Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
አይዶልን በቲክቶክ ለቲክቶከሮች!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በቅርብ ቀን የአይዶል ውድድርን በቲክቶክ ይዞ ሊመጣ መሆኑን አስታወቀ።

የምሥራቹ የተሰማው ትናንትና በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው። ኢቢሲ አይዶልን በቲክቶክ የሚጀምረው የቲክቶከሮችን ጥረት ለመደገፍ መሆኑን የኢቲቪ መዝናኛ ቻናል ኃላፊ ተዓምርአየሁ ወንድማገኝ ገልፀዋል።
በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ከወዲሁ ዝግጅታቸውን እንዲጀምሩም ኃላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህን የተመለከተውን መረጃ ለመከታተል እና በውድድሩም ለመሳተፍ ያመቻቸው ዘንድ የኢቢሲ ዶትስትሪም ገጾችን በመከተል ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን የኢቢሲ ዲጂታል ቤተሰብ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢቢሲ ቀጣዩን የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ከአሁኑ ከፍ ባለ ደረጃ ይዞ እንደሚመለስም አቶ ተዓምርአየሁ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ቃል ገብተዋል።
የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ በርካታ ታዳሚዎች እና ተወዳዳሪዎች በተገኙበት ባማረ እና በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ ከኢቢሲ ጋር በአጋርነት ለሰሩ አዘጋጆችም ምስጋና አቅርበዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #tiktokcreativeaward