Waliya Entertainment
287 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የማስተዋል እያዩ እንዚራ አልበም በአሪፍ ዝግጅት ተጠናቀቀ።

በድምፅ ችሎታው በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ እንዚራ የሚለውን አልበሙን ከለቀቀ በኃላ በብዙዎች ዘንድ መልካም ምላሽ ማግኘቱ ይታወቃል። አልበሙ በበርካቶች ዘንድ መወደዱን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ጋዝ ላይት ክበብ በርካታ አንጋፋና ጀማሪ ሙዚቀኞች በተገኙበት በአሪፍ ሁኔታ ተመርቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #mastewal_eyayu
September 3, 2024
September 6, 2024
ሴሊና ጎሜዝ ስሟ ከዝነኛ ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

ሴሊና በድምጻዊነት፣ በተዋናይነት እና በሥራ ፈጣሪነቷ ባስመዘገበቻቸው ስኬቶች የተነሳ ወጣት ቢሊየነር መሆኗ ተዘግቧል። እንደ ብሉም በርግ ዘገባ ከሆነ የ32 ዓመቷ ተዋናይት እና ድምጻዊት 1.3 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በማካበት የዝነኛ ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ስሟ ተካትቷል።

የሀብት ምንጯን ሲገልጽም ከአምስት ዓመት በፊት ያቋቋመችው የመዋቢያ ዕቃዎችን ከሚያመርተው ኩባንያ ጋር የተያያዘ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ ድርጅትም የ1 ቢሊዮን የአክስዮን ድርሻ አግኝቷል ሲል መጽሔቱ ገምቷል።

'ሬር ቢውቲ' የተሰኘው ይህ ብራንድ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ ስኬትን ያስመዘገቡ የመዋብያ ምርቶችን የሚያቀርብ ሲሆን እስከ የካቲት ወር ባሉት 12 ወራት ብቻ 400 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ሽያጭ ማስመዝገቡም ተጠቅሷል።

ድምጻዊቷ ባለፈው ዓመት በኢንስታግራም በርካታ ቁጥር ተከታይ ካላቸው ሴቶች መካከል ቀዳሚዋ ስትሆን በኢንስታግራም ብቻ 424 ሚሊዮን አድናቂዎች እንዳሏት ተዘግቧል ይህም ከቴይለር ስዊፍት እና ከካይሊ ጄነር ቀዳሚ ሲያደርጋት ከክርስትያኖ ሮናልዶ (638 ሚሊዮን) እና ከሊኦኔል ሜሲ (504 ሚሊዮን) በመቀጠል ሦስተኛዋ ዝነኛ ነች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Selina_gomez
September 7, 2024
September 7, 2024
September 7, 2024
September 7, 2024
የሙዚቃ ባለሞያ ብሌን ዮሴፍ በNBC ታለንት ሾው ብቅ ብላለች።

ድምፃዊት እና የሙዚቃ ባለሞያ ብሌን ዮሴፍ ከሶስት ወር በኃላ ብቅ ብላለች ከዚህ ቀደም በሙዚቃ ዳኝነት በኮካ ኮላ ሱፐር እስታር እንዲሁም በፋና ላምሮት በዳኝነት አገልግላለች፡፡
በፋና ላምሮት ቆይታዋ ከምዕራፍ ሁለት ጀምሮ እስከ ምዕራፍ አስራ ስድስት በየምዕራፎቹ እንዲሁም የአራተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ድረስ በዳኝነት በፋና ላምሮት ቆይታ አድርጋለች፡፡
ከሶስት ወር ቆይታ በኃላ በNBC ታለንት ሾው በተዘጋጀው አራተኛው ምዕራፍ ጳጉሜ 1/2016 በምሽት ሁለት ሰዓት በተደረገው ውድድር በዳኝነት ብቅ ብላለች፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #blen_yosef
September 7, 2024
September 8, 2024
19 ዓመት በባይተዋርነት የተሰቃየው ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጾ

የተወዳጁ ድምፃዊ ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጾ እያንዳንዱ የሙዚቃ ክሩ እጅግ አሳዛኝ አስተካዥ በቁዘማ የሚሰሙ አስለቃሽም ናቸው ። አንድ ጓደኛዬ እንዲህ አለኝ" የአሌክስ ዘፈን ወጥ እየሰራህ ካዳመጥከው ድስቱ ያራል" አለኝ ። ለምን? ስለው "በትዝታ አክናፍ ስለ ሚወስድህ "አለኝ::

ሕይወት ውጣ ውረድዋ ብዙ አድካሚ ነው ። አንዴ ሞላው ስትል ፤አንዱ ይጎላል ከፍታ እና ዝቅታ አንዱ የፈተና መድረክ ናቸው፡፡ ካለፍናቸው ጀግና ልባም በዛ ላይ ብቁ አስተዋይ በሁሉም ነገር የደነደነ የመሸከም ጫንቃ ይሰጥሀል፡፡ የመሻገርያ ቁልፎችን ፈለጋ ስትዳክር በመጨረሻም ሲገኙ ያነቁሀል፡፡

አሌክሶ ላይ ያንን ተመልካቻለሁ ፤ ያለፈበትን ሕይወት ሕመም ሲያወጋው እጅግ በተሰበረ ልብ ነው። ሀገሩን እያሰበ ያንን ጭንቀት ጊዜ ወደ ኃላ ተስቦ አይቶ በሆድ ይፍጀው ስሜት " ማን እንደ ሀገር "ሲል ተደጋጋሚ ጊዜ ይገልፃል፡፡ይህን ስሰማ ባይተዋር የተሰኘ ሙዚቃ ድቅን ይልብኛል ።

አለማየሁ ደመቀ ይህንን ሕይወት ውጣ ውረድ ቀድሞ አስቦ ነው የሰጠው ብዬ ከራሴ ጋር ሙግት ፈጥራለሁ። ምክንያቱም የዛሬ ቃለ ምልልስ የነበረን ነጐር ሲያወጋ "ያ" ነው የመጣልኝ፡፡

ከዛሬ 19 አመት በፊት እጅግ ዝነኛ የነበረ ሰው ፤ ከሀገር ውጪ ለሙዚቃ ስራ ወደ ባህር ማዶ ሲሄድ ህመም አጋጠመው ። አሌክስ ከህመሙ ጋር እየታገለ እና በተለያዩ ምክንያት ለ19 አመት በህመም እና በናፍቆት ሲሰቃይ ቆይቷል፡፡

"እኔ እና ታደለ ሮባ አንድ ቤት እንኖር ነበር እኔ ስታመም በዛን ጊዜ የቆጠበውን አንድ ሺህ ብር ብዙ ነው እሱን አውጥቶ አሳክሞኛል" ሲል ከ ታደለ ጋር የነበራቸውን ወዳጅነት አንስቷል፡፡

Telegram - https://t.me/waliyaentmt
September 9, 2024
የያሬድ ሹመቴ የዓመቱ ምርጦች

ምርጥ ጋዜጠኛ - Elias Meseret
ምርጥ ፖድካስት - Dawit Tesfaye ደጃፍ ፖድካስት
ምርጥ አልበም - Mastewal Eyayu እንዚራ
ምርጥ ድምጻዊት - YEMa
ምርጥ ድምጻዊ - Aschalew Fetene

የእርሶስ እነማን ናቸው?

እንኳን አደረሳችሁ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
September 9, 2024