Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
"አዮ ኮ፣ ሐርሜ ኮ" ዘመን የማይሽረው ድምፃዊ ገቢ ኤደኦ

በዘጠናዎቹ ውስጥ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ከሚጋበዙ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ውስጥ የድምፃዊ ገቢ ኤደኦ ሙዚቃ ተጠቃሽ ነው። ዛሬ በፋስት መረጃ ተወዳጁን ሙዚቀኛ ገቢ ኤደኦን እናስታውሰው።

በአፋን ኦሮሞ ስለ እናት ከተቀነቀኑ በርካታ ዘፈኖች ውስጥ የአቢቶ ከበደ "Hadha koo" ስሜትን የሚኮረኩር እናት አጠገብ ሆና እንኳን የሚያስናፍቅ የማይጠገብ ሙዚቃ ነው። ሌላኛው ተወዳጅ ስለ እናት ከተዘፈኑ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ የገቢ ኤደኦ "አዮ ኮ" የተሰኘው ነው።

ገቢ ኤደኦ የተወለደው በዝዋይ ዱግዳ (ሐቡራ) ቢሆንም በህፃንነቱ ወደ እናት አባቱ ሀገር ለትምህርት ተብሎ አሰላ ከተማ ገባ። ለትምህርት ተብሎ አሰላ የገባው ገቢ ነፍሱ ወደ ሙዚቃ አደላች አሰላ ከተማም ሙዚቃ ለመስራት አመቺ እድል ሆኖለት። ሙዚቃን በአሰላ ከተማ "ትግል ፍሬ" በተባለ ግሩፕ የጀመረው ገቢ ኤደኦ ጭላሎ ኪነት፣ ፖሊስ የተባሉ የሙዚቃ ቡድኖችን እየተቀላቀለ እስከ ሮሃ ባንድ ድረሰ የሙዚቃ ችሎታውን እያሳደገ ደርሷል።

ገቢ ኤደኦ የመጀመሪያ አልበሙን የአማርኛ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ያቀረበ ሲሆን በ1984 ዓ.ም የአፋን ኦሮሞ አልበም ለአድማጭ አድርሷል።

ገቢ ኤደኦ የአማርኛ አልበም ጨምሮ አራት ሙሉ አልበም እና በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ሰርቷል። ድምፃዊ ገቢ ኤደኦ አሁንም ሙዚቃን እየሰራ ሲሆን ተተኪ ልጁን አኒስ ገቢ ኤዴኦን አበርክቶልናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
ጀምበሩ ደመቀ 2ኛ አልበም ሊለቅ ነው

በ21 አመቱ የመጀመርያውን አልበም በ2014 ዓ.ም ያወጣው ጀምበሩ ደመቀ ፣ ወጣት የሂፕሆፕ አድናቂዎችን ልብ ለመግዛት ጊዜ አልፈጀበትም። በራሱ ስም በተሰየመው የመጀመሪያ አልበሙ የአፍሪካ ጃዝ አባት ከሆኑት ከአንጋፋው ዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ ጋር በመጣመር ዓይፈራም ጋሜን አሰምተውን ነበር። በቅርቡ ከኡኖ ጋር ባቀረቡልን ተፍ ተፍ በተሰኘው ነጠላ ዜማ ይበልጥ ከአድናቂዎቹ ጋር ተቀባይነትን አግኝቷል።

ጀምበሩ በጉጉት የሚጠበቀውን "እሳቱ ሰ" የተሰኘውን ሁለተኛውን አልበም ለመልቀቅ ዝግጁትን ጨርሶ ይገኛል፣በዚህ ሳምንት ለህዝብ ጆሮ ይደርሳል።

በዚህም አልበም ከወጣት አቀንቃኞች ጋር የተጣመረባቸው ስራዎች ይገኛሉ፣ ከባህር ማዶ ከኬንያው እውቅ አርቲስት ሬገን ዳንዲ እና ከትውልደ ቡሩዎንዲ በዜግነት እንግሊዛዊው ሙቲ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ከሌሎች ወጣት አርቲስቶች ጋር በአንድነት ሰርቷል፣

ይህ በአፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ የጀምበሩን አልበም ከሃገራችን አልፎ ለአፍሪካውያን ታዳሚዎች ጆሮ እንዲስብ በማመን የተሰራ ስራ እንደሆነ ተገልፃል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ታዋቂዋና ተወዳጇ አርቲስት ዘሪቱ ከበደ ዛሬ ልደቷ ነው

🎂🎂Happy Birthday🎂🎂

ከዘሪቱ ከበደ ስራዎች የቱን ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Zeritu_kebede #Album  #Waliya_Entertainemnt
1👍1
የባላገሩየባላገሩ ምርጥ የፍፃሜ ተወዳዳሪዎች

1, ቅዱስ ዳምጤ - BM01
2, ሄኖክ አበበ - BM02
3, ርብቃ ጌታቸው - BM03
4, እስማኤል መሃመድ - BM04
5, ብሩክ ሙሉጌታ  - BM05
6, በሱፍቃድ መዝገቡ - BM06
7, አክሊሉ አስፋው - BM07

እርሶ የማን አድናቂ ኖት?

👍1