Waliya Entertainment
291 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
በ1994 ዓ.ም የኤልያስ መልካ አሻራ ያረፈበት በሚክሲንግ፣ ቤዝ ጊታር እና አሬንጅመንት ድንቅ ብቃቱን ያሳየበት ለብዙዎቻችን ከሀገር ጫፍ እስከ ጫፍ 90's ላይ ከልጅ እስከ አዋቂ ትዝታ እንደ እሳት የሚጭር ድንቅ አልበም ነው።

ኢቫንጋዲ አልበም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ታትሞ ለገበያ የቀረበ ሲሆን Copyright አልበም በ CD ታትሞ ገበያ ያስጨነቀበት ጊዜ ነበር። የዚህ ሙዚቃ አልበም አርት እንደሚከተለው ሲሆን ሙሉ መረጃዎች ተቀምጠዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
2
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲዬ ከሞት ተረፈ

በቅርቡ ይለያል የተሰኘውን አልበሙን ለህዝብ አድርሶ በብዙዎቹ ዘንድ አድናቆትን ያተረፈው ድምፃዊ ቴዲዬ በቅርቡ ለሚያቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት አሜሪካ መግባቱ ይታወቃል።

ድምፃዊውም በአሜሪካ የጥቁሮች የነፃነት ቀን በሰፊው በሚከበርበት በ june 20 የሙዚቃ ቪዲዬ ቀረፃ ላይ በቦታው ላይ የነበረውን አከባበር በማስገባት እየቀረፀ በነበረበት ሰአት በቦታው ላይ በጋንግስተሮች መሃል በተነሳ ጠብ የሽጉጥ ተኩስ ተነስቶ በቀኑ ቦታው ላይ ከነበሩት ሰዎች 15 ሰዎች ሲቆስሉ 1 ሰው ሞቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_yo
👤 Abdu Kiar | አብዱ ኪያር
🎵 pee |
━━━━━━━━━━━━━━
➠ RELEASED: 2024
➠ GENRE: #Ethiopian
➠ TYPE: #Album
➠ TRACKS: 13
➠ FORMATS: #Mp3
➠ CHANNEL: @Waliyaentmt
━━━━━━━━━━━━
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Abdu_kiar #Album #Ethio_albums #Waliya_Entertainemnt
🔥1🙏1
"ዱርዬ ተሰብሰብ "

ከአመታት በፊት ተ/ሀይማኖት ፊትለፊት ያለው አንበሳ ጫማ መደብር ያለበት ህንጻ ሰፊ በረንዳ የጎዳና ተዳዳሪዎች መናሀሪያ ነበር ። እና እዚህ ቦታ ፌስታል ሙሉ ክትፎ ይዞ የሚመጣ አንድ ሰው ነበር ፨

ይህ ሰው ኬኔዲ መንገሻ ነው ፡፡ ኬኔዲ አንዳንዴ ነሸጥ ሲያደርገው ወደዛ ይሄድና ዱርዬ ተሰብሰብ እያለ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ በጊዜው ተ/ሀይማኖት ሱማሌ ተራ አካባቢ ዝነኛ ከነበረው ግዛው ክትፎ ቤት ገዝቶ ያመጣውን ክትፎ አብሯቸው እየተሻማ ይበላና ለያንዳንዳቸው የሻይ ሰጥቶ በብርቱካንማ ሬኖ መኪናው ይሄዳል ።
.......
አስገራሚው ነገር ኬኔዲ የትኛውም ታዋቂ ሰው የማያደርገውን ይህን መሳይ ነገር ሲያደርግ. .. በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ዝነኛ ከነበሩ አርቲስቶች መሀከል አንዱ ነው ። ሆኖም ዝናው አንድም ቀን ትከሻውን አጉብጦት አያውቅም ።
.......
አንድም ቀን በኩራት ልቡ ሳያብጥ ፡ አንድም ቀን ላይ ሆኖ አድናቂዎቹን ቁልቁል ሳያይ ፡ እንደጠዋት ፀሀይ ብልጭ ብሎ አፍታም ሳይቆይ ይህችን ምድር ተሰናብቶ ሄደ ።
RIP
የሰውነት ጥግ ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከኤሮስፔስ ወደ ሙዚቃ !

ሙላቱ አስታጥቄ ለትምህርት ወደ አውሮፓ ሲያመራ እድሜው 20 እንኳን አልሞላውም ። ከጥሩ ቤተሰብ ነው የተገኘው የሀብታም ልጅ ነበር ማለት እንችላለን ። በጥሩ ኢትዮጵያዊ ባህል እና ስነልቦና ያደገ ።
በ16 አመቱ በዌልስ ኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግ ማጥናት ጀመረ ። የሚማርበት ዩንቨርስቲ ተማሪዎቹ ከመደበኛ ትምህርታቸው በተጨማሪ ሌሎች ትምህርቶችን በትርፍ ጊዜያቸው እንዲማሩ ያበረታታል ።
እናም ወጣቱ ሙላቱ አስታጥቄ ሙዚቃን ማጥናት ጀመረ ። እንድያውም ከነአካቴው ስለጠፈር ምርምር ትምህረት ይቅርብኝ ብሎ ሙሉ ለሙሉ ሙዚቃው ላይ አተኮረ ። ወደ ለንደን አምርቶ በትሪኒቲ ኮሌጅ ሙዚቃን አጠና ። ከዛም ለንደን ላይ በጃዝ ሙዚቃዎች መሳተፍ ሲጀምር ቀጠል አድርጎም ሙዚቃዎችን ማጥናት ተያያዘ ። አሰብ አድርጎ ደግሞ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በአለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ እንደሚቻል ያምናል እናም በትምህርት ልቆ ለመገኘት ወደ አሜሪካ ተጉዞ በቦስተን በርክሌ ሚዩዚክ ኮሌጅ በመማር የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ።

በ60ዎቹ ከላቲኖች ጋር በመሆን ''Afro Latin jazz'' ቁጥር 1እና 2 በአሜሪካ ሀገር ሰራ ።
በ1969 እኤአ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ እጅግ ተወዳጅነትን ያገኘበትን ስራ አጥንቶ ጨርሶ 1972 እኤአ ላይ አሜሪካን ሀገር በማምራት አስቀረፀ። ይህ ስራ የላቲን ፣የአፍረካ ፣ፈንክ እና ሌሎችንም አለም አቀፍ ሙዚቃዎች ስልት አዋህዶ የተቀናበረ ኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ነው ። ''ሙላቱ ኢትዮጵያ '' የተሰኘ ኢትዮ ጃዝ አልቀም ተሰርቶ እጅግ ተወዳጅነትን አገኘ ።

ይህ ስራ ከተለቀቀ የፊታችን ሰኞ 52ኛ አመቱን ይያዛል ።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt