Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የኤልያስ መልካ አድናቂዎች ዛሬ በሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት የኤልያስ 5ተኛ ሙት አመቱን በማስመልከት አከበሩ።

በብዙዎች ዘንድ የሙዚቃ ፈጣሪ ተብሎ አድናቆትን የተቸረው ኤልያስ መልካ 5ተኛ ሙት አመቱን መሙላቱን አስመልክቶ ዛሬ የኤልያስ መልካ አድናቂዎች በሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት አክብረዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #elias_melka
❣️ የሶል ንግሥት አስቴር አወቀ
የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በሙዚቃ ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች 🇺🇸

#Ethiopia | የኢትዮጵያን ሙዚቃ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ አድማጮች ጋር እንዲደርስ በማስቻል ፈር-ቀዳጅ በመሆንሽ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ልባዊ ደስታውን በመግለፅ እንኳን ደስ አለሽ ይላል ።

በአፍሪካ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ለፈጠርሽው ከፍተኛ ተፅእኖና በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጣቱን ትውለድ በማነቃቃት ያደረግሽው አርዓያነት ይህንን እውቅና እንድታገኚ አድርጓል።

እ. ኤ.አ ጥቅምት 13 ቀን 2024 በሚደረገው የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ይህ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶልሻል።

የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል ዛሬ፣ እሁድ ኦክቶበር 13/2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት እተካሄደ ነው።

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን ያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር የሽልማት ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።

ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #aster_aweke
ከአራት ዓመታት በላይ ጊዜን የወሰደው የወጣቱ ድምፃዊ እዮብ በላይ አልበም በዚህ አመት ለአድማጭ ይደርሳል ተባለ::

ድምፃዊ እዮብ በላይ ከአራት ዓመት በላይ ስለወሰደበት አልበሙ አንዳንድ መረጃዎች የተናገረ ሲሆን ከአንድ ዓመት በፊት ሰርቶ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ባደረሰው እና ተወዳጅነትን ባተረፈው ‹ማለዳ› በተሰኘው ነጠላ ዜማው የሚታወቀው ወጣቱ ድምፃዊ እዮብ በላይ በአዲስ ስራም መጥቷል፡፡

ድምፃዊው ዓርብ ጥቅምት 1/2017 ‹አጀቤ› የተሰኘውን ሁለተኛ ስራውን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰ ሲሆን ምህረትዓብ ደስታ በግጥምና ዜማ ተሳትፎ አድርጎበታል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ) በቅንብር እና ሚክሲንግ እንዲሁም ሰለሞን ሃ/ማርያም በማስተሪንግ ተሳትፎ እንዳደረጉበት ድምፃዊው ከመሰንበቻ ጋር ባደረገው ቆይታ አንስቷል፡፡

ከአራት ዓመት በላይ የሆነውን አልበሙን ወደ ሙዚቃ ወዳጆች ሊያደርስ መሆኑንም ድምፃዊው ተናግሯል። የ ይህን የበኩር የሆነ አልበሙን እስከ ዘንድሮ ዓመት መጨረሻ ሰርቶ ላይ ለማጠናቀቅ አቅዶ በሂደት ላይ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ከአልበሙ አስቀድሞ ተጨማሪ አንድ ነጠላ ዜማ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ያለው ድምፃዊ እዮብ በላይ ስራው ለአድማጭ ብቁ ሆኖ ሲገኝ ለመልቀቅ መታቀዱን በተጨማሪነት ገልጿል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የ500 ሺህ ብር ካሜራ

ስንታየሁ ሲሳይ የበለጠ ሳቁን ዛሬ ደራሲ ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር በሆነው ቴዎድሮስ ተሾመ እነሆ 500መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የታሸገ አዲስ ብላክ ማጂክ ካሜራ እንካ ስንቴ ስራህን ጀምር ላይቶች እና ሌሎች እቃዋች በፈለክም ሰአት በውሰት መልክ መውሰድ ትችላለህ ብሎ ከፍተኛውን ስጦታ አበርክቶለታል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ዳዊት ጽጌን ጨምሮ የሙያ ባልደረቦቹ በአሜሪካ እውቅና ተሰጣቸው

#Ethiopia | ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የሙዚቃ አቀናባራው አበጋዝ ሺዎታ እና ፕሮሞተር ሰለሞን ገብረማሪያም (ኪንግ ሶሎን )ጨምሮ በሲያትል ከተማ እውቅና ተሰጣቸው ።

ደዊት ፅጌ በ2024 በአሜሪካን ከተሞች ያቀረባቸው የተሳኩ ዝግጅቶች በማስመልከት እና ልዩ ተስጦ ያለው ድምፃዊ በመሆኑ ለሙዚቃው ላበረከተው አስተዋፆ ጭምር እውቅና አግኝቷል።

የሙዚቃ አቅናባሪው አበጋዝ ሺዎታ በኢትዮጵያ የምርጥ ሙዚቃ አቀናባሪ በመሆኑ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲሁ እውቅና በክብር ተሰጥቷቸዋል።

በተያያዘ ዜና - የኪንግ ሶሎ ፕሮሞሽን ባለቤት ፕሮሞተር ሰለሞን ላለፉት 10 ዓመት በሲያትል ውስጥ በርካታ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት እውቅና ተሰጥቶታል። ( City of Seattle • Office of the Mayor) የሲያትል ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት ቢሮ እውቅናውን የሰጠ ሲሆን ምክትል ከቲባዋም (Adiam Emery ) በዝግጅቱ ላይ በመገኘት የእውቅና ሰርተፍኬቱን አበርክተው አድናቆታቸውን ለተሸላሚዎቹ ገልጸዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሃያላኑዋ አሜሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ከሚንቅሳቅስባቸው ዋንኛዋ ከተማ የሆነው ሲያትል ዋሽግተን ምክትል ከቲባዋ መሆናቸው ለኢትዮጵያን ትልቅ ኩራት መሆኑ ተግልጿል።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dawit_tsige
የአርቲስት አምሳል ምትኬ የባህል አዳራሽ የእሳት ቃጠሎ አጋጠመው

የተወዳጇ እና የባሕል ሙዚቃ አቀንቃኟ ድምፃዊት አምሳል ምትኬ የባህል ምሽት ቤት እና የምግብ አዳራሽ ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ መውደሙ ከስፍራው በደረሰን መረጃ አረጋግጠናል

የባሕር ዳር ነዋሪ እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረገው ርብርብ ጥሩ ነበር። ሆኖም የእሳቱ ሁኔታ ከባድ ስለነበር ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የባህር ዳር ምንጮች አረጋግጠዋል።

የእሳት አደጋውን እስከ ምሽት 5:30 ገደማ ለመቆጣጠር የተደረገው ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ ተነስቷል።

ከእዚህ በተጨማሪ በምሽት ቤት ፊት ለፊት የነበረውና በርካታ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያፈራው አንጋፋው ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ሳይወድም እንዳልቀረ ተነስቷል።

መረጃው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በክልሉ ሆነ በፌዳራል መንግስቱ በኩል የተሰጠ ምላሽ እስካሁን የለም።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #amsal_mitke