Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የሐረሪ ባህላዊ የሙዚቃ ኖታ : የጥናት መፅሐፍ

#Ethiopia | የሐረሪ ባህላዊ የሙዚቃ ኖታ ላይ ትኩረት ያደረገ የጥናት መፅሐፍ ተመርቋል፡፡

የጥናት መፅሐፉን ያዘጋጁት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም የሐረሪ ክልል ባህል ቅርስ እና ቱሪዝም ቢሮ ናቸው፡፡

የሐረሪ ብሔረሰብ ተዝቆ የማያልቅ ቱባ የስልተ ምት እንዲሁም የማህበራዊ ክንዋኔ ባለቤት መሆኑን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሰርፀ ፍሬስብሃት ተናግረዋል፡፡

መፅሐፉ ይህንን ሐብት አጥንቶ መሰነድን ዓላማ ማድረጉንም ምክትል ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ በበኩላቸው ሐረር የበርካታ የጥበብ ባለሞያዎች መፍለቂያ መሆኗን ጠቁመው የጥናት መፅሐፉ የክልሉን ባህላዊ ሙዚቃ በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ሚና እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ታሜ እንደዋዛ 6 ዓመት ሞላው

የዛሬ 6 ዓመት በዚች ቀንና በዚች ስአት ነበር ድምፃዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት የተለየን:: ድምፃዊ ታምራት ደስታ ቀኑ ረቡዕ እለት ሚያዚያ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ነበር ። ታሜ በተወለደ በሰላሳ ዘጠኝ (39) አመቱ በህክምና ስህተት ከዚህ አለም በሞት የተለየው:: ታሜ ሃያ አንድ (21) አመታት በቆየበት ስኬታማ የሙዚቃ ታሪኩ አራት (4) ያህል አልበሞችን እና ከዘጠኝ (9) ያላነሱ ነጠላ ዜማዎችን አበርክቷል::

የምንጊዜም ምርጡ ድምጻዊ ታምራት ደስታ ከድምጻዊነቱ ባሻገር ቤተሰቡን (ልጆቹን) አክባሪ ማህበራዊ ህይወትን የሚያውቅ: ቁም ነገረኛ እና አስተዋይ ነበር::ታምራት ለብዙዎቻችን አረፈ እንጂ አልሞተም ዘመን በማይሽራቸው ተወዳጅ ስራዎቹ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል::ነፍስህን ከደጋጎቹ ያድርግልን ታሜ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
መልካም ልደት ዲጄ ቤቢ🎉

በተለያዩ የመድረክ ፣ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች የምናውቀው እንዲሁም የአዲስ ሙዚክ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነው ዲጄ ቤቢ ዛሬ ልደቱ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ዝክረ ጥላሁን ገሠሠ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨
በዛሬው ዕለት ታሪክ ሲወሳ ሚያዚያ 11 : 2001 ክቡር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት ቀን ነበር፡፡

በወሊሶ ከተማ መስከረም 17 ቀን 1933 ዓም የተወለደው ጥላሁን ገሠሠ በ1949 በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ ፡፡
ከ1950ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት እስከ 1960ዎቹ አጋማሽ ድረስ በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ አጃቢነት አያሌ ድንቅ ዘፈኖችን በመጫወት እውቅናን አትርፏል ።

ያልዘፈነበት ጉዳይ የለም የሚባልለት ጥላሁን ገሠሠ ድንበር የማይገድበው ፍቅር፣ የሀገር ክብር ገላጭ እንዲሁም መካሪ ስራዎቹ ለዚህ ተጠቃሽ እንደሆኑ ይነገራል ።

ጥላሁን በሚያዘያ ወር 1985 አንገቱ ላይ በስለት የመወጋት አደጋ ደርሶበት እንደነበር ነገር ግን ይህ በድምጻዊነት ከመቀጠል አላገደውም ።

በኢትዮጵያ የዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ደማቅ ታሪክን ያሳለፈ፣ ትውልድ ተሻጋሪ፣ ተደማጭ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያበረከተው ድምጻዊ የክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ በተወለደ በ68 አመቱ በዛሬው ዕለት ማለፋን ታሪክ ይዘክራል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምጻዊ ሳሚ ዳን ዘመናዊ የሙዚቃ ስቱዲዮ ገነባሁ አለ::

በሬጌ ሙዚቃ ተጫዋችነቱ የሚታወቀው ሳሚ ዳን ስቱዲዮ አስገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን አሳውቋል።

ድምፃዊው የስቱዲዮና የቪዲዮ ቀረፃዎችን ማድረግ የሚያስችል ሩፍታፕ ሚውዚክ ሲል የሰየመውን ስቱዲዮ ግንባታውን አጠናቅቆ ማስመረቁን ገልጿል።

ድምፃዊ ሳሚ ዳን ስቱዲዮውን ለመገንባት ቀድሞውኑ ፍላጎት የነበረው ቢሆንም አዳዲስ ሙዚቀኞች ዘርፉን ለመቀላቀል በሚያደርጉት ሂደት ውስጥ እነርሱን ለመርዳት መንገዱ አስቸጋሪ መሆኑ በይበልጥ እንዳነሳሳው ይገልፃል።

የስቱዲዮ መገንባት ስራው የኮቪድ ወረርሽ በተከሰተበት ወቅት ቤት ውስጥ ተሞክሮ ጥሩ ውጤት እንዳገኘበት የሚናገረው ሳሚ ዳን ግንባታውን በፈጣሪ እርዳታና በመልካም ስዎች ትብብር እውን ሊሆን እደቻለም ያብራራል ።

አዲሱ ስቱዲዮ ሙከራ ተደርጎለት ሪከርድ ማድረግ የጀመረ ሲሆን በሁሉም የሙዚቃ ዘርፍ ስራዎችን እየከወነ ይገኛል።

ድምፃዊ ሳሚ ዳን አያይዞም ሌላኛው መልኬ የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም በመስራት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
የኮራ አዋርድን በሰፊ ልዩነት በመምራት ላይ እንደሚገኝ ድምፃዊ አስቻለው ፈጠነ አስታወቀ::

በቅርብ አሸናፊው በሚታወቀው የኮራ የሙዚቃ ውድድር አስቻለው በ47% ከመቶ ድምፅ እየመራ ይገኛል::

ድምፃዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ስለ ሆነው ሲገልፅ "ክቡራን የጥበብ ወዳጆቼ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ ሁለተኛውን ዙር የኮራ ዉድድርም በአንደኝነት በሰፊ ልዩነት እየመራን ነው" ሲል ፅፏል።

አስቻለው በቅርብ በሰራቸው ባህላዊ ሙዚቃዎቹ ከፍተኛ አድናቆት እያገኝ ነው::

ድምፃዊዉን ለመምረጥ https://www.koraawards.com/top40 መጠቀም ትችላላቹህ::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ሱልጣን ኑሪ (ሶፊ) የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 120ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስመልከት በልዩ ሁኔታ የተቀናበረ ሙዚቃን ለአምባሳደር ማሲንጋ አስረከበ።