Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
አንድ ሚልየን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ብር

በለንደን ከተማ በተካሄደው የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ላይ ከታዳሚዎች እና ከአስተባባሪዎች የተገኘውን 8,300 ፓውንድ (1,457,000.00 ብር) አዘጋጆቹ ገቢ አድርገዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro
ቬሮኒካ አዳነ ለተከታዮቿ ያስተላለፈችው መልእክት

"አንዳንዴ ሰዎች ራሳቸውን ወደም ሰዎችን የሚያዩበት ልክ ድንቅ ይለኛል የኔ ተከታዬች ወይም ቤተሰቦቼ ከአጀማመረ ጀምሮ ስለሚያቁኝ ለነሱ ምንም ማብራራት አይጠበቅብኝም ! በጣም ደግሞ አወዳችዋለሁ።

ይህ መልዕከት ለተጠባባቂ ተከታዮቼ ማለትም ቬሮኒካ ላይ የሆነ ነገር እስክትይዙ ብቻ ለምትወዱኝ የሆነ እንቅፋት ቢያጋጥመኝ እኔን እህቴ ሳይሆን ይድፋሽ ለሚሉ ጊዜያዊ ሰዎች አኔማለት ማን እንደሆኑኩ ልንገራችሁ

ሁሉም ሰው እኩል ነው ብዬ የማምን በአስተሳሰብ ወደም በአመለካከት ወይም በሀይማኖት ቢቃረኑኝ እኔም የኔን ይዤ እነሱም የነሱን የማከብር ሰው ስለሆኑኩ ሰውነት የሚገባኝ ሴት ነኝ።

ለኔ class ማለት ብራንድ መልበስ ፣ ካለው ጋር መዋል ፣ act ማድረግ ይሄ አለኝ ፣ እንዲ ነኝ ማለት ሳይሆን

ከሁሉም ማሀበረሰብ ጋር ተመሳስሎ ፣ ተከባብሮ፧ ተዋዶ ፣ ያለውን አካፍሎ መኖር ነው!

ስለዚህ በዚ ጕዳደ ላይ ምን አልባት የመጀመሪያዬም የመጨረሻዬም መልዕከት ከሆነ ሳልደርስባችሁ ፣ ሳልነካችሁ ፣ ሳልመጣባችሁ ስለኔ ምንም ለምትሉ ሰዎች ማንንም አልሰማም መስሚያዬ ጥጥ ነው አላችዋለሁ።" - ቬሮኒካ አዳነ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Veronica_adane
"የፒያሳ ቆሌዎች" የተሰኘ የቱርጉም መጽሐፍ ተመረቀ

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ሙዚቃ ጥናት የታወቁት ጃፓናዊው አንትሮፖሎጂስት ፕሮፌሰር ኢትሱሺ ካዋሴ የጻፉት "የፒያሳ ቆሌዎች" የተሰኘው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ትናንት ማምሻውን በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ተመርቋል።

ፕሮፌሰር ኢትሱሺ ካዋሴ ላለፉት 25 ዓመታት የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሲያጠኑ የቆዩ ሲሆን፣ መጽሐፉም በጥናታቸው ወቅት የገጠማቸውን ማህበራዊ ገጠመኞች ላይ የተመሠረተ እንደሆነ በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።

"የፒያሳ ቆሌዎች" የተሰኘው መጽሐፍ በፕሮፌሰር ኢትሱሺ ካዋሴ በጃፓንኛ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን፣ "Mischief of the Gods" በሚል ርዕስ በጄፍሪ ጆንሰን ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመ ሲሆን፣ በአማርኛ ደግሞ ያዕቆብ ብርሃኑ እና ዓለማየሁ ታዬ ተርጉመውቷል።

በምረቃው መርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን ከመጽሐፉ ላይ ንባብ፣ አጠር ያለ ዳሰሳና ከተርጓሚዎቹ ጋር ጥያቄና መልስ ሌሎች የአዝማሪ ጨዋታዎች ተከናውነዋል።

መጽሐፉ በኢትዮጵያ ሙዚቃ እና ባህል ላይ ያተኮረ ሲሆን፣
17 የተለያዩ ታሪኮች ፣ 149 ገጾች ያሉት ሲሆን በ350 የኢትዮጵያ ብር ለገቢያ ቀርቧል።

"የፒያሳ ቆሌዎች" ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ጥናት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
የሳምንቱ ብዙ የታዩ ሙዚቃዎች ዝርዝር

📈 ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም

1️⃣የድምፃዊ አስቻለዉ ፈጠነ - አሞራዉ ካሞራ
በሳምንቱ ውስጥ የጨመረው የተመልካች ብዛት: 565,266

2️⃣ የድምፃዊ አማኑኤል የማነ - ንስክላ
በሳምንቱ ውስጥ የጨመረው የተመልካች ብዛት: 498,323

3️⃣ የድምፃዊ ያሬድ ነጉ - አለምድም
በሳምንቱ ውስጥ የጨመረው የተመልካች ብዛት: 444,491

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
በቀደምት ጀግኖች አያቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት እንዲሁም በታላቁ ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችን ዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብልህ አመራር እና አስተባባሪነት ለተቀዳጀነው አንፀባራቂው የ፻፳ ወ፱ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው::

ይህ በታሪክ ተመዝግቦ በየአመቱ የምንዘክረው አድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል የኢትዮጵያን ነፃነት ያስከበረ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ የቅኝ ግዛት ቀንበር ተጭኗቸው ሲሰቃዩ ለነበሩ አፍሪካዊያን ወንድም እና እህቶቻችን እንዲሁም በመላው አለም በጭቆና ውስጥ የነበሩትን ጥቁር ህዝቦች ቀና ብለው እንዲሄዱ እና ነፃ እንዲወጡ በወቅቱ ታላቅ መነቃቃትን የፈጠረ ገናና የጥቁር ህዝቦች ድል ነው።

የዘንድሮውን የ፻፳ ወ፱ ኛው የአድዋ ድል በአል ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ቀላል ለማይባሉ አመታት አንድነቷን አስጠብቃ ወደ ፊት እንዳትራመድ ሰቅዞ የያዛትን ተከታታይ የብሔር ፖለቲካ አዙሪት እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ያስከፈለንን እና እያስከፈለን ያለውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ካለንበት ውስብስብ እና እጅግ ኋላቀር የዘር ፖለቲካ ለመውጣት ከመቼውም ጊዜ በላቀ አንድነታችንን አስተባብረን የህልውናችን መሰረት የሆነችው እናት ሀገራችንን ለማዳን በንቃት መቆም ይጠበቅብናል።

<<ምንሊክ ጥቁር ሰው!>>

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro #adwa
ተወዳጁ የባህል ሙዚቀኛ አስቻለው ፈጠነ በኦንላይን ገበያ መጣ!!

ታሪክና ባህል በተሸከሙ ሙዚቃቹ ስምና በልዩ ልዩ ታሪካዊ ፎቶዎች የታተሙ ደረጃቸውን የጠበቁ ቲሸርቶችን በኦንላይን ገበያ አቀረበ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #aschalewu_fetene
እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም የድል በዓል እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

ዓድዋ
👉የነፃነት_አርማ
👉የጥቁር_ሕዝቦች_ድል
👉የአንድነት_ተምሳሌት
👉አድዋ ኢትዮጵያዊነት።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #adwa
አንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ በልዩ ስጦታ በወዳጅ ዘመዶቹ ተሸለመ

#Ethiopia | የትዝታው ንጉስ ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ለሀገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ላደረገው አስተዋፅዖ ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት ከወዳጅ እና ቤተሰቦቹ ከልብ የመነጨ አድናቆትን አግኝቷል።

በፕሮግራሙ ላይ ለታዋቂው ድምፃዊ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ለበርካታ አመታት ላበረከቱት ትሩፋት ያላቸውን ጥልቅ አክብሮት እና ምስጋና የሚገልጽ የወርቅ ሃብል ተበርክቶለታል።

ድምፃዊዉ ዘመን እና ጊዜ የማይሽራቸውን ስራዎችን በመስራትየሚታወቀው ማህሙድ አህመድ የሀገሪቱን የባህልና የሙዚቃ ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ በኩል ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #mehamu_ahmed
ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አዲስ ነገር ይዛ እየመጣች ትገኛለች…

ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ የበኩር አልበምዋን "መጠርያዬ" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ይዛ መምጣትዋን አይዘነጋም፡፡

ሁል -ጊዜ አዳዲስ ጉዳዮችን ይዛ ብቅ የምትለው ወጣቷ ድምፃዊት ከሰሞኑ የሚለቀቁ ቪድዮች እንደ ሚኖሩም ገልፃለች፡፡ በራስዋ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ እንዲህ ስትል ለአድናቂዎቿ የሙዚቃ አድማጮች በሙሉ አድርሳለች፡፡

…"አንድ አንዴ ፈጣሪን ማመስገኛ ቃል አጣለሁ ተመስገን…በጣም የማከብረው ድርጅት ጋር የBrand Ambassader የመሆን ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ነገ የምለቀውን ቪድዮ ሙሉ በሙሉ ገዝተውታል፡፡ የኔ ደስታ የሚያስደስታችሁ ቤተሰቦቼ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
ለማንኛውም የነገው አዲስ ነገር በMarch 8 በveronica Adane Youtube Channel የሚለቀው በውስጡ ያለው 12 ቪድዮ ነው ብዙ ደክመውበታል እንደ ምትወዱት አልጠራጠርም" ስትል ገልፃለች፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #veronica_adane
ድምጻዊ አስቻለው በእሥራኤል 🇮🇱

በተለየ የአዚያዚያም ስልቱ ፤
በሀገረሰባዊ የአከዋወን ብቃቱ፤ የምናውቀው ‼️
በ "እናትዋ ጎንደር " የሙዚቃ አፍቃሪውን ልብ ከፍቶ የገባው፤
በ "አስቻለ" አልበሙ ብቃቱን አስመስክሮ "አሞራው ካሞራ" ን የመረቀን ፤
ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ‼️

የመጀመሪያ ኮንሰርቱን በእሥራኤል 🇮🇱 ሊያቀርብ ነው‼️