“ክብር ለጥበብ” የእውቅና አሰጣጥ መርሃ - ግብር አየተካሄደ ይገኛል
*
3ኛው “ክብር ለጥበብ” የእውቅና አሰጣጥ መርሃ-ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እየተካሄደ ይገኛል።
የኪነ-ጥበብ፣ ስነ-ጥበብ እና ዕደ-ጥበብ ዘርፍ ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የሚሰጥ አገር አቀፍ የእውቅና መርሃ-ግብር እንደሆነ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስታውቋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በአዋጅ ከተቋቋመበት እና ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የኪነ-ጥበብ፣ የስ-ጥበብ እና የእደ-ጥበብ ዘርፉን ተልእኮ ለማስፈጸም እንደሆነ በሥነ-ስርዓቱ ተጠቅሷል።
ተልእኮውን በማሰፈጸምና በማበረታት በጥበብ ዘርፉ ላይ የሚሰሩ ሙያተኞችን ማበረታት እና እውቅና መስጠት አንዱ የተልእኮ አካል በመሆኑ መርሃ -ግብሩ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በ2013ዓ.ም የተካሄደው የመጀመሪያው የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር በውድድር መልክ ሲካሄድ እንደነበር ይታወሳል። ከ2ኛው ክብር ለጥበብ የእውቅና መርሃ ግብር ጀምሮ ዝግጅቱ የውድድር ሳይሆን በሀገራችን የጥበብ ዘርፍ ላይ የራሳቸውን አሻራ ያበረከቱ እና አሁንም እያበረከቱ ለሚገኙ ባለሙያዎች እውቅና ለመስጠት ያለመ መርሃ ግብር እንደሆነ ታውቋል።
በእውቅና መርሃግብሩ በቴአትር፣ በፋሽን፣ በሙዚቃ፣ ዲጄን ጨምሮ በ12 ዘርፎች ለ50 ሙያተኞች እውቅና እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል።
በሽልማት መርሃ ግብሩ ወጣት እና አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

የማስተዋል እያዩ "እንዚራ" አልበም መቼ ይለቀቃል? ⏳
"እጅግ የማከብራቹ ውድ አድናቂዎቼ እና መላው የሙዚቃ አድማጮቼ በቅድሚያ ላሳያችሁኝ ውዴታ እና አክብሮት ከልቤ አመሰግናለው።
እነሆ "እንዚራ" የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሜን ወደ እናንተ ለማድረስ አሰናድተን የጨረስን ሲሆን የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በኤላ ቲቪ አማካኝነትም በተለያዩ አማራጮች ይለቀቃል እናተም አንደወትሮው አድምጣችሁ አስተያየታችሁን እንደምታደርሱኝ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።" - ማስተዋል እያዩ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music

👍1🔥1
የዘመን ቃናዎች ቁጥር 1
*
የዘመን ቃናዎች ቁጥር 1 የሙዚቃ ቅጂዎች ማስተዋወቂያ ተካሂዷል።
ለዛቸው ከፍ ያለ፣ በትናንት ትዝታ ውስጥ ያሉ፣ ተወዳጅና ለጆሮ የሚስማሙ፤ ነገር ግን በጊዜ ዑደት የተረሱ፣ በደንብ ያልተደመጡ 3 ዜማዎች በነበራቸው ቃና የአሁኑን ዘመን የዋጁ እንዲሆኑ በግጥም ተስተካክለው በድምፃዊ ዳዊት ፅጌ አማካኝነት ለአድማጮች ቀርበዋል።
የሙዚቃ ዝግጅቱ በተለያዩ ምክንያቶች 2 ዓመት እንደፈጀ ተነግሯል።
ሙዚቃውን አንጋፋው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽወታ ያቀናበረው ሲሆን፤ ከድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ጋር በጋራ ፕሮዲዩስ አድርገውታል።
ሙዚቃዎቹ በ1950፣ 60 እና 70ዎቹ የተሰሩ ሲሆኑ፤ ሁሉም ከባንድ ጋር በመድረክ የተቀዱ ናቸው።
ሥራው አድካሚ ቢሆንም ትናንትን የዘከርንበት፣ እኔም ሕልሜን የኖርኩበት ነው ያለው ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ፤ ሁለተኛ አልበሙም በቅርቡ ለአድማጭ ጆሮ እንደሚደርስ ተናግሯል።
የሙዚቃ አቀናባሪው አበጋዝ ክብረወርቅ ሽወታም የአስቴርና የጋሽ ጥላሁንን የቆዩ ዜማዎች በድጋሚ ሰርተናል፤ ይህንንም በዛ ልክ ሰርተነዋል ብሏል።
በሙዚቃ አጃቢነት፥ መስፍን ሽፈራው፣ መስፍን ሙላት እና ሜላት ቀለመወርቅ ተሳትፈዋል።
የዜማ ደራሲ አየለ ማሞ፣ የድምፃዊ እሳቱ ተሰማ፣ የድምፃዊ አሰፋ አባተ እና የድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ ቤተሰቦች ዜማዎቹ እንዲሰሩ ስለፈቀዱም ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

❤1
አርቲስት ጌታቸው ኃ/ማርያም "ወጣቱ ትውልድ በትውልድ ቅብብሎሽ የወረሰውን ሀገር ወዳድነት እና አንድነት ማስቀጠል አለበት" ሲል በባሕል ማዕከል በነበረውው የኪነ-ጥበብ ምሽት ላይ ተናገረ።
***
አርቲስት ጌታቸው በባሕል ማዕከል በነበረውው የኪነ-ጥበብ ምሽት የክብር እንግዳ ሆኖ በቀረበበት መድረክ ባስተላለፈው መልዕክት ወጣቱ ትውልድ በትውልድ ቅብብሎሽ የተረከባትን ሀገሩን መውደድ እና አንድነቱንም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልጿል።
ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ጠንካራ የስራ ባህል እና ምክናታዊነት ብሎም ችግሮችን ወደ እድል እየቀየሩ የመፍትሔ አካል መሆን ከወጣቱ ትውልድ የሚጠበቅ ሀላፊነት ስለመሆኑም አርቲስት ጌታቸው በስፋት አውስቷል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music
***
አርቲስት ጌታቸው በባሕል ማዕከል በነበረውው የኪነ-ጥበብ ምሽት የክብር እንግዳ ሆኖ በቀረበበት መድረክ ባስተላለፈው መልዕክት ወጣቱ ትውልድ በትውልድ ቅብብሎሽ የተረከባትን ሀገሩን መውደድ እና አንድነቱንም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልጿል።
ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ጠንካራ የስራ ባህል እና ምክናታዊነት ብሎም ችግሮችን ወደ እድል እየቀየሩ የመፍትሔ አካል መሆን ከወጣቱ ትውልድ የሚጠበቅ ሀላፊነት ስለመሆኑም አርቲስት ጌታቸው በስፋት አውስቷል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
የክብር ዶክተር ጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ከአድናቂዎቹ ጋር ራት የሚበላበት ምሽት ሊካሄድ ነው።
በሀገራችን በጃዝ ሙዚቃው ዘርፍ የጃዝ አባት በመባል የሚታወቀውና በሙያው ከ50 አመታት በላይ የሰራው የክብር ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ የካቲት 9/2016 ዓ/ም በግዮን ሆቴል በሚገኘው በአፍሪካ ጃዝ መንደር ከአድናቂዎቹ ጋር ተገናኝቶ ራት ይበላል ፊርማውንም ያስቀምጣል።
በዝግጅቱ ላይ ተጋባዥ እንግዶች እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም እንደሚገኙ የታዋቂ ኤቨንት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል አበራ ተናግረዋል።
ታዋቂ ኤቨንት ከእዚህ በፊት የተለያዩ ኤቨንቶችን በማዘጋጀት የሚታወቅ ሲሆን ይሄን ዝነኞችን ከአድናቂዎቻቸው ጋር የማገናኘቱን ስራ ሲያከናውን ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
ከእዚህ በፊት አርቲስት ሰላም ተስፋዬን በሸራተን አዲስ ሆቴል ከአድናቂዎቿ ጋር በማገናኘት ራት የመብላትና የፎቶ ግራፍ መነሳት መርሀ ግብር ማካሄዱ የሚታወስ ነው።

👤 Dawit tsige | ዳዊት ፅጌ
🎵 Yezemen Kana | የዘመን ቃና
━━━━━━━━━━━━━━
➠ RELEASED: 2024
➠ GENRE: #Ethiopian
➠ TYPE: #Album
➠ TRACKS: 3
➠ FORMATS: #Mp3
➠ CHANNEL: @Waliyaentmt
━━━━━━━━━━━━
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
#Dawit_tsige #Album #Ethio_albums #Waliya_Entertainemnt

የሰርፀ ፍሬስብሃት መልዕክት
#Ethiopia | ስለ ዳዊት ጽጌ የተዋጣለት ድምፃዊነት ዛሬ ምን ዐዲስ ነገር መናገር ይቻላል? ኹሉ የመሠከረለት ዜማ የሚኩል እና ሸምኖ የሚቋጭ አዚያሚ ነው። በሙያም በግብረ ገብም ማንነቱን ያስመሠከረ የዘመን አርአያ ነው።
ወደ ኋለኛው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዘመን መለስ ብሎ፥ "ወትረ ኅልው" (classic) የምንላቸውን ዜማዎች ተጫውቶ አዳመጥኳቸው። እጅግ በሚገርም ብቃት እና ዘመን አሻጋሪ በኾነ መንፈስ ውብ አድርጎ ነው ያዜማቸው። የተመረጡት ሙዚቃዎችም በተሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫዎች ላይ እንደተወሳው፣ ከዘወትር ድምጫችን የራቁ እና በቀላሉ የማናገኛቸው ሥራዎች ናቸው።
አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ፥ በተለመደ የሙያ አክብሮት እና ጥንቃቄው፣ የቀደሙ አቀናባሪዎችን አሻራ እንዳይለቅ አድርጎ በዘመን Expression የተጌጠ Adaptation እና Re-Arrangement የተዋሐዱበት ፕሮዳክሽን አስደምጦናል። የጥላሁን ገሠሠን፣ የማሕሙድ አሕመድን፣ የዓለማየሁ እሸቴን፣ የምኒልክ ወስናቸውን፣ የአስቴር ዐወቀን፣ የተፈራ ካሣን (በግርማ ተፈራ) ሥራዎች፤ በልዩ ጥራት እና ከፍታ (ራሳቸውን ድምፃውያኑን ባሳመነ ብቃት) ፕሮዲውስ ማድረጉ ይታወቃልና፣ እንዲህ ያለውን ፕሮዳክሽን እንዴት re-arrange ሊያደርገው እንደሚችል መገመት አይሳነንም ።
የሙዚቃ መሣሪያዎቹ formation እና የሙዚቀኞቹ የየግል ብቃት ብዙ የሚያስጽፍ፣ ምሁራን ሙዚቀኞችን ያገናኘ አስደናቂ መሰባሰብ ነው። እንደ አንድ ኦርኬስትራ ወይም ባንድ አብረው ብናያቸው ኹሌም የምመኛቸውን ሙዚቀኞች ይህ ፕሮዳክሽን ማገናኘት ችሏልና በጣም ደስ ይላል።
እያንዳንዱ ሥራ የራሱ ፈተና ስላለው፥ ይሄኛውም ለሙዚቀኞቹ ፈተና ይኖረዋል። ግን የተሳካለት ስሜት ሰጪ ፕሮዳክሽን መሠራቱን መመስከር ይቻላል።