Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
አብርሃም በላይነህ - ሻላዬ ቀን በቀን አዲስ አልበም ሊለቀቅ ነዉ!

በሀገራችን የሙዚቃ እንደስትሪ ውስጥ ጉልህ ድርሻን ካበረከቱ ወጣት ድምፃዊያን መካከል እና የተለያዩ ነጠላ ሙዚቃ ሥራዎችን በመስራት እና በትወናው ዘርፍ በመሳተፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደማጭና ታዋቂ ለመሆን የቻለውን ተወዳጁ ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ/ሸላዬ/ ሙሉ የሙዚቃ አልበሙን ወደ ሕዝብ ለማድረስ መሰናዶውን እንደጨረሰና ከአስራ ሦስት ዓመታት በፊት ለአድማጭ ባደረሰው “ሻላዬ” ነጠላ ዜማው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው አብርሃም በላይነህ እነሆ ዛሬ ደግሞ ዘጠኝ አመት የተደከመበትን እና 12 ዜማዎችን የያዘዉን “ቀን በቀን” የተሰኘ አልበም ለሙዚቃ አፍቃሪያን እንካችሁ ሊለን ነው፡፡

አብርሃም በላይነህ በሥራዎቹ የአገራችንን ባህልና አዳዲስ ነገሮችን ለማስተዋወቅ የሚጥር ሲሆን በ 2013 ዓ.ም በለቀቀው “ዳርም የለው” ነጠላ ዜማ ከተወዳጁ የኦሮምኛ ድምፃዊ አሊ ቢራ ጋር በመሆን ታሪክን ተጋርቷል ጡሁም ዜማንም አስደምጦናል፡፡ ድምጻዊው በአዲስ አልበሙም ከኤልያስ መልካ ጋር በመሆን የሰራቸው አምስት ሙዚቃዎችና ከሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ጋር በተጣመረበቻው ሰባት ዜማዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በላቁ ሙዚቃዊ ሀሳቦች ፍቅርን፣ተስፋንና አገራዊ አንድነትን እሴቶችን እና ምክርን አንፀባርቋል፡፡ “ቀን በቀን” አልበም 9 ዓመታትን የዝግጅት ጊዜን የጠየቀ ሲሆን ወንደወሰን ይሁብ፣ መሰለ ጌታሁን፣ናትናኤል ግርማቸው፣ እና አንተነህ ወራሽን የመሳሰሉ የአገራችን የሙዚቃ ሰዎች ተሳትፎ አድርገውበታል፡፡

አልበሙ የፊታችን ታኅሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአብርሃም በላይነህ የዩቱዩብ ቻናልና በመላው ዓለም በሚገኙ የሙዚቃ መተገበሪያዎች ለአድማጭ ይደርሳል፡፡

@waliyaentmt
@waliyaentmt
የድምጻዊ ሶና ታከለ ወረ ቦሌ ነጠላ ዜማ አዲሱ የልዑል ሲሳይ አልቻልኩምን አስከትሎ በተከታታይ ለአምስት ሳምንታት በአንደኝነት

በሳምንቱ ዉስጥ በዩቲዩብ በብዛት የታዩ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ የሳምንቱ ምርጥ መቶ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሰንጠረዥ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"አሪፍ ነገር ለመስራት አቅም የሌለኝ አታስመስሉብኝ” ፀደኒያ ገ/ማርቆስ

ተወዳጇ ድምፃዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ በድጋሚ ዘፍናው ከሰሞኑ ለአድማጭ ያቀረበችው "እወድሀለው" ሙዚቃ ከተሰራ ሀያዓመት እንዳስቆጠረ ተናግራለች::

በወቅቱ በአህጉር ደረጃ የተዘጋጀውን የኮራ የሙዚቃ ሽልማትን ያስገኘው ሙዚቃ እና "ቢሰጠኝ" ሙሉ አልበም «በጥንቃቄ የተሰራ ነው »ብላለች::

ፀደኒያ ይህንን ለስለስ ብሎ ተሰርቶ የነበረውን እወድሀለው ሙዚቃ ከሰሞኑ በሬጌ ስልት ተጫውታ ለአድማጭ አቅርባለች::

ይህን ተከትሎ የሙዚቃ አፍቃሪያን «ስራው ዳግም መሰራቱ ተገቢ አይደለም» እና «ተሻሽሎ ተሰርቷል» የሚል አስተያየት ሰጥተዋል::

ስለጉዳዩ ድምፃዊቷን በመድረኮች ላይ ሙዚቃውን በተለያዩ ስልቶች ስጫወተው ቆይቻለሁ አዲስ የሆነው አሁን ለሰማው ነው ስራዎቼን በቀጣይ የምለቅበትን የራሴን የዩቲዮብ ገፅ ለማጠናከር በሚል ሰራነው ከዛም ከ20ዓመቱ ጋር ተገጣጠመ» ብላለች::

የሙዚቃው መሰራትን በተመለከተ የሚሰጡ አሰተያየቶችን በሁለት መልኩ መከታተል ይገባል የምትለው ፀደኒያ አዲሱን አጨዋወት የወደዱት ደስ የተሰኙትን ያህል በተቃራኒው የቀድሞ ለምን ተነካ በሚል ከመውደድ የሚመነጩ መልዕክቶች እንደሆኑ እና ለዛም ክብር እንዳላት ተናግራለች::

« አዲስ ነገር ለመስራት ግን አቅም የሌለኝ አታስመስሉብኝ » ስትል ገልፃለች::

አዲስ አልበሟ እየተጠናቀቀ እንደሆነ የገለፀችው ፀደኒያ ገ/ማርቆስ እስከዛው መዳረሻ ሌሎች ነጠላ ዜማዎቿን እንደምታስደምጥም አሳውቃለች::

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
«ለበርካቶች መነሻ የሆነው ዲጄ ኪንን ተረባርበን እናሳክመው» ዲጂ ዊሽ(የቅርብ ጓደኛ)

የመጀመሪያ ከነበሩ ዲጄዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ዲጄ ኪን አሁን ላይ የጤና እክል አጋጥሞት ድጋፍ የሚፈልግበት ጊዜ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል::

የዲጄ ኪን የቅርብ ጓደኛ ዲጄ ዊሽ እንደሰማው ኪን ያለበት የስኳር ህመም ተባብሶ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ስራ እንዲያቆሙ አድርጎታል። ይህን ተከትሎ ኪን አሁን ላይ የዲያሊስስ ህክምና እየተደረገለት ቢገኝም በዘላቂነት ካለበት የጤና ችግር እንዲወጣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት ሀኪሞች መናገራቸው ተገልፇል::

ዲጂ ዊሽ እንደሚለው ህክምናውን ለማስፈፀም በ90ዎቹ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ሙዚቃን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ በማስተዋወቅ እና የተለያዩ ስራዎችን በመስራት አይረሴ ጊዜን ለሰጠው ዲጂ ኪን ለህክምና ወጪው እንዲታገዝ ጥሪ ቀርቧል::

የኪን ህክምናን በተመለከተ የጎ ፈንድሚ አካውንት የተከፈተ ሲሆን የኪን ወንድምም ኩላሊት ለመለገስ ቃል ገብቶ አስፈላጊውን የህክምና ሂደት መጀመሩንም ዲጄ ዊሽ ገልጿል።

ኪን ሙዚቃቸውን ያስተዋወቀላቸው የጥበብ ሰዎች አብሯቸው የሰራቸው ተቋማትን ጨምሮ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ለዲጂ ኪን ህክምና ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ ተጠይቋል::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #djkin
አይዶልን በቲክቶክ ለቲክቶከሮች!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በቅርብ ቀን የአይዶል ውድድርን በቲክቶክ ይዞ ሊመጣ መሆኑን አስታወቀ።

የምሥራቹ የተሰማው ትናንትና በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው። ኢቢሲ አይዶልን በቲክቶክ የሚጀምረው የቲክቶከሮችን ጥረት ለመደገፍ መሆኑን የኢቲቪ መዝናኛ ቻናል ኃላፊ ተዓምርአየሁ ወንድማገኝ ገልፀዋል።
በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ከወዲሁ ዝግጅታቸውን እንዲጀምሩም ኃላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህን የተመለከተውን መረጃ ለመከታተል እና በውድድሩም ለመሳተፍ ያመቻቸው ዘንድ የኢቢሲ ዶትስትሪም ገጾችን በመከተል ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን የኢቢሲ ዲጂታል ቤተሰብ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢቢሲ ቀጣዩን የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ከአሁኑ ከፍ ባለ ደረጃ ይዞ እንደሚመለስም አቶ ተዓምርአየሁ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ቃል ገብተዋል።
የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ በርካታ ታዳሚዎች እና ተወዳዳሪዎች በተገኙበት ባማረ እና በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ ከኢቢሲ ጋር በአጋርነት ለሰሩ አዘጋጆችም ምስጋና አቅርበዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #tiktokcreativeaward
እዬቤል ፀጋዬ የፋና ላምሮት ምዕራፍ 18 የፍጻሜ ውድድር አሸናፊ ሆነ።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 18ኛው የፋና ላምሮት የድምጻውያን ውድድር ትናንት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በፍጻሜ ውድድሩም እዮቤል ፀጋዬ፣ ግሩም ነብዩ፣ ማእረግ ሃይሉ እና እየሩሳሌም አሰፋ የተዘጋጁበትን ሥራ በማቅረብ ብርቱ ፉክክር አድርገዋል፡፡

በዚህም እዮቤል ፀጋዬ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #fanalamrot
የተወዳጁ ድምፃዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ) የመጀመርያ አልበም ጥር 16 ይለቀቃል ተባለ፡፡

ተወዳጁ ድምፃዊ አልበሙን በቅርብ ቀን ማለትም ጥር 16/2017 ለመልቀቅ ዝግጅቱን መጨረሱን ገልጿል፡፡ ድምፃዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ)በፋና ላምሮት ውድድር በአምስተኛው ምዕራፍ አሸናፊ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ የሆነ ከዛም የተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጭ አድርሷል በተለይ “ደሴ ላይ ቤቷ” በህዝብ ዘንድ በይበልጥ ይታወቃል፡፡ አሁን ደሞ የበኩር አልበሙን “አልጣሽ” የተሰኘ ስያሜ ያለው ሲሆን ወደ 11 የሙዚቃ ክሮች ተካተዋል፡፡

በዚህ አልበም ተወዳጅ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን

በዜማ
- አበበ ብርሀኔ   6 ዜማ
- አቤል ሙልጌታ  4 ዜማ እና ግጥም
- አህመድ ተሾመ ( ዲንቢ )  1 ዜማ

በግጥም 
- ይልማ ገብረአብ  4  ስራ
- ናትናኤል ግርማቸው  1  ስራ
- መሰለ ጌታሁን  1  ስራ
- ተስፋ ብርሀን  1  ስራ

በቅንብር
- አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ  8  ሙዚቃ
- አቤል ጳውሎስ  3  ሙዚቃ

እንዲሁም ሁሉንም  11 ሙዚቃዎች ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ አድርጏቸዋል::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Ahmed_manjus
persistence ሊደነቅ ይገባል !
.
ይህን የጋሽ መሐሙድን ቃለምልልስ ከሕይወትህ ላይ ጊዜ ቀንሰህ ብትመለከተው አንድ ሰው ከየት ተነስቶ የት መድረስ እንደሚችል ብቻ አይደለም የምትመለከተው ።
ትልቅነት ያላጠፋው: ዝና ያላበላሸው ትህትና አንደበት አውጥቶ ሲናገር ትሰማለህ ። በእርሱ ዘፈን ዝነኛ ከሆነው መስፍን ከሚባለው ዘፋኝ ጋር የነበረው ወግ : ብዙአየሁ ደምሴና ሙሉቀን መለሰን ያገናኘበትን ሁኔታ ሲያወጋ የምትመለከተው ትልቅ ሰውነትን ነው ። ክብርን መጠበቅን ነው ። ስለ የአበሻ የሙዚቃ ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ ሲናገር የምትመለከተው ይህንን ነው ።
.
ከሁሉም በላይ ከ21 ዓመቱ አንስቶ ላለፉት 63 ዓመታት በተወዳጅነት የዘለቀ ሙያዊ መሰጠት ትመለከታለህ ። አንድ የምታውቀውና የምትወደው ነገር ላይ በብቃት መቆየት (persistence ) መደነቅ አለበት ።
.
#መሐሙድአህመድ
የትልቅነት ስም !
በኤርሚያስ በጋሻው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #mehammudahmed
ዛሬ የተወዳጁ ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ልደት ነው።

መልካም ልደት !
ከኤፍሬም ስራዎች የቱን የበለጠ ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #EphremTamiru #happybirthday
የኢትዮጲያ ምርጥ 30 ድምፃዊያን።

1, ቴዲ አፍሮ
2, ልጅ ሚካኤል
3, ሮፍናን
4, አብዱ ኪያር
5, ዳዊት ፅጌ
6, አደም መሃመድ
7, መሳይ ተፈራ
8, በረከት ተስፋዬ
9, ሙላቱ አስታጥቄ
10, ጎሳዬ ተስፋዬ
11, ወንዱ ማክ
12, ሃና ተክሌ
13, እንዳለ ወ/ጊዬርጊስ
14, አስቴር አወቀ
15, መስከረም ጌቱ
16, አቢ ላቀዉ
17, ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ
18, ራሄማ ሺፋ
19, ዩሃና ሳህሌ
20, ዳዊት ጌታቸው
21, ያሬድ ነጉ
22, አገኘሁ ይደግ
23, ቃሬ ዘ ማስክ
24, አብነት አጎናፍር
25, ሳያት ደምሴ
26, ዘሪቱ ከበደ
27, ቴዲ ዬ
28, ሙሉአለም ታከለ
29, እሱባለዉ ይታየዉ
30, ሳሚ ዳን

- ደረጃዉን ያወጣዉ Viberate.com የተሰኘዉ አለም አቀፍ ድረገፅ ሲሆን መነሻዉንም አርቲስቶቹ ባላቸዉ ተከታዬች እና በተሰሙበት ልክ ነዉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #singers