Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ተወዳጁ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ከአባቱ ሞት በዃላ የአልበም ምርቃቱን ሊያደርግ ነው።

በብዙዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅነትን ያገኘው የሚካኤል በላይነህ አዲሱ ‘አንድ ቃል’ የተሰኘውን አልበም ቅዳሜ ጥቅምት 30 /Nov. 09/ በማርዯት ሆቴል ለማስመርቅ ዝግጅቱን ጨርሷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #micheal_belayneh
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በዩቲዩብ ከ 1ሚሊዮን በላይ ሰብስክራይበር በማግኘት የዩቲዩብ ጎልድ በተን ተሸላሚ ሆነ።

እንኳን ደስ አለህ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro
ወጣቱ ድምፃዊ ከወራት በኋላ የአልበም ስራውን ለአድማጭ እንደሚያደርስ ገለፀ

ከእዚህ ቀደም ሰርቶ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ባደረሳቸው አንቀልባ፣ ሀገሬ፣ ንማጀ፣ እንዲ ነው ወይ? እና ሌሎች ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎች የሚታወቀው ወጣቱ ድምፃዊ በፍቃዱ ያደቴ (በፊ ያድ) የመጀመሪያ አልበሙን ሰርቶ እንዳጠናቀቀ ተናግሯል።

በአልበም ስራው ውስጥ የተለያዩ ሀሳቦችን እና በልዩ ልዩ ስልተ ምት የተቃኙ ስራዎች እንደተካተቱበት ድምፃዊው አንስቷል።

እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ የአልበም ስራውን ለአድማጭ ለማድረስ መታቀዱን የገለፀ ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ እንዳደረጉበት ገልጿል።

ከአንድ ሳምንት በፊት ለአልበሙ መዳረሻ ይሆን ዘንድ ታስቦ የተሰራው ነጠላ ዜማው በድምፃዊው ስም በተከፈተው ዩቲዩብ ቻናል መለቀቁንም ተናግሯል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #befiyad
የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ አልባሳትና ቁሳቁስ ለዕይታ ሊቀርብ ነው።

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ አልባሳት እና ቁሳቁስ ትውልድ እንዲያየው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ተቋም ጥቅምት 29 ቀን 2017 በክብር ይቀመጣል ተባለ፡፡
በዕለቱም የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ሌሎች እንግዶች እንደሚገኙ የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የመታሰቢያ ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡

ታሪካዊ የሆኑ እና በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ኅያው ሆነው እንዲኖሩ ከአርቲስቱ ቤተሰቦች የተሰበሰቡ አልባሳት እና ቁሳቁሶችንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተረክቦ ለዕይታ ያቀርባሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #tilahun_gessesse
ተወዳጅዋ ድምፃዊ የማርያም ቸርነት (የማ) እና እዩኤል መንግስቱ የኢትዮጵያን ቱባ ክዋኔ ጥበብ ለማስተዋወቅ በአውሮፓ ሊዞሩ ነው።

"በቅርቡ ለሶስት ወር ከግማሽ ከኢትዮጵያ ውጪ በአውሮፓ (ፈረንሳይ፣ ቤልጂየም፣ ስዊትዘርላንድ፣ ሞናኮ ሞንቴካርሎ፣ አንዶራ) በተለይም በተለያዩ የፈረንሳይ ግዛቶች የኢትዮጵያን ቱባ ክዋኔ ጥበብ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል። ለወራት ልምምድ ያደረግንበት ይህንን የሀገራችንን ክውን ጥበብ (Performing Art) በዓለም አቀፍ መድረክ ለማቅረብ ከሙሉ የሙዚቃ፣ የዳንስ እና የሰርከስ ቡድን ጋር ዝግጅታችንን መጨረሳችንን ዛሬ በቱሊፕ ሆቴል /Tulip Hotel/ በነበረን ጋዜጣዊ መግለጫ አብስረናል።

በሚኖሩን በነዚህ ዓለም አቀፍ መድረኮች በኢዩኤል መንግስቱ ፕሮድዩስ ከተደረገው እና የበኩር ስራዬ ከሆነው "ከደጋ ሰው አልበም" ውስጥ የተወሰኑ ስራዎችን የማቀርብ ሲሆን በተጨማሪም በአንጋፋው የፈረንሳይ የፊልም ሙዚቃ ደራሲ፣ አቀናባሪ፣ የሙዚቃ መሪ/conductor/ ክርስቲያን ክራቬሮ የተፃፉ ሙዚቃዎችን የምናቀርብ ይሆናል።

የአፍሪካን ድሪም አርትስ እና ሰርከስ (African Dream Arts and Circus) መስራች፣ ሀላፊ፣ አሰልጣኝ በሆነው የኔነህ ተስፋዬ ዳይሬክተርነት እና በፈረንሳዩ ሰርክ ፌኒክስ ካምፓኒ ፕሮዲዩሰርነት ለተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ክውን ጥበብ /Performing Arts/ በፌኒክስ መድረክ እንድንቀርብ ስለተጋበዝኩ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።" - የማርያም ቸርነት(የማ)

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yema
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠን አልባሳት እና ቁሳቁሶችን ተረከበ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠን አልባሳት እና ቁሳቁሶችን ተረክቧልደ

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠን አልባሳትና ቁሳቁሶች በምርምር ተቋሙ ሙዚየም ማኖሩ ታሪክን ለትውልድ ከማሸጋገርም ባሻገር ተተኪ ሞያተኞችን ለማፍራት ያግዛል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #tilahun_gessese
ሙዚቀኛ መሰለ አስማማው አረፈ

ለ20 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስመጥር የክራር ተጫዋች እና አቀናባሪ የነበረው መሰለ አስማማው ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ሙዚቀኛ መሰለ ባደረበት ህመም ለወራት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ አርፏል ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የአንጋፋው የክራር ሙዚቃ መሳሪያ ተጨዋች መሰለ አስማማው የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ተፈፀመ!

(ይትባረክ ዋለልኝ)

#Ethiopia | የአንጋፋው የክራር ሙዚቃ መሳሪያ ተጨዋች የነበረው መሰለ አስማማው የቀብር ሥነ ሥርዓቱም ዛሬ ረቡዕ ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በየካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቹ ዘመዶቹ ጓደኞቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና ጥቂት ድምፃዊያን ጋዜጠኞች በተገኙበት ተፈፀሟል ፡፡

የመሰለ አስማማው የቀብር ስነስርዓት በየካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና ዲያቆናት በሙያው ብዙ ለሐገሩ ለሰራና ለደከመ ለአንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሐይማኖት ተከታይ የሚደረገውን ስርዓት በማድረግ ቤተክርስቲያኒቱ በክብር ሽኝት በማድረግ ስርዓተ ቀቡሩም እንዲፈፀም አድርጋለች::

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ በነበረው ፕሮግራም የመሰለ አስማማው የህይወት ታሪክ ከመቅረቡ ውጪ አንድ ሙዚቃ ባለሙያ ሲያርፍ ሁልጊዜ በየቀብሩ እንደምናየው አይነት የሐዘን መግለጫ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበርም ሆነ መሰል ተቋሞችና ታዋቂ ግለሰቦችም በሽኝቱ ፕሮግራም ላይ ምንም አላሉም::

ሌላው የሙዚቀኛ መሰለ አስማማውን በሙዚቃ መሳሪያዎችና በክራር የተቀነባበሩ የሙዚቃ ስራዎቹን በፈለጉት ሰዓት ላሻቸው ጉዳይ የሚጠቀሙበት የሐገራችን ሚዲያዎች ዛሬ የዚህን ሰው የቀብር ፕሮግራም ለመዘገብ ቸግሯቸዋል::

በመሰለ የቀብር ፕሮግራም ላይ ከአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ከእኔ /ትርታ ኤፍ ኤም/ ውጪ የተገኝ ሚዲያ አልነበረም ::

ይህ ጉዳይ እጅግ ያሳዝናልም እንደሐገርም የሚያሳፍር ተግባርም ነው:: ይህን ያህል ህዝብ እንዲመጣ የሆነውም በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የተሰራው ዘገባ እንጂ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አንድም ሥራ የለም::

@waliyaentmt
@waliyaentmt
@waliyaentmt