Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
መነበብ አለባቸው የምትያቸው 5 መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው?

ቤቲ ጂ፡የመጀመሪያው የM. M. Kay- ‘The Far Pavilions’ በሕንዳዊና በፈረንጅ መካከል ያለ የፍቅር ታሪክ ነው። በጣም ረዥም ነው። ግን በጣም ከምወዳቸው መጻሕፍት አንዱና ታሪኩን ውስጡ ገብቼ ያነበብኩት ነው። ሁለተኛ ‘ፍቅር አስከ መቃብር’፣ ስለ ኢትዮጵያ ምንነትና ማንነት፤ ስለእኛ ባህልና ሥነ ሥርዓት ማወቅ ከፈለግን. . . ብዙ ምስጢር ያለው መጽሐፍ ነው። ሌላው ‘Romeo and Juliet’ ነው። የፍቅር ታሪክ ነው፣ ግን መቸኮል ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ያሳያል። ሌላኛው ‘Animal Farm’ ነው። አሁን ስለምንኖርበት ዓለምና ስለ ሰዎች አኗኗር ብዙ ትምህርት ይሰጠናል።

የቀጣይ ዓመት ዕቅድሽ ምንድ ነው?
ቤቲ ጂ፡ሁለተኛ ልጄን በሰላም ተገላግዬ፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሦስተኛ አልበሜ ይወጣል። ከዛ በፊት አንድ ነጠላ ዜማ እለቃለሁ ብዬ አስባለሁ። ወደ ፊልም ሙያ ውስጥም ለመግባት እየሞከርኩ ነው። ዘንድሮ በእኛ የክረምት ወቅት በአሜሪካ በነበረኝ ቆይታ የትወና ትምህርት ወስጄ ነበር። ከእኔ ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል ሆኖ ስላገኘሁት ወደ ፊልም ትወና የምገባበት ዓመት ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Betty_g
ፍቅራአዲስ ለበአል ከቢቢሲ ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ

ቢቢሲ፡የ2016 ዓ. ም. ልዩ ትውስታዬ የምትይው ምንድን ነው?

ፍቅርአዲስ፡ በ2016 ዓ. ም. እንዲህ የምለው ነገር የለኝም። አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ትዝታ የለኝም። እውነቱን ልንገርሽ፣ ጭንቀት ነው የማስታውሰው። የጎንደር ልጅ ነኝ። ስደውል ቤተሰብ ውስጥ ያለው ሰላም ማጣት ያስጨንቃል። እየተረበሽ ገንዘብ ብትሠሪም፣ ሥራ ላይ ብትሆኚም ደስታ የለውም።

ቢቢሲ:በበዓል ወቅት በጣም የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው?

ፍቅርአዲስ፡ዶሮ ወጥ እና ጥብስ ነው በጣም ደስ የሚለኝ።

የምንጊዜም ምርጥ የምትያቸው 3 ዘፈኖች ወይም አልበሞች የትኞቹ ናቸው?

ፍቅርአዲስ፡የአስቴር አወቀን ነዋ. . . ከሷ ምንም የምጠላው ዘፈን የለኝም። የአዲስ ዓመቱን ‘እዮሃ አበባዬ’ ብትጋብዢልኝ ደስ ይለኛል። አስቴርን በጣም ነው የምወዳት። ሁሌም ከሷ እማራለሁ። ቀና ናት። በዚሁ እንኳን አደረሰሽ በይልኝ። ከራሴ ሙዚቃዎች ልንገርሽ. . . ‘ልዑል አስወደደኝ’፣ ‘ምስክር’ እና ‘ዞማ’ን እወዳቸዋለሁ።

መነበብ አለባቸው የምትያቸው 5 መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው?

ፍቅርአዲስ፡ከማንበብ ይልቅ ሲነበብ ስሰማ ነው ደስ የሚለኝ። ቢነበቡ የምላቸው ‘አንድ ለእናቱ’ እና የፍቅረማርቆስ ደስታ መጻሕፍት ናቸው። አቤ ቁጭ ስንል አንብቦልኛል። አቤ ግጥሙን የጻፈው ‘ያሙ ያሙ’ የሚለው ዘፈኔ ‘አቻሜ’ ከሚለው መጽሐፍ ነው የተወሰደው። በትረካ ሰምቼ ከወደድኳቸው መካከል ‘ፍቅር እስከ መቃብር’ ዋናው ነው።

የቀጣይ ዓመት ዕቅድሽ ምንድ ነው?
ፍቅርአዲስ፡ሁሉም ነገር ሰላም ሆኖ፣ በቀጣይ ዓመት የሠራሁትን ሲዲ ለማውጣት ዝግጀት ላይ ነኝ።

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
ዮሐና አሸናፊ በአዲስ አመት አዲስ አልበም ይዞ እየመጣ ይገኛል በዚህ የመጀመርያው የአልበም እንደሚለቀቅ ያበሰረው ዮሐና አሸናፊ ነው፡፡

በማህበራዊ ገፁ ይንን ብሏል፡፡
“ጤና ይስጥልኝ ነግቷል አዲስ አመት መጥቷል ….. አዲሱ አመት አኔ ጋር አዲስ አልበም ይዟል!እናንተጋስ?” ሲል ገልጿል”፡፡ ብሏል፡፡
...

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yohanna
የኢትዮጵያ ወርቃማው የሙዚቃ ታሪክ ሲነሳ . . .

#Ethiopia | የወርቃማው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ባለውለታ አርቲስት መርዓዊ ስጦት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ግንባር ቀደም ቦታ ከሚይዙ አንጋፋ ሙዚቀኞች መካከል አንዱ ናቸው ። ከሀምሳ አምስት ዓመት በላይ በቆየበት የሙዚቃ ህይወቱ በክላርኔትና አልቶ ሳክስ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት በሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲነት በአቀናባሪነት እንዲሁም በኃላፊነት (አመራር) ቦታ ላይ ለበርካታ አመታት አገልግለዋል ።

የአምባሰሉ ንጉስ የክላርኔት ንጉስ በመባል የሚታወቀው ጋሽ መርዓዊ ስጦት ውልደትና እድገታቸው ከወሎ አምባሰል ልዩ ስሙ ዳቃ ወረዳ ነው ። ከአምባሰል ወጥተው በክላርኔት አምባሰልን ወደር በማይገኝለት ሁኔታ በመጫወት በሙዚቃ መድረክ ላይ ነግሰው ኖረዋል ። አርቲስት መርዓዊ ስጦት አምባሰልን ሲጫወቱ አይቶ ስሜቱ የማይኮረኮር ፣ የማያነባ የለም ።

የሙዚቃ ህይወታቸው የሚጀምረው በ1942 ዓ.ም ገና የ14 አመት ልጅ እያሉ የማዘጋጃ ቤት በወቅቱ የሙዚቃ እና ቴአትር ማስፋፊያ "ጎንደሬው ገብረማርያም " የተሰኘ ቴአትርና የመንገድ ላይ የሙዚቃ ትርኢት (ፋንፋር ባንድ) ለማሳየት ደሴ በመጡበት ወቅት ልባቸው ይሰረቅና እሳቸውም እንደነሱ መሆን እንደሚፈልጉ በመጠየቃቸው አዲስ አበባ ከመጡ እናስተምሮታለን ይሎቸዋል።
ይህ ቃል በጊዜው ከሰጡት ውስጥ አንዱ ተስፋዬ ሳህሉ "አባባ ተስፋዬ " ነበሩ ። እሳቸውም ለአዲስ አመት የእንቁጣጣሽ አበባ ስለው በየሹማምንቱ ቤት በማዞር ሀምሳ ብር ይሰበስቡና ወዴት ነህ የሚለው ጥያቄ እንዳያስጨንቃቸው ሆን ብለው ብርድ ልብስ ቀደው ላሰፋ ነው ።  በሚል ሰበብ ከቤት ይወጣኑ ከአንድ ጣልያናዊ ሹፌር ጋር ተነጋግረው በትሬንታ ኳትሮል ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ ።

አጠያይቀውም ቃል የገቡላቸውን ሰዎች ያገኙና በአስራ አራት አመታቸው የሙዚቃ ትምህርታቸውን ይጀምራል ። ከትምህርታቸው ጋር አንድ ላይ ማደርያና የኪስ ገንዘብ ጭምር ይሰጣቸው ነበር ።  በወቅቱ ከእሳቸው ጋር አብረው ከነበሩት ሙዚቀኞች መሀል የሳክስፎኑ ንጉሥ ጌታቸው መኩሪያ አንዱ ናቸው ። ስድስት አመት በዚህ ሁኔታ ካሳለፉ በኋላ የጃንሆይ  25ኛ የብር ኢዩቤልዩ በአል ምክንያት በማደረግ የአሁኑ ብሄራዊ ቴአትር የቀድሞ ቀ. ኃ.ስ ቴአትር ቤት ሲቁቋም ከተመረጡት አስራ ሶስት ሙዚቀኞች መካከል አንዱ በመሆን መስራች ሆኑ ።

በአርመናዊው አስተማሪና አለቃቸው ሙሴ ነርሲስ በምግባራቸውም ሆነ በትምህርት አቀባበላቸው የሚደነቁት አርቲስት መርዓዊ ከሙሴ ነርሲስ ህልፈት በኋላ የሙዚቃ ክፍሉን ተረክበው ለሰላሳ አመታት በአለቃነት አገልግለዋል። በዚህም ወቅት ለአርቲስት ምኒልክ ወስናቸው ፣  ለመልካሙ ተበጀ  ፣ ጠለላ ከበደ ፣ ፍቅርተ ደሳለኝ . . .  ለበርካቶች ግጥምና ዜማ ደርሰዋል ። ሙዚቃ አቀናብረዋል ። ከነዚህም ውስጥ የምኒልክ ወስናቸው የእንጆሪ ፍሬ፣ ትዝታ አያረጅም፣ስኳር ስኳር፣ አፈር አትንፈጊኝ፣ በምድረ ሱዳን ያለሽው ፣ ጥቁሯ ጽጌረዳ፣ የመልካሙ ተበጀ፣ ብእር ብእር ፣ ሰላም ጤና ይስጥልኝ፣ ንቢቱ፣ የፍቅርተ ደሳለኝ ልማት ልማት ሌሎችም ይገኙበታል ።

ከዚህም ባሻገር ከ200 የማያንሱ አብዮታዊ  መዝሙሮችን፣ ለሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እና ለሌሎችም በርካታ ታዋቂ ቴአትሮች ማጀቢያ ሙዚቃዎችን ደርሰዋል ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብም የመጀመርያ የሆነውን የክለቡን መዝሙር የሰሩት አርቲስት መርዓዊ ስጦት ናቸው ።  በአፄ ኃይለስላሴ ፣ በዘመነ ደርግ እና በዘመነ ኢህዲግ ጊዜ በተሰራው የኢትይጵያ ህዝብ መዝሙር ላይ የጋሽ መርዓዊ ትንፋሽ ተቀርጿል! ዜማው በሚሰራበት ጊዜም ኦርኬስትራውን የመምራትና የማስተባበር ስራውን የሰረት ጋሽ መራዊ ስጦት ናቸው ። 

በሙያው All Black People Music Festival ጨምሮ በናይጄሪያ ፣  በግብጽ በሱዳን ፣ በቻይና በራሺያ ፣ በአሜሪካ እና ሌሎችም ሀገራት ሀገሩን ወክሎ ተሳትፈዋል ። በአሜሪካ ሀገርም ከሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ ጋር በመሆን አምባሰልና ትዝታ ለትውልድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲተላለፍ በካሴትና በሲዲ አስቀረጸዋል  ። ለዚህና መሰል አስተዋጽኦ በተለያዩ ጊዜያት ሽልማትን አግኝተዋል ።

★ ከጃንሆይ የማበረታቻና የመጻህፍት ሽልማት

★ በደርግ ጊዜ በማስታውቂያ ሚኒስትር የምስጉን ሰራተኛ ወርቅ ተሸላሚ።

★ የአለም አቀፍ ጎልድ ሜርኩሪ ሽልማት (ሽልማቱ አለማቀፋዊና ትላልቅ የአለም መሪዎችን ጨምሮ ሳይንቲስቶችና ምሁራን የሚሸለሙት ነው )

★ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር  የወርቅ ሽልማት

★ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ማህበር የክብር ሽልማት ።

★ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር (ባህል ማዕከል) የክብር ዋንጫ ተሸላሚ።

★ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ የክብር ሜዳሊያ ሽልማት ጥቆቶቹ ናቸው።

ጋሽ መርዓዊ ጡረታም ከወጡም በኋላ ከሙዚቃው ሳይርቁ እስከ ቅርብ ጊዜ ከብሄራዊ ቴአትር ደጅ አይጠፋም ። የልብ ህመም አጋጥሞቸው የትንፋሽ መሳሪያ መጫወት እስከተከለከሉበት ጊዜ ድረስ ክላርኔታቸውን ይዞው መገኘት ባለባቸው ቦታ ሁሉ እየተገኙ ህዝብን ያስደስቱ ነበር ። በህይወታቸው ከኦርኬስትራው ተነጥለው በየትኛውም ምሽት ክለብ ሰርተው አያውቁም  ። በተሰጥኦ ያምናሉ ። አዳዲስ ወጣቶች በመጡም ጊዜ ካሉበት አድኖ በማግኘት እና በማበረታታት ይታወቃሉ።  

አርቲስት መርዓዊ ስጦት ባላቸው ጊዜ ሁሉ ባለተሰጦ ልጆች በማደን ችሎታቸውን እያደነቁ ፣  እየመከሩ የሚያበረታቱና ምን አይነት አርቲስት መሆን እንዳለባቸው ምሳሌ  በመሆን ጭምር የሚደግፍ የሙያ አባትም ጭምር ናቸው ! ለዚህም "የአለም አቀፍ ሜርኩሪ" ሽልማታቸው ወጣት ባለሙያዎች ባዩት ጊዜ እንዲበረታቱበትና እንዱነሳሱበት በማሰብ በስጦታ መልክ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ዋና ስራ አስኪያጅ ቢሮ እንዲቀመጥ አስረክበዋል ።

ሆኖም የኢትዮጵያ የሚዚቃ ወርቃማ ዘመን ባለውለታ አርቲስት መርዓዊ ስጦት ለዘመናት የኖሩበት መኖሪያ ቤት በቅርቡ ሊፈርስ እንደሆነ ተነግሯቸዋል ። ሆኖም 40/60 ኮንዶሚኒየም ምዝገባ በነበረበት ወቅት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተመዝግበው ሙሉ ክፍያ ፈፅመው ቤቱ ያልተሰጣቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ የሚመለከተው አካል ጋር በተደጋጋሚ አቤት ቢሉ ሰሚ አጥተው እጅጉን አዝነው ይገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር ፣ የኢትዮጵያ ባህል እና እስፓርት ሚኒስትር ለእኚ ባለውለታ ለሀገር የዋሉትን ውለታ ተመልክቶ ለከፈሉት ክፍያ ተገቢውን ምላሽ ከከተማ መስተዳደሩ ያገኙ ዘንድ ጥሪ ለማስተላለፍ እወዳለሁ !

ባለውለታን ማክበር ነገ ባለውለታ ዜጋን ማፈራት ነውና ባለውለቶቻችንን እናክብር !!!

ታሪኩ ዘውዱ
ከካናዳ 🇨🇦

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የድምፃዊ ንዋይ ደበበ እና የአይዳ ሐሰን ወንድ ልጅ የሆነው ሰላም ንዋይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በጋብቻ ተሳስረው አሜሪካን አገር ለረጅም አመት የኖሩት ንዋይና አይዳ ከቅርብ ዓመታት በፊት በይፋ መለያየታቸውን ቢገልፁም እንደ ቤተሰብ ብዙም አልተራራቁም። በትዳር ሕይወታቸው ፅናት የተባለች ሴት ልጅና ሰላም የተባለ ወንድ ልጅ በጋራ ያፈሩት ንዋይና አይዳ ልጆቻቸውን ያሳደጉት ቨርጂንያ ውስጥ ሲሆን፣ ሰላም ከጊዜ በኋላ በገጠመው የጤና እክል የተነሳ ሕክምና ሲከታተል ቆይቷል። በተለይ የኩላሊት ኢንፌክሽን ተጠቂ በነበረበት ሰዓት አንድ ኩላሊት እናቱ አይዳ ሰጥታው ንቅለ ተከላ ማድረጉ ይታወሳል።

ከልጅነቱ ጀምሮ ተጨዋች፣ ሳቂታ እና ቀልድ የሚወድ ተወዳጅ ልጅ ነበር ትምህርቱን ተከታትሎ ያጠናቀቀው እዚያው አሜሪካን አገር ሲሆን፣ ሲበዛ አዛኝ ልብ የነበረውና ሰዎችን መርዳት የሚያስደስተው ሰላም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #neway_debebe
በዩቲዩብ በብዛት ተመልካች ያገኙ 10 የሳምንቱ ሙዚቃዎች

በዚህ ሳምንት "ወረ ቦሌ" የተሰኘ የሶና ታከለ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ተከታታይ ሳምንት ደረጃውን እየመራ ነው። አልበሟን የለቀቅችው ቬሮኒካ አዳነ ባ ለፈው ሳምንት በአምስት ሙዚቃዎች የደረጃ ሰንጠረዡን ተቆጣጥራ የነበረ ቢሆንም በዚህ ሳምንት ተመልሰው ወርዷል።

1ኛ🟡 ሶና ታከለ (ወረ ቦሌ) 🎶 982,943 እይታ
2ኛ🟢 ኤደን ገ/ሥላሴ (ይኹን) 🎶 751,847 እይታ
3ኛ🟢 አብዱ ኪያር (ገለመሌ) 🎶 499,553 እይታ
4ኛ🟢 አብዱ ኪያር (ቡቡዬ) 🎶 412,327 እይታ
5ኛ🟢 አንዱዓለም ጎሳ (ቢሊሌ) 🎶 399,247 እይታ
6ኛ🟢 ሰላማዊት ዮሐንስ (ሰንቢደ) 🎶 396,519 እይታ
7ኛ🟢 ቬሮኒካ አዳነ (ተናገር) 🎶 388,952 እይታ
8ኛ🔴 ቬሮኒካ አዳነ (መጠሪያዬ) 🎶 371,724 እይታ
9ኛ🔴 ልጅ ሚካኤል (የድሬ ልጅ) 🎶 351,081 እይታ
10ኛ🟢 ልጅ ሚካኤል (አዲስ አራዳ) 🎶 311,157 እይታ

🟢 ደረጃ ያሻሻሉ
🔴 ደረጃ የቀነሱ
🟡 ባሉበት ደረጃ የቆዩ

🎶 በሳምንቱ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት የታዩ ሙዚቃዎችን በትክክለኛ ዳታ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ምርጥ አስር ሙዚቃ ሰንጠረዥ ነው።

🎶 ቁጥሮች በሳምንት ውስጥ የጨመሩትን እይታ ብቻ ነው የሚያሳየው።

ቅዳሜ መስከረም 3/2017 ዓ.ም

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
Waliya Masterclass: An Evening of Musical Inspiration

Join us for an unforgettable musical journey at the Waliya Masterclass, hosted by @waliyaentmt at the British Council.

Be captivated by the enchanting voice of Yemariam Chernet (Yema), the star behind the acclaimed album "Yedega Sew," and the brilliant producer Eyuel Mengistu.

Discover their stories: Dive into the creative process, challenges, and triumphs that brought this masterpiece to life. This event is a must for every music enthusiast!

Experience live performances: Enjoy an evening filled with live music from Talented artists.

📅 Date: Saturday, September 21 
🕓 Time: 4 PM sharp 
📍 Venue: British Council, inside British Embassy

🚪Free Enterance

⭕️ Remember to bring your ID and arrive on time as seats are limited!

Reserve your spot👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeN_V7VRiXUra9yr_6SUnRDtRSZyyylQ-Hyq5yf8FXY4xj1hA/viewform?usp=sf_link

@Waliyaentmt @yemisme @eyuelmengistu @BritishCouncilEthiopia
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!!

ዋልያ ማስተርክላስ በተሰኘው ወርሃዊ ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ዙር ብዙዎች ሙገሳ ከቸሯት እና ትንሿ ጂጂ እያሉ  ከሚያደንቋት ድምፃዊት የማርያም ቸርነት (የማ) እና ከአልበሙ አዘጋጅ ፣ አቀናባሪ እንዲሁም ዜማ እና ግጥም ደራሲ ከሆነው እዩኤል መንግስቱ ጋር ከ "የደጋ ሰው" አልበም ጀርባ ያለውን ታሪክ ልምዳቸውን ሊያካፍሉን የፊታችን ቅዳሜ በብሪቲሽ ካውንስል ከ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

📅 ቀን : ቅዳሜ, መስከረም 11
🕓 ሰአት : ከቀኑ 10 ሰአት
📍 ቦታ : ብሪቲሽ ካውንስል (እንግሊዝ ኢምባሲ ውስጥ)

🚪መግቢያ በነፃ

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ለመታደም ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ ቀድመው ይመዝገቡ👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeN_V7VRiXUra9yr_6SUnRDtRSZyyylQ-Hyq5yf8FXY4xj1hA/viewform?usp=sf_link

አዘጋጅ :- ዋልያ ኢንተርቴይመንት

@Waliyaentmt @yemisme @eyuelmengistu @BritishCouncilEthiopia
2 ቀን ቀረው!!!

ዋልያ ማስተርክላስ በተሰኘው መርሃግብራችት የ ጂጂ ምትክ እያሉ  ብዙዎች ከሚያደንቋት ድምፃዊት የማርያም ቸርነት (የማ) እና ከአልበሙ አዘጋጅ ፣ አቀናባሪ እንዲሁም ዜማ እና ግጥም ደራሲ ከሆነው እዩኤል መንግስቱ ጋር ከ "የደጋ ሰው" አልበም ጀርባ ያለውን ታሪክ ልምዳቸውን ሊያካፍሉን የፊታችን ቅዳሜ በብሪቲሽ ካውንስል ከ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

📅 ቀን : ቅዳሜ, መስከረም 11
🕓 ሰአት : ከቀኑ 10 ሰአት
📍 ቦታ : ብሪቲሽ ካውንስል (እንግሊዝ ኢምባሲ ውስጥ)

🚪መግቢያ በነፃ

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ለመታደም ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ ቀድመው ይመዝገቡ👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeN_V7VRiXUra9yr_6SUnRDtRSZyyylQ-Hyq5yf8FXY4xj1hA/viewform?usp=sf_link

አዘጋጅ :- ዋልያ ኢንተርቴይመንት

@Waliyaentmt @yemisme @eyuelmengistu @BritishCouncilEthiopia
ነገ 10:00 አይቀርም!!!

ዋልያ ማስተርክላስ በተሰኘው መርሃግብራችት የ ጂጂ ምትክ እያሉ  ብዙዎች ከሚያደንቋት ድምፃዊት የማርያም ቸርነት (የማ) እና ከአልበሙ አዘጋጅ ፣ አቀናባሪ እንዲሁም ዜማ እና ግጥም ደራሲ ከሆነው እዩኤል መንግስቱ ጋር ከ "የደጋ ሰው" አልበም ጀርባ ያለውን ታሪክ ልምዳቸውን ሊያካፍሉን የፊታችን ቅዳሜ በብሪቲሽ ካውንስል ከ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

📅 ቀን : ቅዳሜ, መስከረም 11
🕓 ሰአት : ከቀኑ 10 ሰአት
📍 ቦታ : ብሪቲሽ ካውንስል (እንግሊዝ ኢምባሲ ውስጥ)

🚪መግቢያ በነፃ

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ለመታደም ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ ቀድመው ይመዝገቡ👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeN_V7VRiXUra9yr_6SUnRDtRSZyyylQ-Hyq5yf8FXY4xj1hA/viewform?usp=sf_link

አዘጋጅ :- ዋልያ ኢንተርቴይመንት

@Waliyaentmt @yemisme @eyuelmengistu @BritishCouncilEthiopia
ቴዲ አፍሮ የቢቂላ ሽልማትን ተሸለመ

በሀገራችን እንቁ አትሌት የተሰየመው “ቢቂላ አዋርድ” ትልቅ ክብር ከሚሰጣቸው የሽልማት ተቋሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን እስካሁንም ለበርካታ የሀገር ባለውለታዎች እውቅናን በመስጠት ሲሸልም ቆይቷል። ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award) ከሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ከምንም አይነት ትርፍ እራሱን ባገለለ መልኩ በካናዳ ከ50 አመታት በላይ በኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው የተቋቋመው። ይህ ተቋም በትምህርታቸው፣ በንግዳቸው፣ በሙያቸው ብሎም በበጎ አድራጎት ስራ ተሰማርተው ልዩ ስኬት ያስመዘገቡ እና አርአያ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ በመሸለም እውቅናን የሚሰጥ ትልቅ ኢትዮጵያዊ መድረክ ነው።

በዚህ አመት አስረኛ (10) የምስረታ በአሉን ያከበረው የቢቂላ አዋርድ ተቋም፥ ትላንት ምሽት መስከረም 11 (21 September 2024) በተደረገው መርሃ ግብር ላይ በሙዚቃው ዘርፍ የዚህ አመት ተሸላሚ የሆነው የግጥምና የዜማ ደራሲ ብሎም የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነውን የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን በዚህ ግዙፍ መርሃግብር ላይ በመገኘት ሽልማቱን በደማቅ ስነስርዓት በክብር ተቀብሏል

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro
ሮፋናን ኑሪ በሀዋሳ እና በወላይታ የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ ነው፡፡ተወዳጁ የግጥም ዜማ ደራሲ እንዲሁም አቀናባሪ ሮፍናን ኑሪ ከሀገር ውጪ ወደ ባህር ማዶ ተጉዞ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር የሙዚቃ ስራዎችን ሲያቀርብ ቆይቶ ነበር፡፡ አሁን ደሞ በኢትዮጲያ የሙዚቃ ስራዎችን ለማቅረብ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

የኔ ትውልድ ጥቅምት 2/2017 በበሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ጥቅምት 9 በወላይታ ዝግጅቱን ያቀርባል ተብሏል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #rophnan