ሴሊና ጎሜዝ ስሟ ከዝነኛ ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ
።ሴሊና በድምጻዊነት፣ በተዋናይነት እና በሥራ ፈጣሪነቷ ባስመዘገበቻቸው ስኬቶች የተነሳ ወጣት ቢሊየነር መሆኗ ተዘግቧል። እንደ ብሉም በርግ ዘገባ ከሆነ የ32 ዓመቷ ተዋናይት እና ድምጻዊት 1.3 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በማካበት የዝነኛ ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ስሟ ተካትቷል።
የሀብት ምንጯን ሲገልጽም ከአምስት ዓመት በፊት ያቋቋመችው የመዋቢያ ዕቃዎችን ከሚያመርተው ኩባንያ ጋር የተያያዘ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ ድርጅትም የ1 ቢሊዮን የአክስዮን ድርሻ አግኝቷል ሲል መጽሔቱ ገምቷል።
'ሬር ቢውቲ' የተሰኘው ይህ ብራንድ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ ስኬትን ያስመዘገቡ የመዋብያ ምርቶችን የሚያቀርብ ሲሆን እስከ የካቲት ወር ባሉት 12 ወራት ብቻ 400 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ሽያጭ ማስመዝገቡም ተጠቅሷል።
ድምጻዊቷ ባለፈው ዓመት በኢንስታግራም በርካታ ቁጥር ተከታይ ካላቸው ሴቶች መካከል ቀዳሚዋ ስትሆን በኢንስታግራም ብቻ 424 ሚሊዮን አድናቂዎች እንዳሏት ተዘግቧል ይህም ከቴይለር ስዊፍት እና ከካይሊ ጄነር ቀዳሚ ሲያደርጋት ከክርስትያኖ ሮናልዶ (638 ሚሊዮን) እና ከሊኦኔል ሜሲ (504 ሚሊዮን) በመቀጠል ሦስተኛዋ ዝነኛ ነች።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Selina_gomez