Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ኢትዮ- ጃፓን የሙዚቃ ኮንሰርት ተካሄደ

#Ethiopia | በኢትዮጵያ እና በጃፓን የባህል የሙዚቃ ባለሙያዎች በጋራ በትናንትናው እለት በብሔራዊ ቴአትር የሙዚቃ ኮንሰርት ተካሂዷል።

እውቁ የጃፖን ኢትዮ አርት ክለብ (ኮዶራኒ ባንድ ) እና በተለያዩ ሀገራዊና የውጪ መድረኮች ላይ የሀገራችንን ባህላዊ መሳሪያዎችን በመጫወት የሚታወቀው ሞሰብ የሙዚቃ ቡድን በጋራ በመሆን በብሄራዊ ቴአትር የሙዚቃ ኮንሰርት አካሂዷል።

በኮንሰርቱ ላይ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ-ጥበብ ስነ-ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ብሩክ ተፈራ፣ በኢትዮጵያ የጃፖን እንዲሁም የሌሎች ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አማካሪው:- ከኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ባሻገር እንደነዚህ ያሉ እና መሰል ባህላዊና ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱንና የባህል ልውውጡን ይበልጥ የሚያጠናክሩ እንደሆነ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በግምባር ቀደምትነት ስሙ ከሚጠቀሰው ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠን ጨምሮ በርካታ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ስለ ጃፓን እንዳቀነቀኑ እና በጃፓን ባህል ዙሪያ እንደሰሩ እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ ጃፓናውያንም በኢትዮጵያ ባህል ዙሪያ በተለያየ ወቅት እንደሰሩ አስታውሰው ይህ የሚያሳየው የሁለቱ ሀገራት የእርስ በእርስ ግንኙነት ስር የሰደደ እንደሆነ ነው ብለዋል።

በኮንሰርቱም የሁለቱን ህዝቦች ታሪክ እና ባህል የሚገልፁ የሙዚቃ ስራዎች እንዲሁም ሁለቱ የሙዚቃ ቡድኖች የተጣመሩበት (የኮላቦሬሽን ሙዚቃ ) ስራዎች ለታዳሚያን ቀርበዋል።

@waliyaentmt
@waliyaentmt
@waliyaentmt
👍3
'የማነህ'? አልበም

#Ethiopia : በገና በዓል እንዲሁም በአስፋው መሸሻ ህልፈት ሳቢያ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብሩ የተራዘመው የድምጻዊት እየሩሳሌም አስፋው ሦስተኛ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ይፋ ተደረገ።

በመርሃ ግብሩ ላይ ድምጻዊቷ የሙዚቃ ስራዋ ይፋ መደረጉን አብሥራ፤ ከአድማጮች ጋር ያስተዋወቃት 'ሃሎ አዲስ አበባ' የተሰኘ ከአሥር ዓመታት በፊት የተሠራ ሙዚቃ በአዲስ መልክ ተሰርቶ በ'የማነህ' የሙዚቃ አልበም ውስጥ መካተቱን ገልጻለች።

ከአሥር ዓመታት በላይ ከአድማጭ ጋር ሳትገናኝ ለመቆየቷ ግጥም እና ዜማ የመሰብሰብ ሂደት እንዲሁም የስቱዲዮ በሥራ መጨናነቅ ምክንያት መሆናቸውን ድምጻዊት እየሩሳሌም አስፋው ተናግራለች። ይሁን እንጂ አልበሙ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት የሙዚቃ ድግስ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተነግሯል ።

በአውታር የሙዚቃ መተግበሪያ በታህሳስ ወር መጨረሻ የተለቀቀው 'የማነህ' የሙዚቃ አልበም 16 ነጠላ ዜማዎችን የያዘ ሲሆን ከጥቂት ጊዜ በኋላ አልበሙን በሲዲ የማሳተም እና ይፋዊ የአልበም የምርቃት መርሃ ግብር መታቀዱን የመድረኩ አዘጋጅ አብረሃም ግዛው ገልጿል።

'የማነህ' የሙዚቃ አልበም ብስራት ጋረደው፣ ምስክር አወል፣ ምዕራፍ አሰፋ፣ ቢኒያምር አምዱ፣ አብረሃም ኪዳኔ እንዲሁም ሌሎች አንጋፋ እና ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት እንደሆነም ተገልጿል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
1👍1
የተዐምር ግዛዉ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ

ግጥም እና ዜማ አብርሀም ዘዉዴ
ሙዚቃ ቅንብር እና ሚክሲንግ
ሚካኤል ሀይሉ
ማስተራንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
🎯 POSTPONED | ተራዝሟል

#Ethiopia | የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 9(February 17) በጊዮን አፍሪካን ጃዝ መንደር ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውና ሰፊ ዝግጅት የተደረገበት ዝነኞችን ይተዋወቁ (celebrity meet and great) ሁለተኛው መርሀግብር (ከክብር ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ) ጋር ሀገራችን በዛው ሳምንት በምታሰናዳው 43ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል!

ታዋቂ ኤቨንትስ meet the celebrities በተሰኘው መርሀግብሩ አንጋፋ ተወዳጅና በስራቸው ብሎም ባበረከቱት መልካም አስተዋፅኦ እውቅናን የተጎናፀፉ ዝነኞች ከአድናቂዎቻቸው ጋር የሚገናኙበትን ቅንጡ መድረክ በየጊዜው ያዘጋጃል::

ይህ መድረክ ታዋቂዎች በልካቸው የሚከበሩበት፣የሚሸለሙበትና ከአድናቂዎቻቸው ጋር የሚገናኙበት የታዳሚያንን ቀልብ የገዛ አጉዋጊ ዝግጅት ነው::

የዚህኛው ዙር እንግዳችን የክብር ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ እንደሆነ ይታወቃል::
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ታዋቂዋ ዘፋኝ ቬሮኒካ አዳነ የአሜሪካ ቆይታዋን አራዘመች።

ታዋቂዋና ተወዳጇ አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሙዚቃ ዝግጅቷን ከምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ስታቀርብ የነበረውን ዝግጅቷን የጨረሰች መሆኑን ያሳወቀች ቢሆንም ከአዘጋጆቹ ጋር በመነጋገር ለቀጣይ ሶስት ሳምንታት በማራዘም በ ፍሌም ላውንጅ ዝግጅቷን እንደምትቀጥል አሳውቃለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music