Waliya Entertainment
295 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ከአብዱ ኪያር አዲሱ አልበም ጀርባ ያለው የሙዚቃ አቀናባሪ ስማገኝሁ ሳሙኤል

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ  ተሰርተው ለሙዚቃ አፍቃሪያን እየደረሱ ከሚገኙ የሙዚቃ ስራዎች ጀርባ አሻራውን በማሳረፍ ላይ የሚገኘው ወጣቱ የሙዚቃ አቀናባሪ ስማገኘሁ ሳሙኤል ከሀገር አልፈው ባሕር ማዶ መሻገር የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት እንደሚጥር አስታውቋል።

በቅርቡ ለሙዚቃ አፍቃሪያን በደረሰው የአብዱ ኪያር አምስተኛ አልበም ከአንድ ስራ በስተቀር በሁሉም ላይ በቅንብር እና በማስተሪንግ ተሳትፎ አድርጓል። ከአብዱ ኪያር ጋር የአልበም ስራው የመስራቱ አጋጣሚ የተፈጠረው በኮሜዲያን ጥላሁን እልፍነህ እና በብስራት ሱራፌል አማካይነት መሆኑን ተናግሯል።

በእዚህም መሰረት የአልበሙ ማሟሻ ቀዳሚው ስራ "ሰውዬው" የተሰኘው ሙዚቃ እንደነበር አንስቷል፣ ከእዚያ በኋላ ሌሎች የሙዚቃ ስራዎች ሊሰሩ መቻላቸውን ወጣቱ አቀናባሪ ይገልፃል።

"ባይ ባይ" የተሰኘው ሙዚቃ ደግሞ በመሰራት ረገድ ሶስተኛው ቢሆንም የሙዚቃው ቅጂ ለማድረግ ግን ሁሉም ተቀድተው እስኪያልቁ አስገድዶ ነበር።

ምክንያቱ ደግሞ አብዱ ኪያር ሙዚቃው በሚሰራበት ወቅት ላይ ይረበሽ ስለነበር ነው ያለው ስማገኘው ሁሉም ስራዎች ተቀድተው ካለቁ በኋላ ወደ እዚህኛው ሙዚቃ ቅጂ መሻገራቸውን ተናግሯል፣ በመጨረሻው ቅጂም ከአንድ ጊዜ በላይ መቅዳት እንዳልተቻለ አንስቷል፣ በእዚህም መነሻነት ከአልበሙ ስራ ውስጥ ለእዚህኛው ሙዚቃ የተለየ ቦታ እንደሚሰጥ ተናግሯል።

ይህን አልበም ለመስራት የቀደሙ የአብዱ ኪያር ስራዎችን ጊዜ ሰጥቶ ማዳመጥን ጨምሮ የእዚያን ወቅት የሙዚቃ ስራዎች ለመረዳት ሰፊ ጊዜ እንደወሰደበት በቆይታው አንስቷል።
ባልታሰበ አጋጣሚ ዶግ አመድ የሆነብኝ ስቱዲዮዬ ካሳጣኝ ይልቅ የሰጠኝ ይበልጣልና ለበጎ ነው ብዬ ተቀብዬዋለሁ ያለው ስማገኘው የህዝብ ፍቅርን ያየሁበት፣ ሰዎች ለስራዎች ቦታ እንዳላቸው የተረዳሁበት ነው ሲል ይናገራል።

መለስ ብሎ የትላንት መንገዱን የሚገልፀው ስማገኘሁ ተወልጄ ያደኩበት አከባቢ የሀዘንም ሆነ የደስታ ስሜቱን የሚገልፅበት መንገድ ሙዚቃ መሆኑ ላይ በእምነት ተቋም ውስጥ ኪቦርድን ጨምሮ ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ጋር መቆራኘቴ የፈጠረልኝ ድርብ አጋጣሚ ወደ እዚህ መስመር ወስዶኛል ሲል ይናገራል።

የመጀመሪያው የሙዚቃ መሳሪያው ደግሞ ክራር መሆኑን የሚገልፀው ስማገኘሁ ሳሙኤል በእዚህ መነሻት ዛሬ ላይ በርካታ የሙዚቃ ስራዎች የሚፈልቁበትን ስቱዲዮውን "ዲታ" ብሎ ለመሰየሙ ምክንያት እንደሆነው ይናገራል።
(ዲታ የሚለው ቃል ወላይትኛ ሲሆን ትርጓሜው "ክራር" ማለት ነው።)

ከህዝብ ጋር በስፋት የተዋወቀበት ቀዳሚ ስራው ደግሞ የአስገኘው አሽኮ(አስጌ ዲንዳሾ) ሙዚቃ መሆኑንም ይነሳል።

የሙዚቃ ባለ ተሰጥኦ ልትባል የምትችለዉ ያደክበትን ማህበረሰብ እንዲሁም የሀገርህን የተለያዪ ብሄሮችን ባህል ጠብቀህ ከዘር እና ጎሳ ጎራ  ሳትይዝ በሙዚቃዉ አለም ራስህን በአለም አቀፍ ለየት ባለ በራስህ ቀለም ስትጓዝና ተቀባይነትህም በአድማጩ ዉስጥ ተፅእኖ ሲፈጥር  ነዉ ሲልም ይገልፃል።

👉ስማገኘሁ ሳሙኤል (Dita Studio)
በጥቂቱ ካቀናበራቸው እና ከድምፃዊያን ውስጥ ሙዚቃ የሰራላቸዉ እዉቅ ወጣት ድምፃዉያን መሀከል

1 ጃኪ ጎሲ
2 ብስራት ሱራፌል
3 አብዱ ኪያር
4 ሄዋን ጃኖ
5 ያሬድ ነጉ
6 ዲዲ ጋጋ
7 አስጌ ዴንዳሾ
8 አንዱአለም ጎሳ
9 አለምዬ
10 ሰላማዊት (ምላሽ)
11 ማሚላ ሉቃስ
12 ኪቺኒ ጎአ
13 ማይኪ ሸዋ
14 ምእራፍ አሰፋ
15 ታሪኩ ጋንጋሲ
16 አለማየሁ ዛሳ
17 ሳሚ ጎ
18 ነፃነት ሱልጣን
19 ቡዜ ማን
20  ኮሜዲያን ታሪኩ 80 (ባማን ደና ) ይገኙብታል::
ከዘመናዊ ሙዚቃዎች ባለፈ የብሔረሰብ ሙዚቃዎችንም ሰርቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music  #dita_studio
Abdu Kiar ! (ABD)
The real አራዳ from ሰባተኛ !!

ቃለምምልሳቸው በፍጹም እንዲያልፈኝ ከማልፈልገው ሰዎች መካከል አብዱ አንደኛው ነው ። ለምን ? ራሱን ሆኖ ስለሚያወራ : ስለማያስመስል : ነገር ለማሳመር ብሎ ስለማይራቀቅ ።

ከብዙ የዚህ ዘመን የሃይማኖት ሰባኪዎች ይልቅ የአብዱ ኢንተርቪው ለልብ የቀረበ ነው። ስለሞራል : ስለትህትና: ስለሰው መሆን : ስለመልካምነት : ስለሕይወት ውጣ ውረድ ኤቢዲ ሳይመክርህ ይመክርሃል ።

አዲሱን አልበም ለሰራለት አቀናባሪው ስማገኘሁ አዲስ መኪና ቀይሮለታል። ሰይፉ ሲጠይቀው 'ወላሂ የራሱን ሂሳብ ነው የሰጠሁት ' አለ ። አየኸው ስብዕና !

ብዙ charity አለው ግን ከረዳው ሰው ጋር ፎቶ የለውም ። አይናገረውም። ሲነሳበትም አይወድም።አንዳንድ ሰው በሙዚቃ ጥራት አቃቂር ሊያወጣባቸው የሚሞክርባቸው ሙዚቃዎቹ እንዴት እንደጻፋቸው : ለምን እንደዘፈናቸው ሲናገር የህሊናው ነገር ይገርመኛል ።

እነ አብዱ ሰፈር ነኝ ! and am really proud of the dude ሰባተኛ created !

Via Journalist Ermias Begashaw

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
እንደ አብዱ ኪያር መሆን ካልተሰጠህ በቀር አትችልም
**
መሬት መርገጡ ሁሌም ይደንቀኛል ። ቅለቱ ይስበኛል ። ከድምጻውያን የአብዱኪያርን ያህል ቃለመጠይቁን ሙሉውን ማየት ፣ እኔም ራሴ ቃለመጠይቅ ባደረኩለት የሚያጓጓኝ የለም ። በድምጻዊነት እንደ እርሱ መሆን ፣ ከእርሱም በላይ መሆን ትችላለህ ። ጉሮሮህ ላይ ወዝ ከተሰጠህ በቃ ። እንደ አብዱ መሬት መርገጥ ግን ከድምጻዊነቱ በላይ ከባድ ነው ። ሰውነት ደግሞ እሱ ነው ። ችሎታና ዝናህ ያንተ ነው ። እንደ አብዱ ስትስቅ የአፍህ ቅርጽ ሳያሳስብህ ፣ ስትናገር ያለ Editing ያንኑ ያሰብከውን አድርገህ ፣ ማልቀስ ካለብህ ዝናህ ሳያሳስብህ ፣ ዘና ብለህ ፣ ፈታ ብለህ ፣ ከሁሉ በላይ ዝናህን ጥለህና ሰውነትህን አንስተህ መቆም ከባዱ ስራና ስጦታ እሱ ነው ። የሚሰጥህ ነው እንደ ድምጻዊነቱና ደራሲነቱ ሁሉ ። የተሰራህበት ነው ። ቀድሞ ያለቀ ጉዳይ ነው ። ሌላው ላይ ያማረውን ልብስ ገዝተህና ለብሰህ እንደሚያምርብህ አይደለም ። ባህሪ የልክህ ነው ። አንስተህ መልበስ ነው ። ሰው መክሮህ ወይም መጽሐፍ እንብበህ የምታስተካክለው ጥቂት ነው ።

" ምን ሆኛለሁ ? " መጽሐፍን እንደ ተደራሲ ሳነበው የተሰማኝ ይህ ነው ። ግድየላችሁም አንብቡት ። በሰው ችሎታ እመሰጣለሁ እንጂ አልቀናም ። ሰውነት ያስቀናኛል ። " እሱን በሆንኩ " ያሰኘኛል ። ለዚህ ነው አብዱ ኪያር ሁሌም የሚያስቀናኝ ።

ከጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተክላአረጋይ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
ድምጻዊ ዮሐናን የካሴት ኦድዮ ስራዎች የብራንድ አምባሳደር ሆነ

ካሴት የኦዲዮ ስራዎችን ማለትም ዘፈን፣ መዝሙር፣ ወግ፣ ትረካ፣ ግጥም በጃዝና መሰል ስራዎችን ለአድማጮች በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ለመሸጥ ታልሞ የተሰራ የቴሌግራም ቦት እንደሆነ ዛሬ ሐምሌ 29/2016 ዓም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ተደርጓል።

ካሴት በኦንላይን ኮሙኒኬሽን የበለፀገ ሲሆን አድማጮች በቀላሉ በስልካቸው ላይ ሌላ አዲስ መተግበሪያን መጫን ሳያስፈልጋቸው በሚያዘወትሩት ቴሌግራም ላይ @kasetrobot ብለው ቦቱን በመቀላቀል መጠቀም እንደሚችሉ በመግለጫው ተገልጿል።

አቶ ናሆም በለጠ ካሴትን ያበለፀገው ድርጅ የኦንላይን ኮሙኒኬሽን መስራች እና ስራ አስኪያጅ ናቸው "አርቲስቶች በካሴት ቴሌግራም ቦት ስራዎቻቸው ለገበያ ሲያውሉ አድማጮች የገዙትን አልበም ለሌሎች መላክና መስጠት የማያስችል በመሆኑ የኮፒራይት ጥሰትን ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም እያንዳንዱን ሽያጭ መከታተል ሚያስችል የድሀረ-ገፅ መግቢያ ስለሚኖራቸው አሰራሩን ግልጽ ያደርገዋል" ብለዋል።

በ3 ቋንቋዎች አማርኛ፣ እንግሊዘኛ እና አፋን ኦሮሞ አማራጭ የቀረበ ሲሆን በሰከንዶች ውስጥ አልበሙን በቴሌብር እና ኤም.ፔሳ ገዝተው ማዳመጥ እንደሚቻል በመግለጫው ተብራርቷል።

በቅርብ ጊዜ በርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ለህዝቡ እያደረሰ የሚገኘው ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ዮሐና ከፍተኛ ክፍያ በተባለልት የካሴት ብራንድ አምባሳደር በመሆን በመድረኩ ሹመቱን ተቀብሏል።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Yohanna #Music
ሙዚቃዊ የፐብሊሺንግና የአርቲስት ውል ከአንጋፋው አይቤክስ ባንድ ጋር ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን ጆቫኒ ሪኮና ሰላም ስዩም አይቤክስ ባንድን ወክለው የተፈራረሙ ሲሆን ይህ ስምምነት ሙዚቃዊ ቀደም ሲል የተሰሩ የአይቤክስ ስራዎችን እንዲያወጣ እንዲሁም ከባንዱ ጋር ወደ ፊት አብሮ እንዲሰራ ያስችላል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ተወዳጁ ራፐር ልጅ ሚካኤል አዲስ አልበም ሊያወጣ ነው።

ከዚህ በፊት በሰራቸው ሁለት አልበሞች ተቀባይነትን ያገኘው ተወዳጁ የራፕ ሙዚቀኛ ልጅ ሚካኤል "አዲስ አራዳ" የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ሊለቅ መሆኑን አሳወቀ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #lij_mic
ድምፃዊት ዳጊ እና ቤቢ



#photo #waliya_entertainment #music #dagi #baby
❣️ ጸልዩልኝ! - አርቲስት ያሬድ ነጉ

#Ethiopia | አርቲስት ያሬድ ነጉ ( ደግ ልቡን ይዞ) ጓደኞቹን በማስተባበርም የተለያዩ ለድጋፍ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን እና ለምግብነት የሚውሉ ግብአቶችን በአይሱዙ አስጭኖ የአደጋው ስፍራ ድረስ በመገኘት ( ደራሽ ለወገኔ 🙏❤️ ) በማለት በአስክሬን ፍለጋ ስራ ላይ ነበር።

ትናንት - ያሬድ ነጉ ወደ ይርጋለም ከተማ ለጾመ ፍልሰታ ( መንፈሳዊ ጉዞ ) ላይ ነበር።

ይሁንና ...
ትናንት ሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 3:30 ሰዓት ላይ ከጓደኞቹ ጋር እራት እየተመገበ ሳለ "ልቤን!" ብሎ አላትዮን ጠቅላላ ሆስፒታል ገብቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ጀርባ የነበረችው “ኃይለኛዋ” ሴት !

#Ethiopia: በቅርቡ ተወዳጁ ድምጻዊ እጅግ ስኬታማ የተባለለትን የሙዚቃ ድግሱን በዱባይ ማቅረቡ ይታወቃል ። ይህን ኮንሰርት ያዘጋጀው ማነው ካላችሁ ደሞ G-power የሚባል ድርጅት ነው፡፡ኮንሰርቱ ያማረ እና ያልተንዘላዘለ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ደግሞ ከዚሁ ድርጅት የአስተዳደር ሰዎች አንዷ የሆነችው መአዛ ፈንታው ዋነኛ ተጠቃሽ ናት።

በኮሪያ በነበራት ቆይታ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህርነት አንስቶ በዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ኮሚኒኬሽ ሌክቸረርነት እንዲሁም በUN የደቡብ ኮሪያ ቢሮ የስደተኞች አስተርጓሚነት ሰርታለች፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ወደ ደቡብ ኮርያ ሲሄዱም ከኮሪያውያኑ ባለስልጣናት ጋር እንዲግባቡ የኮርያ ቋንቋን አቀላጥፋ የምትናገረው መአዛ ትጠራለች፡፡ የዱባዩን ድግስ ያለ እንከን የደገሰችው መአዛ አሁን ደሞ ለአዲስ አመት" G -power እንቁጣጣሽ ኮንሰርት" እያዘጋጀችም ነው፡፡

ተጠባቂው ኮንሰርት ጳጉሜ 2 በዱባይ ይካሄዳል ። በኢትዮጵያዊያን የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፍት አምስት ድምጻዊያን ስራቸውን ያቀርባሉ ። በዕለቱ ኮንሰርቱን የሚያደምቁት ኢትዮጵያዊያን ድምጻዊያን ፤ ነዋይ ደበበ ፣ጎሳዬ ፣አብርሀም ፣አንዱ አለም ፣ ዮሀና....በአዲስ አመት ይደምቃሉ ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music