Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቹ

      🌼 መልካም አዲስ አመት🌼

https://youtu.be/FUorYcTAA0A?si=9ZtS0h-kj63Gs0SU

#newyear #Ethiopia #waliya_entertainment
የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ከ አርቲስቶች

"በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ። መጪው አዲስ ዓመት የሰላም የአንድነትና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል!" - ቴዲ አፍሮ

"ክፉ ዓመት ነበር እንኳንም አለፈ::😫
ወዳጆቼ ክፉ እንዳሰበልን ሳይሆን እርሱ እንዳሰበልን ሆኖ እንኳንም አሻገረን::

ኡፍፍፍ ...እግዚአብሔር ግን  ይችላል!!💪🏾

#መልካም_አዲስ_አመት🌼🌼🌼 " - አስጉ.

"ጤና ይስጥልኝ ነግቷል
አዲስ አመት መጥቷል .....
አዲሱ አመት አኔ ጋር አዲስ አልበም ይዟል!
እናንተጋስ?" -  ዬሃና

"🌼🌼🌼
ሰላም እንዴት ናችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ ውድ የሀገሬ ልጆች

እንኳን ለ2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ እያልኩኝ መጪው አዲስ ዓመት በሀገራችን ሰላም ፍቅር ጤና እንዲሁም በረከት የሚነግሥበት ዓመት ይሆን ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው!
🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼" - ዳዊት ፅጌ

"መልካም አዲስ አመት🌼🌼🌼
እንኳን አደረሳችሁ !!
Happy Ethiopian new year !" - ሄዋን ገ/ወልድ

"በሀገር ውስጥም በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
መልካም አዲስ አመት እንዲሆንልን  እመኛለሁ ሰላም ፍቅር ጤና ለሁላችን" - ዲበኩሉ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #newyear
በ2016 በዩቲዩብ በርካታ ተመልካች ያገኙ ምርጥ 10 የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች

1ኛ ቬሮኒካ አዳነ [እናነይ] 18+ ሚሊዮን
2ኛ ሮፍናን [ሸግዬ] 13+ ሚሊዮን
3ኛ ዮሰን ጌታሁን [ባለ ጊዜ] 9+ ሚሊዮን
4ኛ ልዑል ሲሳይ [የኔ አመል] 9+ ሚሊዮን
5ኛ አንዱዓለም ጎሳ [ቢሊሌ] 9+ ሚሊዮን
6ኛ ዳኜ ዋለ [ወንድ ልጅ ቆረጠ] 9+ ሚሊዮን
7ኛ ናሆም መኩሪያ [ባዳ ባዳ] 8+ ሚሊዮን
8ኛ እዮብ በላይ [ማለዳ] 8+ ሚሊዮን
9ኛ ያሬድ ነጉ [ሁሌ] 7+ ሚሊዮን
10ኛ አብዱ ኪያር [ገለመሌ] 7+ ሚሊዮን

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ኩኩ ሰብስቤ ለበአል ከቢቢሲ ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ

ቢቢሲ፡ የ2016 ዓ. ም. ልዩ ትውስታዬ የምትይው ምንድን ነው?

ኩኩ፡ በ2016 ዓ. ም. አሜሪካ ለስድስት ወር ቆይቻለሁ። ለ16 ዓመት የኖርኩበት አገር ነውና እዛ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወዳጆቼን፣ ጓደኞቼን አዝናንቻለሁ። ሳን ፍራንሲስኮ፣ ሲያትል፣ ዲሲ እንዲሁም ካናዳ። በዛው ዓመታዊ የጤና ምርመራ አድርጌ፣ ከወዳጆቼ ጋር ገበያ አድርጌም ነበር። ሌላው፣ በየጊዜው ስሄድ እንደማደርገው ከኢትዮጵያ ቁልፍ መያዣዎች ይዤ ሄጄ ነበር። ሰዎች በ20 ዶላርም፣ በ100 ዶላርም ገዝተውኛል። ያንን ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ አምጥቼ ለችግረኞች መርጃ እንዲውል ሰጥቻለሁ። አዲስ አልበም በቅርቡ ስለማወጣ እዛ ሆኜ ብዙ ነገር አዘጋጅቻለሁ።

በበዓል ወቅት በጣም የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው?

ኩኩ፡ክትፎና ዶሮ ወጥ እወዳለሁ። ዋና እነሱ ናቸው። የበግ ወጥም እወዳለሁ።
የምንጊዜም ምርጥ የምትያቸው 3 ዘፈኖች ወይም አልበሞች የትኞቹ ናቸው?

ኩኩ፡የውልሽ. . .ሙዚቃ እንደ ቀለም ነው። ቀለሞች ሁሉ ስናያቸው እንደምንወዳቸው፣ ብዙ የተለያዩ ዘፋኞችን እኔ በጣም ነው የምወዳቸው። ያለ ምክንያት በአንድ ወቅት ዝነኛ አልሆኑም እና ልክ እንደ ቀለም ለመምረጥ ያስቸግረኛል። ሙሉቀን መለሰ፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ ቴዲ አፍሮ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ አስቴር አወቀ፣ ጂጂ፣ ሐመልማል፣ ነጻነት. . . ስንቱን እዘረዝራለሁ? ቴዲ አፍሮ የሕዝብ ልጅ፣ መልዕክተኛ ስለሆነ እጅግ በጣም አደንቀዋለሁ። ከእኔ ዘፈኖች ምረጭ ብትይኝ፣ ‘ከልጆቻችሁ የቱን አብልጣችሁ ትወዳላችሁ?’ እንደማለት ነው። ቢሆንም ያነሳኝ ዘፈንና መታወቂያዬ ስለሆነ ‘ፍቅርህ በረታብኝ’ ን በጣም ነው የምወደው። ትዝታ አልበሞቼ ላይ ያሉ የትዝታ ቅኝቶቼንም እወዳለሁ።

መነበብ አለባቸው የምትያቸው 5 መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው?

ኩኩ፡‘ፍቅር እስከ መቃብር’፣ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው የጻፉት ‘አርሙኝ’- ድሮ ያነበብኩት አስተማሪና ደስ የሚል ታሪክ ያለው መጽሐፍ ነው፣ ሌላው የአቤ ጉበኛ ‘አልወለድም’ እና ከአሁኖች ደግሞ ‘እመጓ’ መነበብ ያለባቸው መጻሕፍት ናቸው እላለሁ።

የቀጣይ ዓመት ዕቅድሽ ምንድ ነው?

ኩኩ፡ በ2017 ዓ. ም. አልበሜ ይወጣል። እንደእኔ ሐሳብና ፍላጎት፣ በመስከረም መጨረሻ ወይም በጥቅምት እንደሚያልቅ ተስፋ አለኝ። 90 በመቶው አልቋል። ትንሽ የሚስተካከል ነገር ነው የቀረው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Kuku_Sebsibe
አቢ ላቀው ለበአል ከቢቢሲ ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ

ቢቢሲ፡ የ2016 ዓ. ም. ልዩ ትውስታዬ የምትይው ምንድን ነው?

አቢ፡ እውነቱን ለመናገር አገር ቤት ባለው ሁኔታ የተነሳ በ2016 ዓ. ም. ጥሩ ትውስታ የለኝም። 2017 ዓ. ም. አገራችን በጣም የምትፈልገው ሰላም የሚመጣበት፣ ሰዎች ሰላምና ደኅንነታቸው የሚጠበቅበት እንዲሆን እፀልያለሁ።

በበዓል ወቅት በጣም የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው?

አቢ፡ በበዓል የምንበላቸውን ባህላዊ ምግቦችን ሁሉ እወዳቸዋለሁ። ግን በዋናነት ዶሮ ወጥ። በአዲስ ዓመት አከባበር ከምንም በላይ ደስ የሚለኝ ግን የቤተ ክርስቲያን ሥነ ሥርዓትና ቤተሰብ ሲሰባሰብ ነው። ያው በዓሉ አብሮ ተሰባስቦ የመመገብ ስለሆነ።

የምንጊዜም ምርጥ የምትያቸው 3 ዘፈኖች ወይም አልበሞች የትኞቹ ናቸው?

አቢ፡ የአስቴር አወቀ፣ የጂጂ እና የሚካያ በሃይሉ

መነበብ አለባቸው የምትያቸው 5 መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው?

አቢ፡ ሦስት ልንገርሽ። አንደኛ መድሐፍ ቅዱስ፣ ከየትኛው በላይ ነው። ሁለተኛ የPaulo Coelho- ‘The Alchemist’፣ ልባችንን ማዳመጥን እና ሌላ ቦታ የምንፈልገው ነገር ደጃፋችን እንዳለ ያስተምረናል። ሦስተኛ የRobert Kiyosaki- ‘Rich Dad poor Dad’፣ ስለ ፋይናንስ አያያዝ ስለሚያስተምር ማንኛውም ንግድ መክፈት የፈለገ ነው ቢያነበው እላለሁ።

የቀጣይ ዓመት ዕቅድሽ ምንድ ነው?

አቢ፡ ከዓመት በፊት አንድ ፕሮጀክት ጀምሬያለሁ። የቀጣይ ዓመት ዕቅዴ ይሄን ፕሮጀክት ማጠናቀቅ ነው። አንደኛው የሙዚቃ ፕሮጀክቴ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ የራሴን ቢዝነስ መጀመሬ ነው።

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt
ቤቲ ጂ ለበአል ከቢቢሲ ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ

ቢቢሲ፡ የ2016 ዓ. ም. ልዩ ትውስታዬ የምትይው ምንድን ነው?

ቤቲ ጂ፡ ዋናው ከፍታዬ ልጄን ማሳደግ ነበር። አልበሜንም እየሠራሁ ነው። ሁለተኛ ልጅም እየጠበቅኩ ነው። እነዚህ ናቸው ትልልቆቹ የምላቸው።

ቢቢሲ፡ በበዓል ወቅት በጣም የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው?

ቤቲ ጂ፡በበዓል ወቅት በጣም የምወደው ምግብ የእናቴ ዱለት ነው። ጉበት ተመርምሮ በግ አይታረድምና ብዙ ጊዜ በግ ከታረደ በኋላ የምጠይቀው ‘ጉበቱ ደኅና ነው ወይ?’ ብዬ ነው። ምክንያቱም የዱለት ወዳጅ ስለሆንኩና የእናቴ ዱለት በጣም ስለሚጣፍጠኝ።

ቢቢሲ፡ የምንጊዜም ምርጥ ሙዚቃ የምትያቸው 3 ዘፈኖች ወይም አልበሞች የትኞቹ ናቸው?

ቤቲ ጂ፡በዓል ስለሆነ የጋሽ ጥላሁን ‘ክረምት አልፎ በጋ’. . . ልጅ ሆነን ጀምሮ የምንሰማውና በልጅነቴ በዓል ያሳለፍኩበትን የሚያስታውሰኝ ነው። በጣም የማይክል አድናቂ ነኝና ‘Man in the Mirror’ የሚለው ትልቅ ትርጉም ይሰጠኛል።በሕይወታችን ውስጥ ምንም ነገር ስንጠይቅ፣ ለውጥ ማምጣት ስናስብ ራሳችንን ማሰብ አለብን የሚል መልዕክት አለው። ሦስተኛው የብዙነሽ በቀለ ‘የሚያስለቅስ ፍቅር’ ነው። ልጅነቴን ያስታውሰኛል። እናቴ የምትወዳትም ዘፋኝ ስለሆነች የሷን ዘፈን እሞክር ነበር። ሦስት ብቻ ለመምረጥ ግን ከባድ ነው. . . እንደምንም ተጠብቤ ነው የነገርኩሽ።
መነበብ አለባቸው የምትያቸው 5 መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው?

ቤቲ ጂ፡የመጀመሪያው የM. M. Kay- ‘The Far Pavilions’ በሕንዳዊና በፈረንጅ መካከል ያለ የፍቅር ታሪክ ነው። በጣም ረዥም ነው። ግን በጣም ከምወዳቸው መጻሕፍት አንዱና ታሪኩን ውስጡ ገብቼ ያነበብኩት ነው። ሁለተኛ ‘ፍቅር አስከ መቃብር’፣ ስለ ኢትዮጵያ ምንነትና ማንነት፤ ስለእኛ ባህልና ሥነ ሥርዓት ማወቅ ከፈለግን. . . ብዙ ምስጢር ያለው መጽሐፍ ነው። ሌላው ‘Romeo and Juliet’ ነው። የፍቅር ታሪክ ነው፣ ግን መቸኮል ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ያሳያል። ሌላኛው ‘Animal Farm’ ነው። አሁን ስለምንኖርበት ዓለምና ስለ ሰዎች አኗኗር ብዙ ትምህርት ይሰጠናል።

የቀጣይ ዓመት ዕቅድሽ ምንድ ነው?
ቤቲ ጂ፡ሁለተኛ ልጄን በሰላም ተገላግዬ፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሦስተኛ አልበሜ ይወጣል። ከዛ በፊት አንድ ነጠላ ዜማ እለቃለሁ ብዬ አስባለሁ። ወደ ፊልም ሙያ ውስጥም ለመግባት እየሞከርኩ ነው። ዘንድሮ በእኛ የክረምት ወቅት በአሜሪካ በነበረኝ ቆይታ የትወና ትምህርት ወስጄ ነበር። ከእኔ ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል ሆኖ ስላገኘሁት ወደ ፊልም ትወና የምገባበት ዓመት ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Betty_g
ፍቅራአዲስ ለበአል ከቢቢሲ ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ

ቢቢሲ፡የ2016 ዓ. ም. ልዩ ትውስታዬ የምትይው ምንድን ነው?

ፍቅርአዲስ፡ በ2016 ዓ. ም. እንዲህ የምለው ነገር የለኝም። አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ትዝታ የለኝም። እውነቱን ልንገርሽ፣ ጭንቀት ነው የማስታውሰው። የጎንደር ልጅ ነኝ። ስደውል ቤተሰብ ውስጥ ያለው ሰላም ማጣት ያስጨንቃል። እየተረበሽ ገንዘብ ብትሠሪም፣ ሥራ ላይ ብትሆኚም ደስታ የለውም።

ቢቢሲ:በበዓል ወቅት በጣም የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው?

ፍቅርአዲስ፡ዶሮ ወጥ እና ጥብስ ነው በጣም ደስ የሚለኝ።

የምንጊዜም ምርጥ የምትያቸው 3 ዘፈኖች ወይም አልበሞች የትኞቹ ናቸው?

ፍቅርአዲስ፡የአስቴር አወቀን ነዋ. . . ከሷ ምንም የምጠላው ዘፈን የለኝም። የአዲስ ዓመቱን ‘እዮሃ አበባዬ’ ብትጋብዢልኝ ደስ ይለኛል። አስቴርን በጣም ነው የምወዳት። ሁሌም ከሷ እማራለሁ። ቀና ናት። በዚሁ እንኳን አደረሰሽ በይልኝ። ከራሴ ሙዚቃዎች ልንገርሽ. . . ‘ልዑል አስወደደኝ’፣ ‘ምስክር’ እና ‘ዞማ’ን እወዳቸዋለሁ።

መነበብ አለባቸው የምትያቸው 5 መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው?

ፍቅርአዲስ፡ከማንበብ ይልቅ ሲነበብ ስሰማ ነው ደስ የሚለኝ። ቢነበቡ የምላቸው ‘አንድ ለእናቱ’ እና የፍቅረማርቆስ ደስታ መጻሕፍት ናቸው። አቤ ቁጭ ስንል አንብቦልኛል። አቤ ግጥሙን የጻፈው ‘ያሙ ያሙ’ የሚለው ዘፈኔ ‘አቻሜ’ ከሚለው መጽሐፍ ነው የተወሰደው። በትረካ ሰምቼ ከወደድኳቸው መካከል ‘ፍቅር እስከ መቃብር’ ዋናው ነው።

የቀጣይ ዓመት ዕቅድሽ ምንድ ነው?
ፍቅርአዲስ፡ሁሉም ነገር ሰላም ሆኖ፣ በቀጣይ ዓመት የሠራሁትን ሲዲ ለማውጣት ዝግጀት ላይ ነኝ።

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
ዮሐና አሸናፊ በአዲስ አመት አዲስ አልበም ይዞ እየመጣ ይገኛል በዚህ የመጀመርያው የአልበም እንደሚለቀቅ ያበሰረው ዮሐና አሸናፊ ነው፡፡

በማህበራዊ ገፁ ይንን ብሏል፡፡
“ጤና ይስጥልኝ ነግቷል አዲስ አመት መጥቷል ….. አዲሱ አመት አኔ ጋር አዲስ አልበም ይዟል!እናንተጋስ?” ሲል ገልጿል”፡፡ ብሏል፡፡
...

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yohanna
የኢትዮጵያ ወርቃማው የሙዚቃ ታሪክ ሲነሳ . . .

#Ethiopia | የወርቃማው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ባለውለታ አርቲስት መርዓዊ ስጦት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ግንባር ቀደም ቦታ ከሚይዙ አንጋፋ ሙዚቀኞች መካከል አንዱ ናቸው ። ከሀምሳ አምስት ዓመት በላይ በቆየበት የሙዚቃ ህይወቱ በክላርኔትና አልቶ ሳክስ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት በሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲነት በአቀናባሪነት እንዲሁም በኃላፊነት (አመራር) ቦታ ላይ ለበርካታ አመታት አገልግለዋል ።

የአምባሰሉ ንጉስ የክላርኔት ንጉስ በመባል የሚታወቀው ጋሽ መርዓዊ ስጦት ውልደትና እድገታቸው ከወሎ አምባሰል ልዩ ስሙ ዳቃ ወረዳ ነው ። ከአምባሰል ወጥተው በክላርኔት አምባሰልን ወደር በማይገኝለት ሁኔታ በመጫወት በሙዚቃ መድረክ ላይ ነግሰው ኖረዋል ። አርቲስት መርዓዊ ስጦት አምባሰልን ሲጫወቱ አይቶ ስሜቱ የማይኮረኮር ፣ የማያነባ የለም ።

የሙዚቃ ህይወታቸው የሚጀምረው በ1942 ዓ.ም ገና የ14 አመት ልጅ እያሉ የማዘጋጃ ቤት በወቅቱ የሙዚቃ እና ቴአትር ማስፋፊያ "ጎንደሬው ገብረማርያም " የተሰኘ ቴአትርና የመንገድ ላይ የሙዚቃ ትርኢት (ፋንፋር ባንድ) ለማሳየት ደሴ በመጡበት ወቅት ልባቸው ይሰረቅና እሳቸውም እንደነሱ መሆን እንደሚፈልጉ በመጠየቃቸው አዲስ አበባ ከመጡ እናስተምሮታለን ይሎቸዋል።
ይህ ቃል በጊዜው ከሰጡት ውስጥ አንዱ ተስፋዬ ሳህሉ "አባባ ተስፋዬ " ነበሩ ። እሳቸውም ለአዲስ አመት የእንቁጣጣሽ አበባ ስለው በየሹማምንቱ ቤት በማዞር ሀምሳ ብር ይሰበስቡና ወዴት ነህ የሚለው ጥያቄ እንዳያስጨንቃቸው ሆን ብለው ብርድ ልብስ ቀደው ላሰፋ ነው ።  በሚል ሰበብ ከቤት ይወጣኑ ከአንድ ጣልያናዊ ሹፌር ጋር ተነጋግረው በትሬንታ ኳትሮል ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ ።

አጠያይቀውም ቃል የገቡላቸውን ሰዎች ያገኙና በአስራ አራት አመታቸው የሙዚቃ ትምህርታቸውን ይጀምራል ። ከትምህርታቸው ጋር አንድ ላይ ማደርያና የኪስ ገንዘብ ጭምር ይሰጣቸው ነበር ።  በወቅቱ ከእሳቸው ጋር አብረው ከነበሩት ሙዚቀኞች መሀል የሳክስፎኑ ንጉሥ ጌታቸው መኩሪያ አንዱ ናቸው ። ስድስት አመት በዚህ ሁኔታ ካሳለፉ በኋላ የጃንሆይ  25ኛ የብር ኢዩቤልዩ በአል ምክንያት በማደረግ የአሁኑ ብሄራዊ ቴአትር የቀድሞ ቀ. ኃ.ስ ቴአትር ቤት ሲቁቋም ከተመረጡት አስራ ሶስት ሙዚቀኞች መካከል አንዱ በመሆን መስራች ሆኑ ።

በአርመናዊው አስተማሪና አለቃቸው ሙሴ ነርሲስ በምግባራቸውም ሆነ በትምህርት አቀባበላቸው የሚደነቁት አርቲስት መርዓዊ ከሙሴ ነርሲስ ህልፈት በኋላ የሙዚቃ ክፍሉን ተረክበው ለሰላሳ አመታት በአለቃነት አገልግለዋል። በዚህም ወቅት ለአርቲስት ምኒልክ ወስናቸው ፣  ለመልካሙ ተበጀ  ፣ ጠለላ ከበደ ፣ ፍቅርተ ደሳለኝ . . .  ለበርካቶች ግጥምና ዜማ ደርሰዋል ። ሙዚቃ አቀናብረዋል ። ከነዚህም ውስጥ የምኒልክ ወስናቸው የእንጆሪ ፍሬ፣ ትዝታ አያረጅም፣ስኳር ስኳር፣ አፈር አትንፈጊኝ፣ በምድረ ሱዳን ያለሽው ፣ ጥቁሯ ጽጌረዳ፣ የመልካሙ ተበጀ፣ ብእር ብእር ፣ ሰላም ጤና ይስጥልኝ፣ ንቢቱ፣ የፍቅርተ ደሳለኝ ልማት ልማት ሌሎችም ይገኙበታል ።

ከዚህም ባሻገር ከ200 የማያንሱ አብዮታዊ  መዝሙሮችን፣ ለሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እና ለሌሎችም በርካታ ታዋቂ ቴአትሮች ማጀቢያ ሙዚቃዎችን ደርሰዋል ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብም የመጀመርያ የሆነውን የክለቡን መዝሙር የሰሩት አርቲስት መርዓዊ ስጦት ናቸው ።  በአፄ ኃይለስላሴ ፣ በዘመነ ደርግ እና በዘመነ ኢህዲግ ጊዜ በተሰራው የኢትይጵያ ህዝብ መዝሙር ላይ የጋሽ መርዓዊ ትንፋሽ ተቀርጿል! ዜማው በሚሰራበት ጊዜም ኦርኬስትራውን የመምራትና የማስተባበር ስራውን የሰረት ጋሽ መራዊ ስጦት ናቸው ። 

በሙያው All Black People Music Festival ጨምሮ በናይጄሪያ ፣  በግብጽ በሱዳን ፣ በቻይና በራሺያ ፣ በአሜሪካ እና ሌሎችም ሀገራት ሀገሩን ወክሎ ተሳትፈዋል ። በአሜሪካ ሀገርም ከሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ ጋር በመሆን አምባሰልና ትዝታ ለትውልድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲተላለፍ በካሴትና በሲዲ አስቀረጸዋል  ። ለዚህና መሰል አስተዋጽኦ በተለያዩ ጊዜያት ሽልማትን አግኝተዋል ።

★ ከጃንሆይ የማበረታቻና የመጻህፍት ሽልማት

★ በደርግ ጊዜ በማስታውቂያ ሚኒስትር የምስጉን ሰራተኛ ወርቅ ተሸላሚ።

★ የአለም አቀፍ ጎልድ ሜርኩሪ ሽልማት (ሽልማቱ አለማቀፋዊና ትላልቅ የአለም መሪዎችን ጨምሮ ሳይንቲስቶችና ምሁራን የሚሸለሙት ነው )

★ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር  የወርቅ ሽልማት

★ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ማህበር የክብር ሽልማት ።

★ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር (ባህል ማዕከል) የክብር ዋንጫ ተሸላሚ።

★ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ የክብር ሜዳሊያ ሽልማት ጥቆቶቹ ናቸው።

ጋሽ መርዓዊ ጡረታም ከወጡም በኋላ ከሙዚቃው ሳይርቁ እስከ ቅርብ ጊዜ ከብሄራዊ ቴአትር ደጅ አይጠፋም ። የልብ ህመም አጋጥሞቸው የትንፋሽ መሳሪያ መጫወት እስከተከለከሉበት ጊዜ ድረስ ክላርኔታቸውን ይዞው መገኘት ባለባቸው ቦታ ሁሉ እየተገኙ ህዝብን ያስደስቱ ነበር ። በህይወታቸው ከኦርኬስትራው ተነጥለው በየትኛውም ምሽት ክለብ ሰርተው አያውቁም  ። በተሰጥኦ ያምናሉ ። አዳዲስ ወጣቶች በመጡም ጊዜ ካሉበት አድኖ በማግኘት እና በማበረታታት ይታወቃሉ።  

አርቲስት መርዓዊ ስጦት ባላቸው ጊዜ ሁሉ ባለተሰጦ ልጆች በማደን ችሎታቸውን እያደነቁ ፣  እየመከሩ የሚያበረታቱና ምን አይነት አርቲስት መሆን እንዳለባቸው ምሳሌ  በመሆን ጭምር የሚደግፍ የሙያ አባትም ጭምር ናቸው ! ለዚህም "የአለም አቀፍ ሜርኩሪ" ሽልማታቸው ወጣት ባለሙያዎች ባዩት ጊዜ እንዲበረታቱበትና እንዱነሳሱበት በማሰብ በስጦታ መልክ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ዋና ስራ አስኪያጅ ቢሮ እንዲቀመጥ አስረክበዋል ።

ሆኖም የኢትዮጵያ የሚዚቃ ወርቃማ ዘመን ባለውለታ አርቲስት መርዓዊ ስጦት ለዘመናት የኖሩበት መኖሪያ ቤት በቅርቡ ሊፈርስ እንደሆነ ተነግሯቸዋል ። ሆኖም 40/60 ኮንዶሚኒየም ምዝገባ በነበረበት ወቅት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተመዝግበው ሙሉ ክፍያ ፈፅመው ቤቱ ያልተሰጣቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ የሚመለከተው አካል ጋር በተደጋጋሚ አቤት ቢሉ ሰሚ አጥተው እጅጉን አዝነው ይገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር ፣ የኢትዮጵያ ባህል እና እስፓርት ሚኒስትር ለእኚ ባለውለታ ለሀገር የዋሉትን ውለታ ተመልክቶ ለከፈሉት ክፍያ ተገቢውን ምላሽ ከከተማ መስተዳደሩ ያገኙ ዘንድ ጥሪ ለማስተላለፍ እወዳለሁ !

ባለውለታን ማክበር ነገ ባለውለታ ዜጋን ማፈራት ነውና ባለውለቶቻችንን እናክብር !!!

ታሪኩ ዘውዱ
ከካናዳ 🇨🇦

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የድምፃዊ ንዋይ ደበበ እና የአይዳ ሐሰን ወንድ ልጅ የሆነው ሰላም ንዋይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በጋብቻ ተሳስረው አሜሪካን አገር ለረጅም አመት የኖሩት ንዋይና አይዳ ከቅርብ ዓመታት በፊት በይፋ መለያየታቸውን ቢገልፁም እንደ ቤተሰብ ብዙም አልተራራቁም። በትዳር ሕይወታቸው ፅናት የተባለች ሴት ልጅና ሰላም የተባለ ወንድ ልጅ በጋራ ያፈሩት ንዋይና አይዳ ልጆቻቸውን ያሳደጉት ቨርጂንያ ውስጥ ሲሆን፣ ሰላም ከጊዜ በኋላ በገጠመው የጤና እክል የተነሳ ሕክምና ሲከታተል ቆይቷል። በተለይ የኩላሊት ኢንፌክሽን ተጠቂ በነበረበት ሰዓት አንድ ኩላሊት እናቱ አይዳ ሰጥታው ንቅለ ተከላ ማድረጉ ይታወሳል።

ከልጅነቱ ጀምሮ ተጨዋች፣ ሳቂታ እና ቀልድ የሚወድ ተወዳጅ ልጅ ነበር ትምህርቱን ተከታትሎ ያጠናቀቀው እዚያው አሜሪካን አገር ሲሆን፣ ሲበዛ አዛኝ ልብ የነበረውና ሰዎችን መርዳት የሚያስደስተው ሰላም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #neway_debebe