ሙዚቀኞች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፁ ይገኛሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ቴዲ አፍሮ በጌታቸው ካሳ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ የሀዘን መልዕክት አስተላለፈ።

በተወዳጁና በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ በነበረው አንጋፋውና ዝነኛው ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ልባዊ ኅዘን ለመግለፅ እወዳለሁ።
           ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ላለፉት ዐርባ ዓመታት በላይ በቆየበት የሙዚቃ ሕይወት በተጫወታቸው በርካታ እና በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ በሆኑ ሥራዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፤ ከነዚህ ቆየት ካሉ የሙዚቃ ሥራዎቹ  ውስጥም "የብዙኃን እናት፣ "ሳይሽ እሳሳለሁ" ፣ "ቀና ብዬ ሳየው " ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ።
            አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ በስፋት ከሚታወቅበት የድምፃዊነት ሙያው ባሻገር የዜማና የግጥም ደራሲ እንዲሁም የሙዚቃ መሳሪያዎች ተጫዋች ነበር።
             በዛሬው ዕለት በተሰማው ዜና ዕረፍቱም በደረሰው ኅዘን ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለሙያ አጋሮቹ እና ለመላው አድናቂዎቹ በሙሉ መፅናናትን እየተመኘሁ ፤ ፈጣሪ ነፍሱን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን ከልብ እመኛለሁ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Teddy_afro
አርባ ምንጭ ውድ ልጇን ድምጻዊ ካሳሁን እሸቱን (ካስዬን) በታላቅ ድድምቀት እየተቀበለች ነው።

ድምጻዊው በዛሬው ዕለትም አልበሙን በቱሪስት ሆቴል የሚያቀርብ ሲሆን ቅዳሜም ታላቅ ኮንሰርት በአርባ ምንጭ ያቀርባል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ቀብር

* ነገ በክብር ይሸኛል

#Ethiopia | የተወዳጁ አንጋፋ ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ስርዓተ ቀብር ነገ አርብ የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ይፈጸማል።

ቀብሩን ለማስፈጸም በሙያ ባልደረቦቹ ጊዜያዊ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር ፕሬዚደንት አቶ ዳዊት ይፍሩ በሚመራው ኮሚቴ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ዝርዝር መርሀግብሩ ይፋ ሆኗል።

ቀብሩ ከቀኑ በ 8:00 ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን የሚፈጸም ሲሆን ከቀብሩ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር የስንብት መርሀግብር ከቀኑ በ 6:00 ሰዓት ይከናወናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
💥ከ3,000,000 (ሶስት ሚልየን )በላይ እይታ💥
#ፅጋቡ_ተሻለ ( #ሻምበል)

#ሻምበል የተሰኘው የሙዚቃ ስራዉ ለእይታ በበቃ በአምስት አመት ጊዜ ዉስጥ ከሶስት ሚልየን በላይ ተመልካች ማግኘት ችሏል!!

ይህን ድንቅ ስራ በ #Waliya_Entertainemnt የዩቲዩብ ቻናል ላይ ያገኙታል። ሊንኩን በመጫን ብቻ ይመልከቱ👇
https://youtu.be/dZW7CekKLbo

#Waliya_Entertainemnt #tigregna_music #Music
👍2
🎉እንኳን ለ25 ኛ የአብሮነት ዓመት አደረሳችሁ 🔥🎉🎉

" ላፎንቴኖች " የሚለዉን መጠሪያ እና አዲስ የሙዚቃ ስታይል በመያዝ የሙዚቃዉን አለም የተቀላቀሉ
ድምፃዉያን ናቸው ... #ብርሃኑ_ተዘራ እና #ታደለ_ሮባ !
ይዘዉት ከመጡት አዲስ የሙዚቃ አቀራረብ በተጨማሪ በአለባበስና በመድረክ አቀራረብ መንገዳቸዉ የበርካቶችን ቀልብ መግዛት ችለዉ የነበሩት ላፎንቴኖች ከ90ዎች እስካሁን በፍቅር የሚሠሙ በርካታ ተወዳጅ ስራዎችን አበርክተዉልናል።

በተጨማሪም የ #ላፎንቴኖች የሙዚቃ ቡድን አድናቂዎች የድምፃዉያኑን 25 ዓመት የአብሮነት በዓል ቅዳሜ የካቲት 23 ቀን በማርዮት ሆቴል ዝግጅታቸውን ለማቅረብ ጨርሰዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
አክሊሉ አስፋው የባላገሩ ምርጥን አሸነፈ
#Ethiopia
ላለፉት አራት አመታት ሲከናወን የነበረው ባላገሩ ምርጥ የድምፃዊያን ውድድር ዛሬ የካቲት 17/2016 ዓም በሚሊኒየም አዳራሽ በአክሊሉ አስፋው አሸናፊነት ተጠናቋል።
1ኛ አክሊሉ አስፋው
2ኛ ብሩክ ሙሉጌታ
3ኛ ቅዱስ ዳምጤ እና እስማኤል መሀመድ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ሶስተኛ የወጣው እስማኤል መሐመድ ሽልማቱን ሳይቀበል ጥሎ ወረደ!
#Ethiopia
ለአራት አመታት ውድድሩን ሲያካሂድ የነበረው ባላገሩ ምርጥ ዛሬ ፍፃሜን አግኝቷል በፍፃሜ ውድድሩ ላይ 7 ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን 3ኛ ደረጃን በመያዝ ሁለት ተወዳዳሪዎች ተሸልሟል። ቅዱስ ዳምጤ ሽልማቱን ከክብር እንግዶች ሲቀበል እስማኤል መሐመድ ለዳኞች ሰላምታ ከሰጠ በኋላ ሽልማቱን ሳይቀበል ከመድረክ ጥሎ ወርዷል። በውድድሩ ውጤት ላይ ቅሬታ ኖሮት ይሆን የሚል የበርካቶች ግምት ሆኗል

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ባላገሩ ቴሌቪዥን ውድድር ነው የድምጽ ኮሌጅ ነው የከፈተው ?
**
ላገሩ ቴሌቪዥን ባላገሩ ምርጥን ለመፍጠር 4 ዓመት ገደማ ወስዶበታል ። እኔ በግሌ ያለቀ እየመሰለኝ ገና ይቀጥላል ። " ለምን እንዲህ ይሆናል ? ለምን ቶሎ ቶሎ እየጨረሰ አይጀምርም ? " የሚል ጥያቄ ነበረን ብዙዎቻችን ። የዛሬውን ውድድር ሳይ ግን የባላገሩ አሸናፊውን ለመለየት ረጅም ጊዜ መውሰዱ ሰው መፍጠርን አሳይቶናል ። አድገው የመጡትን አወዳድሮ አሸናፊውን መለየት ብቻ ሳይሆን ባላገሩ ቴሌቪዥን አፈሩን በውሀ ለውሶና አቡክቶ ፣ ጭቃውን ቅርጽ አውጥቶና አሟሽቶ ለድንቅ ውጤት ማብቃትን አሳይቶናል ።

በሌሎች ውድድሮች የምናየው ተወዳዳሪ ይዘው የመጡትን በመጠኑ ማስተካከያ መቀባትና አሸናፊውን መሸለም ነው ። ባላገሩ ምርጥ ግን አስቦበት ይሁን ሂደቱ ይፍጠረው ባላውቅም ጭቃውን ውብ ጌጥ ማድረግ ነው ። ህጻኑን ልጅ ማየት ብቻ ይበቃል ። ሂደቱ አሰልቺ ይሆናል ። ነውም ። ግን ደግሞ እንደ ሀገራችን ዩኒቨርስቲዎች በብዛት ከፍቶ እውቀትን ከማራጨት ይህ የባላገሩ ቴሌቪዥን ፀንሶ ፣ አርግዞ ፣ አምጦ የመውለድና አሳድጎ ለውጤት ማብቃት አንድ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ሊታይ ይችላል ። ዛሬ የተረዳሁት ይህንን ነው ። ተወዳዳሪዎቹ ለውድድር የቀረቡ ሳይሆን አንድ ትልቅ መድረክ ላይ በብቃትና በራስ መተማመን ስሜት ኮንርት እያቀረቡ ነው የሚመስሉት ። ይህን ለውጥ የጊዜው ርዝማኔ ራሱ ያመጣው ይመስለኛል ።

ባላገሩ ቴሌቪዥን ያወዳደራቸውን ሸለመ ከማለት በከፍተኛ ደረጃ የድምጽ ብቃት ያስተማራቸውን በማዕረግ አስመረቀ ማለት ይቀለኛል ።
በ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
👍1