Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ድምፃዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ መሰንቆና ዋሽንት ተጫዋች፣ ክራርና በገና ደርዳሪ፣ የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መምህር የሆኑት አለማየሁ ፋንታ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከማስተማርም በዘለለ ትምህርት ቤቱ ሲከፈት የባህል ሙዚቃ ትምህርትን ለተማሪዎች እንዲሆን አድርገው ካሪኩለም በማዘጋጀት ከፍተኛ ሚናን ተጫውተዋል።

ውልደትና እድገታቸው በአሁኑ የዋግምራ ዞን ሰቆጣ አካባቢ ሲሆን፣ በልጅነታቸው በድቁና ማዕረግ ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡

ሙዚቃን የጀመሩት በሀገር ፍቅር ቴአትር ሲሆን ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ዓመታት ያህል በክፍሉ ሰርተዋል፡፡ የኢትዮጵያን የባህል ሙዚቃ በመወከል በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያ በርካታ ሀገራትንም ተዟዙረዋል።

በእንግሊዝ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያና ሌሎችም በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የባህል ሙዚቃ አምባሳደርነት ማዕረግን ያገኙ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ በ1968 ዓ.ም ከዳካር የኔግሮ አርትስ ፌስቲቫል ሽልማት ከዩኔስኮ ለሙዚቃ ስራዎቻቸው እውቅና ፣ ከኮርያ ስፕሪንግ ፍሬንድ ሺፕ አርት ፌስቲቫል ዲፕሎማና የክብር ሜዳሊያና መሰል በርካታ ሽልማቶችንም አግኝተዋል::

አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈፀምም ታውቋል።

Follow us on
Telegram - https://t.me/waliyaent
አርቲስት አንዷለም ጎሳ ከዕጮኛው ሞት ጋር በተያያዘ ለጥያቄ በፖሊስ መጠራቱ ተነገረ

በኦሮምኛ ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አንዷለም ጎሳ ከዕጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ጋር በተያያዝ በፖሊስ ጥያቄ እንደተደረገለት ተሰምቷል።

በማኅበራዊ ሚደያ በርካታ ተከታዮቿ ያሏት ቀነኒ አዱኛ ማክሰኞ ጥዋት መሞቷን ተከትሎ በርካቶች ሐዘናቸውን ከመግለፅ ባሻገር የሞቷ ምክንያት እንዲጣራ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ፖሊስ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

የአርቲስት አንዷለም ማኔጀር ሌሊሳ ኢንድሪስ የአስከሬን ምርመራው በሚኒሊክ ሆስፒታል እንደሚደረግ እና የሟች የቀብር ሥነ-ሥርዓት ረቡዕ እንደሚከናወን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግሯል።

ቀነኒ ከሚኖሩበት ሕንጻ መውደቋን እና "ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ መሞቷን" ሌሊሳ ተናግሮ አንዷለም እና ቤተሰቦቹ ወድቃ እንዳገኟት አስታውቀዋል።

ሌሊሳ ንጋት 11 ሰዓት ሰዓት ስልክ ተደውሎ "ቀነኒ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደገባች" እንደተናገረው ገልጾ፣ "እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከአምስተኛ ፎቅ ወድቃ ነው የሞተችው። ሁኔታውን ለማጣራት ምርመራ ተጀምሯል" ብለዋል።

ሌሊሳ እንደሚለው አርቲስት አንዱአለም በአሁኑ ወቅት ለምርመራ በፖሊስ ጣቢያ ነው የሚገኘው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #andualem_gossa
ምንድነው የተፈጠረው?

የድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ማናጀር የሆነው ለሊሳ እንድሪስ የተፈጠረውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ከሰጠው ምላሽ በፋስት መረጃ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።
ንጋት 11:00 ሰዓት ስልክ ተደውሎ «ቀነኒ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች ቶሎ ድረስ» እንደተባለ የሚናገረው ለሊሳ እሱ ሩቅ በመሆኑ በሰዓቱ መድረስ እንዳልቻለ ይናገራል።

ቦሌ አራብሳ ከአመት በላይ በጋራ ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ከአምስተኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ምን እንደተፈጠረ ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በቅርብ በሚገኘው ያኔት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ጠዋት ፖሊስ መጥቶ ሬሳዋን ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ከወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት እስኪወጣ አስክሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ሱሉልታ መሄዱ ነው የተገለፀው።

ድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከሆስፒታል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዛ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምናውቀው እስካሁን አለመታሰሩን ነው ምርመራ እናድርግ ብሎ ነው ፖሊስ የወሰደው ሲል ማናጀሩ ይናገራል።

ለሁለት አመታት በፍቅር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ጋብቻቸውን ለመፈፀም እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቃለሁ ሲል ለሊሳ ይናገራል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #andualem_gossa
ተፈፀመ

የሞዴል ቀነኒ አዱኛ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ፣ ቤተሰቦቿ እና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት ተፈጽሟል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ሩብ ሚሊየን (250,000) ብር

#Ethiopia | ተወዳጁ ድምፃዊ ሸዋንዳኝ ሃይሉ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 2 ህንፃዎች ግንባታ ማጠናቀቂያ ይሆን ዘንድ የሩብ ሚሊየን (250,000) ብር ድጋፍ አደረገ ።

ያስጀመረን ያስፈፅመናል!!!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #shewanday_hailu
" የልጄን እውነት አፈላልጉኝ ! ... የፍትህ አካላት ተከታትለው የልጄን ሀቋን ያውጣልኝ ፤ ደሟን ያወጣልኝ " - አባት አቶ አዱኛ ዋቆ

ትናንት በቅድስት ሥላሴ የቀብር ስነስርዓት ከተፈጸመ በኋላ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ ለቀስተኞች ፊት ባስተላለፉት መልእክታቸው የልጃቸውን ፍትህ በእጅጉ እንደሚሹ አሳውቀዋል፡፡

" ሁላችሁንም የምጠይቃችሁ፤ አርቲስቶቻችንም ለናንተ የማስተላልፈው መልእክት የልጄን እውነት አፈላልጉኝ፡፡ እንደ ሃጫሉ ሞትም ተድበስብሶ እዳይቀርብኝ " ብለዋል

" እኔ ለማስተማር ነበር ከእቅፌ ያወጧሃት እንጂ እንዲህ እንድትቀጠፍብኝ አልነበረም፡፡ ሌላ የምለውም የለም " ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አባት አቶ አዱኛ ዋቆ " እኔ ቀነኒን የማውቃት እጅግ ታታሪ፣ ስራን የምትፈጥር፣ ደግሞም ሥራ አክባሪ ናት፡፡ እንዲህ እርኩስ መንፈስ ይዟት እራሷን ታጠፋለች የሚለውን ውሸት ነው የምለው፡፡ እሷ ሲቸግርህ ተበድራ እንኳ የምትሰጥ እንጂ ከሷ ይህ አይጠበቅም " በማለት በልጃቸው ኅልፈት መሪር ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

" እኔ አሁንም ቢሆን የፍትህ አካላት ተከታትለው፤ ሀቋን ያውጣልኝ ነው ፤ ደሟን ያወጣልኝ ነው ሌላ ምንም የምለው የለኝም " ብለዋል፡፡

ለጋዋ ወጣት ቀነኒ አዱኛ ዛሬ ከአባቷ አቶ አዱኛ ዋቆ እና እናቷ አስቴር መኮንን መጋቢት 07 ቀን 1991 ዓ.ም. ነው የተወለደችው።

የፊታችን ቅዳሜም 26ኛ ዓመት ልደቷን ለማክበር ስትዘጋጅም ነበር

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በቀነኒ ሞት ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት ቀረበ

አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡን ጠበቃው ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጿል።

ፖሊስ እስካሁን አሻራ ማንሳቱን፣ አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመላክ፣ የአስከሬን ምርመራ ማድረጉን ገልጾ የሰው ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

"አሁን ፎቶግራፎችን ከመዝገቡ ጋር ለማያያዝ፣ የሰዎች ምስክርነት ለመስጠት እና የአስከሬን ምርመራው እስኪመጣ ድረስ ለማጣራት 14 ቀናት ያስፈልገኛል ብሏል።

የአንዱአለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይሰጥ ብሎ ቢጠይቅም ፍርድ ቤት የአስክሬን ምርመራ እንስኪደርስ በማለት 13 ቀናት ድምፃዊው በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ወስኗል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #andualm_gossa
በአንዱአለም ጎሳ ክስ ላይ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ፖሊስ ተጋጩ!

ተጠርጣሪው ድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ከተያዘ በኋላ በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኦሮሚያ ፖሊስና ሚሊሻ መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። ዛሬ ሦስት የኦሮሚያ ፖሊስ መኪኖች ከሚሊሻዎች ጋር አንዱአለምን ወደሚገኝበት ማቆያ ጣቢያ በመሄድ ጉዳዩን ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ እንዲተላለፍላቸው ጠየቁ። የፌደራል ፖሊስና ከንቲባ ጽ/ቤት ያረጋገጡዋቸውን ደብዳቤዎች ይዘው መጡ።

ነገር ግን የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጠርጣሪውንም ሆነ የጉዳዩን ፋይል ለማስተላለፍ ፈቃደኛ አልሆነም። ይህም ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኖ የተኩስ ድምፅም ተሰምቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #andualem_gossa
የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ያለውን አድናቆት ገለፀ።

በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው የአድናቆት መልዕክት "ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ሆይ ፈጣሪ ካንተ ጋር ነውና ሀገር ወዳድ ልበቀና በሳል እና ጥበበኛ መሪ እንደሆንክ ገና አለም ይመሰክርልሀል እየመሰከርልህም ነው የሀገሬ የኢትዮጵያ መሪ በመሆንህ እኮራብሃለሁ" ብሏል።

በመጨረሻም እውነት ካንተ ጋር ነው ሲል ገልጿል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kamuzu_kassa
ምን ማለት እንደሚቻል ግራ ይገባል።

ኪዳኔ ሃይሌ ፀባየ ሸጋ ቀልድና ጨዋታ ኣዋቂ፣በኩናማ ዜማና ግጥም ድርሰት ከፊት የሚቀመጥ፣ በተጨማሪም ድምፃዊና ሳክስፎኒስት ከዚህ ኣለም በሞት መለየቱን ስሰማ ሀዘኔ ከፍተኛ ነው።ኤልያስ መልካ በቅንብር የተሸለመበትን የኩናምኛ ዘፈን ድርሰትን ግጥሙን የፃፈው፣ዜማውን የደረሰውና በድምፅ ያቀነቀነው ኪዳኔ ነበር።በሰላም እረፍ!

ዋልያ ኢንተርቴይመንት ለቤተሰቦቹና ለጓደኞቹ መፅናናትን ይመኛል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Elias_melka #kidane