Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የሮፍናን የፍርድ ቤት ክስ ተዘጋ።

ድምፃዊ ሮፍናን ኑሪ አቶ ሃይለስላሴ አስረስ ተከሳሽ ሆነው የቀረቡበት የፍርድ ቤት ክርክር በስምምነት ተቋጨ።

ክሱ የተጀመረው ጥቅምት 15 ቀን 2016 አ.ም ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ስምምነት መሠረት ሊግባቡ ባለመቻላቸው ሲሆን ሮፍናን የአቶ ሃ/ስላሴ ቤትን በ165 ሚሊዮን ብር ለመግዛት እንደተስማማ የውል ስምምነታቸው የሚገልፅ ሲሆን ቅድመ ክፍያም ወደ 6 ሚሊዮን ብር ለ ሃ/ስላሴ ማስገባቱንም ገልጿል።

ሮፍናን በክሱ ላይም ሲያስረዳ ቅድሚያ ክፍያውን ካስገባሁ በኃላ ሻጭ የባንክ ብድር ውል አልጠብቅም በማለት የተስማማንበትን የቤት ውል ትተው ለሌላ ሰው በ170 ሚሊዮን ብር ሸጠውታል በሚል ሲሆን የወሰዱትንም ቅድምያ ክፍያ ሊመልሱልኝ ባለመቻላቸው ስለዚህም የወሰዱትን ገንዘብ ሊመልሱ ከሚገባቸው ቀን ጀምሮ በሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ሊከፍሉኝ ይገባል ሲል በመጀመሪያ ፍርድ ቤት በቦሌ ምድብ 2ተኛ ልዩ ልዩ የፍትሀብሄር ችሎት ተከሰው ነበር።

ይሁን እንጂ ተከሳሽና ከሳሽ ህዳር 22 ቀን 2017 አ.ም ለፍርድ ቤቱ የእርቅ ስምምነት በማቅረባቸው እርቃቸውም ፀድቆ መዝገቡ እንዲዘጋላቸው በጠየቁት ጥያቄ መሰረት ክሱ የተዘጋ ሲሆን ስምምነቱም ሮፍናን ቅድሚያ የከፈለው 6 ሚሊየን ብር እንዲሁም ተጨማሪ ያወጣው 100 ሺ ብር ባጠቃላይ ስድስት ሚሊየን አንድ መቶ ሺ ብር እንዲመለስለት በማድረግ ክሱ እንዲዘጋ ሆኗል።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Rophnan
👉አርቲስት ሀመልማል አባተ የመካኒሳ ታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት የክብር አምባሳደር ሆና ተመረጠች

"ትልቅ አደራና ኃላፊነት ነው የሠጣችሁኝ፤ከ37 ዓመታት በላይ የኖርኩበትን ሠፈር በተለይ በእግር ኳስ ሀገር የሚያስጠሩ ተጫዋቾችን ለማሳደግ እየደከመ ካለው ፕሮጀክት ጋር በሙሉ አቅሜ ለመስራት ቃል እገባለሁ" - አርቲስት ሀመልማል አባተ

"ትንሽ ከተማ ትልልቅ ህልሞች"የሚል መሪ ቃል ያነገበውና ከተመሠረተ ሶስተኛ አመቱን ያስቆጠረው የመካኒሳ ታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት ተወዳጅዋንና ታዋቂዋን ድምፃዊ ሀመልማል አባተን የፕሮጀክቱ የክብር አምባሳደር አድርጎ መምረጡን ይፋ አድርጓል።

የመካኒሳ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት በተወዳጅ ዘፈኖቿ በምታስተላልፋቸው መልዕክቶች፣በበጎ ስራዎቿና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያላትንና በአካባቢው በአርአያነት የምትጠቀሠውን ተወዳጅዋን አርቲስት ሀመልማል አባተን በሙሉ ድምፅ በመምረጥ ትናንት(ዓርብ)መካኒሳ አቦ ማዞሪያ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ፅ/ቤት በተከናወነ ስነ-ስርዓት የክብር አምባሳደርነት ሠርተፊኬት እንደተሠጣት ታውቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #hamelmal_abate
ቀላቲ ቢውቲ ድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነን የብራንድ አምባሳደር ሆነች

#Ethiopia | ተወዳጅዋ ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ ለቀላቲ ቢዉቲ ለቀጣይ ሁለት ዓመት የክብር አምባሳደር በመሆን ለቴሌቪዥን ፤ ለቢል ቦርድ እና ለማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት የብራንድ አምባሳደር በመሆን ተፈራርማለች።

በ2008 ዓ.ም በአቶ ሮቤል ቀላቴ የተመሠረተው ዋና መቀመጫውም በአዲስ አበባ ያደረገው ቀላቲ ቢዉቲ የተለያዩ የውበት መጠበቂያ ምርቶችን በኦን ላይን በማዘዝ ለደንበኞች ባሉበት ስፍራ ለማድረስ የተመሠረተ ተቋም ነው።

ተወዳጅዋ ድምፃዊ ቬሮኒካ ቀላቲ ቢውቲ ጋር ለመስራት እድሉን በማግኘቷ የተሰማትን ክብር በፊርማ መርሐግብሩ ላይ ገልጻለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #veronica_adane
"ፍሬንች ሞንታና እና ልጅ ሚካኤል " በአንድ መድረክ አዲስ አበባ ላይ

ከሞሮኮ የዘር ሐረግ የተወለደው አለም አቀፍ ተወዳጅነት ያለው አፍሪካ አሜሪካዊው የሂፓፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ፍሬንች ሞንታና አገራችን ኢትዮጵያ መቶ ከኛው አመለ ሸጋው ልጃችን ልጅ ሚካኤል ጋ ስራቸውን ሊያቀርቡ እንደሆን የቅርብ ምንጮቻችን ነግረውናል::

ፍሬንች ሞንታና በሙዚቃዎቹ ውስጥ አፍሪካን በማስተዋወቅና ት/ቤቶችና ሆስፒታሎችን በማስገንባት ትልቅ አስተዋጾ እንደሚያደርግ ብዙ ስራዎቹ ላይ ይታያል በተለይ unforgettable የተባለው በዮጋንዳ ሀገር የተሰራ ሙዚቃው በዓለም በጣም ታዋቂና ዝነኛ ሙዚቃው ነው በእይታም ደረጃ ከአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊየን በላይ ነው::

በነገራችን ላይ ልጅ ማይክም ከዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች ጋ ሀገር ውስጥና ከሐገር ውጪ አንድ መድረክ ላይ በመስራት ብዙ ልምድ አለው:: ይህም የፍሬንች ሞንታናና የሱ የመድረክ ጥምረት አሪፍ ይሆናል ተብሎ ይገመታል::

ዝግጅቱም በሸራተንና በይሳቃል ኢንተርቴመንት አዘጋጅነት ይደረጋል ተብሏል::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #frenchmontanna #lijmic
እንኳን ደስ ያላችሁ !!

#Ethiopia: እንኳን ደስ ያላችሁ - ድምፃዊት ቤቲ ጂ እና ወንድማችን ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #bettyg
አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፃፉት ደብዳቤ ከስራቸው ተሰናበቱ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ሆነው ላለፉት ስድስት አመታት ያገለገሉትን አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀትን ከስራቸው ማሰናበታቸውን ከአንዳንድ ምንጮች ዋልያ ኢንተርቴይመንት ማረጋገጥ ችሏል።

የሙዚቃ ሊቅ እና መምህር የነበሩት አቶ ሰርፀ ከስራቸው የተነሱት በከንቲባዋ ህዳር 23/2017 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ሲሆን ምክንያቱ ግን በደብዳቤ ላይ አልተገለፀም።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Sertsefresbhat
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎤Our Previous Waliya Stage was an unforgettable night!

Leul Sisay captivated the audience with his inspiring journey, while talented musicians delivered breathtaking performances that left everyone in awe. The event was filled with delightful surprises and humorous moments, creating a vibrant and joyous atmosphere. 🎶

Organized by Waliya Entertainment in collaboration with Convex ICT and the British Council, this event truly celebrated the essence of live music and artistic expression.

#WaliyaStage #LeulSisay #LiveMusic #UnforgettableNight #WaliyaEntertainment #convexict #britishcouncil
ዛሬ የተወዳጁ ድምፃዊ እሱባለው ይታየው ልደት ነው ።

መልካም ልደት !
ለመሆኑ ከእሱባለው ስራዎች አንድ ሙዚቃ ምረጡ ብትባሉ የቱን የበለጠ ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Esubalewu #happybirthday
ድምጻዊ አብርሃም በላይነህ ለዘጠኝ አመት የደከመበትን እና 12 ዜማዎችን የያዘዉን “ቀን በቀን” የተሰኘ አልበም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ።

“ቀን በቀን” አልበም የዚህ ትውልድ ቀለም ናቸው የሚባሉት፣ ኤልያስ መልካ እና ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) በላቀ ደረጃ በቅንብር እንደተጣመሩበት የተገለጸ ሲሆን የፊታችን ታኅሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በድምፃዊው የዩቱዩብ ቻናል ለአድማጭ ይደርሳል፡፡

ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ (አብርሃም ሻላዬ) ለዓመታት በተከታታይ በለቀቀቻው ነጠላ ዜማዎቹ በሙዚቃ አፍቃሪያን ከፍ ያለ ዝናን ከመታርፉም በላይ “እቴ ዓባይ” በተሰኘ ሥራውም በ“All African music award” አሸናፊ ለመሆን ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም “ሻላዬ” እና “ባባ ፋዮ” የተሠኙት ሙዚቃዎቹም በየወጡበት ዘመን በተካሔዱ አገራዊ የሙዚቃ ውድድሮች ከምርጦቹ ተርታ ለመመደብ ችለዋል፡፡ አብርሃም በላይነህ በሥራዎቹ የአገራችንን ባህልና አዳዲስ ነገሮችን ለማስተዋወቅ የሚጥር ሲሆን በ 2013 ዓ.ም በለቀቀው “ዳርም የለው” ነጠላ ዜማ ከተወዳጁ የኦሮምኛ ድምፃዊ አሊ ቢራ ጋር በመሆን ታሪክን ተጋርቷል፣ ጡሁም ዜማንም አስደምጦናል፡፡

ድምጻዊው በአዲስ አልበሙም ከኤልያስ መልካ ጋር በመሆን የሰራቸው አምስት ሙዚቃዎችና ከሚካኤል ኃይሉ ጋር በተጣመረበቻው ሰባት ዜማዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በላቁ ሙዚቃዊ ሀሳቦች ፍቅርን፣ ተስፋንና አገራዊ አንድነትን እሴቶችን እና ምክርን አንፀባርቋል፡፡

“ቀን በቀን” አልበም 9 ዓመታትን የዝግጅት ጊዜን የጠየቀ ሲሆን ወንደወሰን ይሁብ፣ መሰለ ጌታሁን፣ናትናኤል ግርማቸው፣ እና አንተነህ ወራሽን የመሳሰሉ የአገራችን የሙዚቃ ሰዎች ተሳትፎ አድርገውበታል፡፡

@waliyaentmt
@waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ምኒልክ ወስናቸው ካረፈ ዛሬ ድፍን 16 ዓመት ሆነው!!

ታህሣሥ 15 2001 ዓ.ም በርካታ አይረሴ የሙዚቃ ስራዎችን የሰሩት አንጋፋው ድምጻዊ ምኒልክ ወስናቸው ያረፈበት ቀን ነው።ይህም ማለት ከዛሬ 16 ዓመታት በፊት መሆኑ ነው።

ምኒልክ ወስናቸው በርካታ ምርጥ ምርጥ ሙዚቃዎችን የሰሩ ሲሆን። በአብዛኞቹ ዘንድ ተወዳጅነትን ያገኙ ሙዚቃዎቹን ከታች የተጠቀሱትን ጨምሮ ብዙ ሙዚቃ ለህዝቡ አድርሰዋል።

1. "ጋሽ ጀንበሬ "

2. "ትዝታ አያረጅም "

3. "ውሸቴን ነው"

4. "ስለ ውበቷ ሳደንቅ"

5. "የሐረር ወጣት"

6. "የእንጆሪ ፍሬ "

7. "አደረች አራዳ"

8. "ትዝታ"

9. "እትት በረደኝ"

10."ፍቅራችን ብዛቱ"

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #minilikwesnachew
" ከፍቅረኛዬ ጋር ሆኜ ሌላ ወንድ አፈቀርኩኝ " ድምፃዊት እግቱ

አርቲስት እግቱ ( ትእግስት) :- በጣም የምወደው ፍቅረኛ ነበረኝ እና ከሱ ጋር ሆኜ ሌላ ሰው ወደድኩኝ ። የሱ መጎዳት በፍፁም ሁለተኛ አስባለኝ። ፈልገኸው አይደለም ፤ ግን የኔ ብለህ ሰው ካስቀመጥክ ከሱ ጋር ጉዳይህን ሳትጨረስ ሌላ ነገር ማድረግ ነውር ነው አይደረገም በማለት በማያ ሚዲያ በሚቀርበው የልብ ወግ ፕሮግራም ላይ ሃሳቧን ገልፃለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #igtu
ሃሌሉያ ተ/ፃዲቅ በአዲስ አልበም

"ከመጀመሪያው የብቻ አልበሜ "ተወዳጅ" በሁዋላ ለእናንተ ላደርሰው አስቤ ስተጋ የከረምኩበትን የአልበም እኩሌታ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ:: 4:28 ይሰኛል🎊🎊 ርዕሱ ቆንጆ ምክንያትም አለው:: እናም አርብ ከአልበም እኩሌታዬ የመጀመሪያውን ሙዚቃ ቪዲዮ በራሴ Haleluya Tekletsadik ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለእናንተ አደርሳለሁ🤗🤗 እንደምትወዱትም አምናለሁ! " - ሃሌ (ሃሌሉያ ተ/ፃዲቅ)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Hallelujah #hale
አብርሃም በላይነህ - ሻላዬ ቀን በቀን አዲስ አልበም ሊለቀቅ ነዉ!

በሀገራችን የሙዚቃ እንደስትሪ ውስጥ ጉልህ ድርሻን ካበረከቱ ወጣት ድምፃዊያን መካከል እና የተለያዩ ነጠላ ሙዚቃ ሥራዎችን በመስራት እና በትወናው ዘርፍ በመሳተፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደማጭና ታዋቂ ለመሆን የቻለውን ተወዳጁ ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ/ሸላዬ/ ሙሉ የሙዚቃ አልበሙን ወደ ሕዝብ ለማድረስ መሰናዶውን እንደጨረሰና ከአስራ ሦስት ዓመታት በፊት ለአድማጭ ባደረሰው “ሻላዬ” ነጠላ ዜማው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው አብርሃም በላይነህ እነሆ ዛሬ ደግሞ ዘጠኝ አመት የተደከመበትን እና 12 ዜማዎችን የያዘዉን “ቀን በቀን” የተሰኘ አልበም ለሙዚቃ አፍቃሪያን እንካችሁ ሊለን ነው፡፡

አብርሃም በላይነህ በሥራዎቹ የአገራችንን ባህልና አዳዲስ ነገሮችን ለማስተዋወቅ የሚጥር ሲሆን በ 2013 ዓ.ም በለቀቀው “ዳርም የለው” ነጠላ ዜማ ከተወዳጁ የኦሮምኛ ድምፃዊ አሊ ቢራ ጋር በመሆን ታሪክን ተጋርቷል ጡሁም ዜማንም አስደምጦናል፡፡ ድምጻዊው በአዲስ አልበሙም ከኤልያስ መልካ ጋር በመሆን የሰራቸው አምስት ሙዚቃዎችና ከሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ጋር በተጣመረበቻው ሰባት ዜማዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በላቁ ሙዚቃዊ ሀሳቦች ፍቅርን፣ተስፋንና አገራዊ አንድነትን እሴቶችን እና ምክርን አንፀባርቋል፡፡ “ቀን በቀን” አልበም 9 ዓመታትን የዝግጅት ጊዜን የጠየቀ ሲሆን ወንደወሰን ይሁብ፣ መሰለ ጌታሁን፣ናትናኤል ግርማቸው፣ እና አንተነህ ወራሽን የመሳሰሉ የአገራችን የሙዚቃ ሰዎች ተሳትፎ አድርገውበታል፡፡

አልበሙ የፊታችን ታኅሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአብርሃም በላይነህ የዩቱዩብ ቻናልና በመላው ዓለም በሚገኙ የሙዚቃ መተገበሪያዎች ለአድማጭ ይደርሳል፡፡

@waliyaentmt
@waliyaentmt