Waliya Entertainment
289 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ዳዊት ፅጌ ለአድማጭ ተመልካቾቹ ላቅ ያለ ምስጋናን አቀረበ።

"እነሆ ምስጋና!
“የዘመን ቃናዎች - ፩” በሚል ስያሜ አርብ ዕለት ለአድማጭ ተመልካች ያቀረብነው የሙዚቃ ስራችን ፣ ከገመትነውም ከጠበቅነውም በላይ የሆነ ተቀባይነትን በማግኘቱ የተሰማንን ልባዊ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን! እኔ እንደ ድምፃዊ የተቀበልኩት ከሰጠሁት በእጅጉ ይልቃል፤ ያገኘሁት ምላሽ ከገመትኩት በጣም ይርቃል...

ከውጥኑ እስከፍጻሜው ከጎኔ ላልተለዩ ባለሙያዎች፣ ሲያበረታቱኝ ለነበሩት ቤተሰቦቼ፣ ሙዚቃዎቹን ዳግም እንድንሰራቸው ፈቃዳቸውን ለሰጡን የፈጠራ ስራዎቹ ባለመብቶች፣ በማስተዋወቅ ላገዙን የመገናኛ ብዙሃንና ሶሻል ሚዲያ ገፆች፣ አስተያየታቸውን ለሰጡን ባለሙያዎችና ግለሰቦች ልባዊ ምስጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ: :

በቀጣይ በአዲሱ አልበሜ እስክንገናኝ በድጋሜ ሁላችሁንም ከልቤ አመሰግናለሁ : :🙏🏾🙏🏾"

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Dawit_tsige
ተወዳጇ ድምፃዊ ኩኩ ሰብስቤ ትዝታ የተሰኘውን አልበሟን በድጋሜ ወደ ህዝቡ ልታደርስ ነው።

ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ በ1998 ዓ.ም ከኤክስፕረስ ባንድ ጋር የሠራችውን በውስጡ 4ቱንም የኢትዮጵያ ቅኝቶችን አካቶ የተዜመውን "ትዝታ" የተሰኘውን አልበም በድጋሚ አርብ ምሽት በራሷ ዩቱብ ቻናል እንዲሁም በተለያዩ የሙዚቃ ማሰራጫዎች ወደ አድናቂዎቿ በድጋሚ ልታደርስ እንደሆነ ገልፃለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Kuku_sebsibe
👍1
GOLDEN VISA 🇦🇪

#Ethiopia | አርቲስት ንዋይ ደበበ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የ10 ዓመት የክብር መኖሪያ ፈቃድ (a UAE residency visa for ten years ) ተቀብሏል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #neway_debebe
ፀጋዬ ደቦጭን በሕይወት እያለ ብናግዘው ይሻላል

#Ethiopia : ኤፍሬም ታምሩ ፣ ጸጋዬ እሸቱ ፣ ጸሃይ ዩሃንስ ፣ ኩኩ ሰብስቤ ፣ ይሁኔ በላይ .... የትዝታዎቻችን ሰሪ የግጥም ደራሲው ጸጋዬ ደቦጭ ስራዎቹን ከሰጣቸው መካከል እነዚህ አርቲስቶች በአንጻራዊነት ጥሩ የሚባል ህይወት ነው ያላቸው። በሚገባ ለሰው መትረፍ የሚያስችል አቅም አላቸው ።

አንጋፋው የግጥምና ዜማ ቀማሪ ጸጋዬ ደቦጭ እንዲህ አደባባይ ሳይወጣ ገመናውን ሽፍን አድርገው : ሞራሉንና ክብሩን ጠብቀው ሊያግዙት ይችሉ ነበር ።

አልሰሙም ነበር ብለን እንያዘው። አሁን ጸጋዬ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቀርቦ አካውንቱን ገልጾ ያለበትን ሁኔታ ተናግሯል። ከዚህም በኋላ ጸጋዬ የማንንም እጅ እንዳያይ ማድረግ ይችላሉ።

አያድርግበትና ደስ በማይል ሁኔታ ቆይቶ ህይወቱ ስታልፍ የቀብር አስፈጻሚ ብሔራዊ ኮሚቴ ውስጥ ዘጥ ዘጥ ማለታቸው አይቀርም። ከዚያ በፊት ግን እንደወዳጅ እንደሙያ አጋር ብዙ ነገር ማድረግ ይችላሉ ። በኤርሚያስ በጋሻው ገሰሰ

ፀጋዬ ደቦጭ አንበሴ ፦

#በ0911135937 ደውሉ ።
#በ1000202569963 ( CBE ) አግዙት ።

#SHARE

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
በትናንትናው እለት የ ሮፍናን ማስተርክላስ (የሙዚቃ ስልጠና) ተካሄደ።

ታዋቂው የሙዚቃ አርቲስት ሮፍናን ከዋልያ ቢራ ጋር በመተባበር ለ 3 ቀን የተጀመረው ስልጠና በኤልያና ሞል ከ150 ሰው በላይ አሰልጣኞች በተገኙበት ተካሄደ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ቬሮኒካ አዳነ ለአድናቂዎቿ ምክር አስተላለፈች።

"እንደኔ ስድብ የቻለ እዚ ምድር ላይ ያለ አይመስለኝም። አንድ ነገር ላሲዛቹ ብዙ ጥፋት ላጠፋ እችላለዉ ሀጥያተኛም ነኝ። አዎ ነኝ። ሰዉ አይደለዉ? አንዳንዴም አንዳንዴ ላማ እችላለዉ( ሰዉ ያረገዉን እንጂ ፈጥሬ አላወራም) ወሬ አልወድም በስራ አምናለዉ ብዙ ሰዎችን እየሰራዉ ፀጥ አስብላቸዋለዉ። በቀሌ ስኬት ነዉ። ባለኝ ነገር አልኮራም መልክም ፣ ዝናም ፣ እድሜም ይሄዳል። ለዛ በጊዜዬ ፈጣሪን እያመሰገንኩ መጠቀም እንዳለብኝ አዉቃለዉ። በጣም የሮጥኩ ከመሰላቹ ( ጊዜ ) ስለሚያሳስበኝ ነዉ።

እሺ ባጠቃላይ ድብን ያልኩ ሀጥያተኛ ነኝ ግን ከኔ አፍ ስድብ አታገኙም ከኔ ስርቆት አታገኙም ያለፋሁበት ቦታ ላይ ቆሜ አታገኙኝም።

ከፈጣሪዬ በስተቀር ማንንም የማልፈራ ላመንኩበት ፖዳይ አንገቴን የምሰጥ የሆኑ ሰዎች ተሰብስበዉ ባወጡት ጎጂ ህግ ሰዉ ይስቅብኛል ብዬ ማልመራ ቤተሰብ ሀይማኖት የማስቀድም አለማወቄ ጉዳይ የማይሰጠኝ ሰዉ የሚንቅ አዉ የሚያመኝ ሰዉ ነኝ።

ወዷ ዋናዉ ሀሳብ ስመጣ ስድብ ከኔ አፍ አታገኙም, አዳነ ይሙት

እና እኔን ለምትወዱኝ ቤተሰቦቼ ለምትሰሙኝ በእድሜ የምበልጣቹ ( 28 ) ዓመቴ ነዉ

ምንም አይነት ሁኔታ ዉስጥ ብትገቡ ፣ ምንም አይነት ሁኔታ ዉስጥ አፍ አታበላሹ። ምንም አይነት ስድብ  ትንሽም ብትሆን ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ንግግር አትናገሩ ትንሽ የምትመስል ስድብም ቢሆን አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ስለሚለካ።

በጣም እወዳችዋለዉ"

በ ቬሮኒካ አዳነ

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
https://www.t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #veronica_adane
የማስተዋል እያዩ አልበም (እንዚራ) አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተደረገ።

የካቲት 1 የሚለቀቀውን "እንዚራ" የተሰኘውን የማስተዋል እያዩን አልበም በተመለከተ ዛሬ አልበሙ ላይ ከተሳተፉ የሞያ ባለቤቶቼ ጋር በማሪዮት ሆቴል ለሚዲያ ባለሞያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን ለዓመታት የተደከመበት እና በርካታ እውቅ የሀገራችን የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት አልበም እንደሆነ እንዲሁም አልበሙ 14 ዘፈኖችን በውስጡ እንደያዘም በመግለጫው ተጠቅሷል።

"እንዚራ" አልበም አርብ የካቲት 1 ቀን በኤላ ቲቪ አማካኝነት እና በሁሉም የኦን ላይን ማሰራጫዎች ወደ ህዝቡ የሚደርስም ይሆናል።

በአልበሙ ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎች

በግጥም:-
ናትናኤል ግርማቸው (5)
ጥላሁን ሰማው (2)
ፍሬዘር አበበወርቅ (4)
አቡዲ (3)
ብሬ ብራይት(1)

በዜማ:-
አበበ ብረሀኔ (1)
ማስተዋል እያዩ (5)
አቡዲ (2)
እሱባለው ይታየው የሺ (1)
ቢኒአምር አህመድ (1)
አምባቸዉ እሸቱ (2)
ምህረትአብ ደስታ (1)
ታመነ መኮንን (1)

በቅንብር:-
ሚካኤል ሀይሉ/ጃኖ (6)
ታምሩ አማረ (5)
ብሩክ አፍወርቅ (3)

ማስተሪንግ:-
ሰለሞን ሀይለማርያም

ፕሮዲዩሰር :-
ማስተዋል እያዩ

ረዳት ፕሮዲዩሰር :-
ደሜ ሉላ

ማኔጅመንት እና ክሬቲቭ ዳይሬክተር:-
ነፃአለም አብዲ

ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር:-
ኤላ ቲቪ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ እና ዋልያ ቢራ ለ18 ወራት የሚቆይ የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ።

በዚህ ጊዜ ውስጥም 10 የሙዚቃ ኮንሰርቶችን በክልል ከተሞች ለመስራት ታቅዷል።
በቅርቡ "ዘጠኝ" በሚል ርዕስ ሁለት የሙዚቃ አልበሞችን በአንድ ቀን ለአድማጮች እንደሚያቀርብ የገለፀው ሮፍናን ለዚህ አልበሙ ከዋልያ ቢራ ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

ሮፍናን እና ዋልያ ቢራ ከዚህ በፊት "ስድስት" በተሰኘው አልበሙ ላይ የነበራቸው ጥምረት በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገልጿል።
በዚህም በክልል ከተሞች 6 ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት ለብዙዎች የስራ ዕድል መፍጠሩ ነው የተገለጸው።

ሙዚቀኛው ከዋልያ ጋር በመተባበር በዚህ ሳምንት በሮፍናን ማስተር ክላስ ለ1መቶ50 ጀማሪ ሙዚቀኞች ልምዱን ማካፈሉም ተገልጿል።

ዋልያ ቢራ ይህንን የማስተር ክላስ ወደ ክልል ከተሞች ለመውሰድ ዝግጅት መጀመሩንም አስታውቋል።

የሁለቱ የአጋርነት ስምምነት የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ከመስራት ባሻገር የአገርን ባህል ማጎልበት ፣ የራስ ጥበብን ማውጣት፣ የስራ ዕድል መፍጠር እና መልካም አመለካከትን መቅረፅ አላማው እንደሆነ ተገልጿል።

ሙዚቀኛው "ሀራምቤ" እና "ኖር" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን በጋራ የያዘ "ዘጠኝ" የተሰኘ አልበም ለአድማጮች ለማቅረብ ዝግጅት መጨረሱን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

"ሀራምቤ" በህብረት ውስጥ ያለ የራስ ቀለምን አጉልቶ ማሳየት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፤ "ኖር" የሚለው አልበም ደግሞ ለአዲስ ሀሳብ፣ ለአዲስ አልበም፣ ለአዲስ ፍልስፍና እና ለአዲስ ነገር ኖር ማለትን የሚያሳይ ነው ሲል ሙዚቀኛው ገልጿል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
👤 Mastewal Eyayu | ማስተዋል እያዩ
🎵 Enzira | እንዚራ
━━━━━━━━━━━━━━
➠ RELEASED: 2024
➠ GENRE: #Ethiopian
➠ TYPE: #Album
➠ TRACKS: 14
➠ FORMATS: #Mp3
➠ CHANNEL: @Waliyaentmt
━━━━━━━━━━━━
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Mastewal_eyayu #Album #Ethio_albums #Waliya_Entertainemnt
👍1