Waliya Entertainment
291 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
3ኛው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 22/2016 (አዲስ ዋልታ) የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የህልፈት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ለ3ኛ ጊዜ በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በ11 ዘርፍ ድምፃዊያንን እጩ ያደረገው ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ የምርጫ ሂደቱ የህዝብ እና የዳኞችን ምርጫ ያማከለ ነው ተብሏል።

አርቲስቱ በህይወት በነበረበት ጊዜ የአፋን ኦሮሞ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላይ ትልቅ አሻራ ያለውና ግጥምን ከዜማ አዋህዶ በርካታ ጉዳዮችን እያነሳ ያቀነቀነ ወጣት አርቲስት ነበር፡ በስራዎቹም በርካታ ነጠላ ዜማ እና አልበሞችን ለህዝብ አድርሷል።

የአርቲስቱን ህልምና ራዕይ ከግብ ለማድረስ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በዚህም በአርቲስቱ ስም በየበጎ አድራጎት ስራ እና ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

በዛሬው እለት የተዘጋጀው መርኃ ግብርም የአርቲስቱን 4ኛ ዓመት መታሰቢያ እና 3ኛ ዙር ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ምክንያት በማድረግ ነው።

በመርኃ ግብሩ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ አርቲስቶች፣ የአርቲስቱ ቤተሰብና አድናቂዎች ተገኝተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ 3ኛ ግዜ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።

በ11 ዘርፍ በርካታ የጥበብ ባለሞያዎች እጩ የሆኑበት አዋርድ የምርጫ ሂደት የህዝብ እና የዳኞች ድምፅን ያማከለ ነበር ተብሏል።

በተካሄደው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 4ኛ ዓመት መታሰቢያ እና 3ኛ ዙር አዋርድ ላይ፥ በአመቱ ምርጥ ሙዚቃ ዘርፍ ድምፃዊ ዮሳን ጌታሁን አሸናፊ ሆኗል።

በምርጥ ባህላዊ ሙዚቃ ዘርፍ ድምፃዊ ታደለ ገመቹ እንዲሁም በአመቱ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ ዘርፍ ድምፃዊ ጉቱ አበራ ሲያሸንፍ፥ ወደ ፊት ተስፋ የተጣለበት ድምፃዊ ያሲን አደም፥ ከመሀሪ ብራዘርስ ባንድ ጋር በመሆን የመድረክ የሙዚቃ ስራ አቅርቧል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
እነሆ የዜናውን ቁልፍ ነጥቦች በአጭሩ:

1. ቴዲ አፍሮ በዱባይ Coca-Cola Arena ውስጥ ታላቅ ኮንሰርት አቅርቧል።

2. ኮንሰርቱ በጣም ኃይለኛ, ልዩ እና ፍቅር የሞላበት ነበር፤ እውነተኛ ኢትዮጵያዊነትን ያሳየ።

3. የስታዲየሙ አዘጋጆች በኢትዮጵያውያን ተመልካቾች ፍቅር, ትህትና እና ስነ-ስርዓት ተገርመዋል።

4. ኢትዮጵያውያን ከዓለም ዙሪያ እና ከኢምሬትስ ተሰብስበው በ45°C ሙቀት ዱባይን አድምቀዋል።

5. ይህ ኮንሰርት በቅርብ ጊዜ በCoca-Cola Arena ከተካሄዱት ሌሎች ኮንሰርቶች (እንደ Jason እና Xzibit) የበለጠ ተመልካች ያሰበሰበ ነበር።

6. ኮንሰርቱ ፍቅር, መተሳሰብ እና መከባበር የታየበት ሆኗል።

7. ቴዲ አፍሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ወክሎ በCoca-Cola Arena የተጫወተ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ሆኗል።

8. ኮንሰርቱ በ30-06-2024 ተካሂዶ ታሪካዊ ቀን ሆኖ ተመዝግቧል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃችሁና ይፈለጋል!

በቅርቡ በሚከናወነው ኮራ አዋርድ በባህላዊ ሙዚቃ ዘርፍ ከተለዩት የመጨረሻ ሁለት ተወዳዳሪዎች አንዱ ድምፃዊ አስቻለው ፈጠነ ሆኗል። ለዚህ ደሞ የናንተ የሀገሩ ልጆች ድምፅ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ውድድሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአሸናፊነት ለመቋጨት የሽልማት ድርጅቱ ይፋ ባደረገው መሠረት የመጨረሻ ዙር ትንቅንቁ ዛሬ ተጀምሯል። ያገር ልጆች ሁሉ አሁንም ድምፃችሁና ጽናታችሁ ይፈለጋል!

ኢትዮጵያውያን በምናውቀው የአልሸነፍ ባይነት ወኔያችን ቀጣዩን ሊንክ በማስፈንጠርና ምርጫ በማድረግ ማሳረጊያውን እናሳምር።

https://zekin.me/kora-awards-2024/ASCHALEW19?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR0pmyH-WTfoPuO1WxkWRkXNBzG4hMDZuYkdQDbs4ts2jCeeKVtxuypyxRc_aem_X0Kcsc98xWdvNdI1BgUNvw
1
"እርድና ከኤርትራውያን እናትና አባቷ ሰባተኛ ውስጥ ከተወለደች እነሆ 48ተኛ አመቷን አስቆጠረች። ፍቅር ሐይማኖት እንደማይገድበው ኦርቶዶክስ ሚስቱ ምስክር ነች። ወንድ ልጅ ገግሞ ሰርቶ ገንዘብ ማግኘት እንዳለበት አምስት አመት ከስድስት ወር የፈጋባት የሳውዲዋ ጅዳ ትመስክር። ሰው ገንዘብና ዝናን ሲያገኝ የነበረበትን መርሳት እንደሌለበት በጉስቁልና ጊዜ የደረሰላቸው የአማርኛ መምህሩን ሒዱና ጠይቋቸው።ሰለ ግጥምና ዜማ ችሎታው አራቱን አልበሞቹን ለጆሮዎቻቹ ጋብዛችሁ መልሱን አድምጧቸው። ስለ ጨዋታ አዋቂነቱ ከስሩ የማይጠፉት ታዋቂ ሙዚቀኞችን ጠይቋቸው።

አብዱ ኪያር ማለት ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ቆሎ ውስጥ እንዳለ ለውዝ ማለት ነው። ቆሎው ሌሎች ሙዚቀኞች ናቸው። ቆሎውን ያለ ለውዙ መቆርጠም ትችላለህ። ለውዙን ስትጨምርበት ግን ቆሎው ጣፍጦህ እንድትቆረጥም ያደርግሃል ። ሁሉም ሰው እንዳጋጣሚ ከቆሎው ውስጥ ቀድሞ የሚቆረጥመው ለውዙን መሆኑ ደግሞ ይገርማል።

አስር አራዳ አውቃለው ዘጠኙ አብዱ ኪያር ነው!

Via Fitse coffee 👌
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👏1
የሀገር ልጅ እንዲህ ሲሳካለት ደስ ይላል!!

#Ethiopia : በየትኛውም መስክ ላይ ያለ የሀገር ልጅ እንዲህ ሲሳካለት፣ ከፍ ሲል፣ በስራው ሲከብር ደስ ይላል። መልካም ግዜ ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች!

#Rophnan #ChrisBrown
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት ተመልካች ያገኙ 10 የሳምንቱ ሙዚቃዎች

1ኛ አብዱ ኪያር (አይዞ) 🎶 1,018,765 እይታ
2ኛ አብዱ ኪያር (ገለመሌ) 🎶 954,657 እይታ
3ኛ አብዱ ኪያር (ፓ! ፓ! ፓ!) 🎶 833,059 እይታ
4ኛ አብዱ ኪያር (ባይ ባይ) 🎶 532,619 እይታ
5ኛ አንዱዓለም ጎሳ (ቢሊሌ) 🎶 480,266 እይታ
6ኛ አብዱ ኪያር (እንደምነሽ) 🎶 367,661 እይታ
7ኛ ሮፍናን (ሸግዬ) 🎶 344,192 እይታ
8ኛ አብዱ ኪያር (ሰውዬው) 🎶 331,458 እይታ
9ኛ ናሆም መኩሪያ (ባዳ ባዳ) 🎶 307,548 እይታ
10ኛ አብዱ ኪያር (ቡቡዬ) 🎶 306,037 እይታ

🎶 በሳምንቱ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት የታዩ ሙዚቃዎችን በትክክለኛ ዳታ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ምርጥ አስር ሙዚቃ ሰንጠረዥ ነው።

🎶 ቁጥሮች በሳምንት ውስጥ የጨመሩትን እይታ ብቻ ነው የሚያሳየው።

ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ተካ በማህበራዊ ገፅዋ ላይ እንዲህ ስትል ለተጠየቀችሁ ጥያቄ መልሳለች፡፡

"በጣም በብዙ ሰው የክለብ ባለቤቶችን ጨምሮ እየተጠየቅኩበት ካሉት ጥያቄዎች ውስጥ ክለብ መቼ ነው የምትመለሽው? ነው፡፡

ክለብ በመስራቴ አሁን ላለሁበት ደረጃ ደርሻለሁ ከ ሶሻል ሚድያ ቀጥሎ ከ እናንተ ከ ቤተሰቦቼ ጋር በደንብ ያስተዋወቀኝ ፡ እኔንም ቤተሰቦቼም ያስተዳደረን …ለተከታታይ ሶስት ዓመት ሰሰራው የነበረው በጣም የማከብረው የስራ ዘርፍ ቢሆንም ከ ፈጣሪ ጋር ከዚህ በኃላ ከ ክለብ ስራ አታገኙኝም፡፡ ስዚህም በፈጣሪ እገዛ እንጂ በኔ አይደለም እና ክብሩን መድሀንዓለም ይውሰድ፡፡እንቁላል ቀስ በቀስ………'' ስትል አሳብዋን በማህበራዊ ገፅዋ ላይ አድርሳለች ፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ሐምሌ 6 ሊደረግ የነበረው ኦሎምፒክ ኮንሰርት ለሐምሌ 13 ተዘዋውሯል።

ኦሎምፒክ ኮንሰርት በመባል ስያሜ የተሰጠው ከ15 በላይ አንጋፋ እና ጀማሪ ድምፃዊዎች የሚሳተፉበት በሌቭል ዋን ኢንተርቴይመንት ተዘጋጅቶ የነበረው ታላቁ ኮንሰርት በመስቀል አደባባይ ሐምሌ 6 ሊደረግ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ዝግጅቱ ወደ ሐምሌ 13 እንደተተላለፈ አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
በሮፍናን ኮንሰርት ሲጠበቅ የነበረው ክሪስ ብራውን ስራውን ሳያቀርብ ቀረ።

በየአመቱ በሰሜን አሜሪካ የሚካሄደው የኢትዬጲያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ዘንድሮም በጆርጂያ ግዛት በአትላንታ ተካሄዶ ያለፈው ቅዳሜ የተጠናቀቀ ሲሆን ከዛም ጎን ለጎን ከተከናወኑ የተለያዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች መሃል በጉጉት የተጠበቀው ሮፍናን እና ክሪስ ብራውንን በአንድ መድረክ ያጣምራል የተባለው ዝግጅት ቢሆንም ክሪስ ብራውን በምሽቱ ዝግጅቱን ሳያቀርብ ቀርቷል ።

ዋልያ ኢንተርቴይመንትም ከውስጥ አዋቂዎች መረጃውን ለማጣራት የሞከረ ሲሆን ክሪስ ብራውን በቦታው ላይ ተገኝቶ ለማቅረብ ቢዘጋጅም በተለያዩ ምክንያቶች ሰአቱ እስከ 9:00 PM ከመግፋቱ የተነሳ በጆርጅያ ግዛት ውስጥ ምንም አይነት ትላልቅ ዝግጅቶች ከዛ ሰአት በላይ መደረግ ስለማይችሉ በፖሊሶች ቁጥጥር ዝግጅቱ ሊቋረጥ ችሏል።

በዝግጅቱ ሮፍናን በአሪፍ መድረክ አያያዝ ለ 1:30 ያህል ሰአት ዝግጅቱን ያቀረበ ሲሆን ነገር ግን በአካልም ከክሪስ ብራውን ጋር ሳይገናኙ ቀርተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ተወዳጇ ድምፃዊት ሐመልማል አባተ በአዲስ ስራ ብቅ ልትል ነው !

ራያ የተሰኘ የሙዚቃ ቪድዮ ክሊፕ በቅርቡ እንደምትለቅ ይፋ አድርጋለች ። ግጥምና ዜማ ቢንያም ረዳኢ ሲሰራው ቅንብሩን አሌክስ ይለፍ ተጠቦበታል ።