Waliya Entertainment
295 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ባልታሰበ አጋጣሚ ዶግ አመድ የሆነብኝ ስቱዲዮዬ ካሳጣኝ ይልቅ የሰጠኝ ይበልጣልና ለበጎ ነው ብዬ ተቀብዬዋለሁ ያለው ስማገኘው የህዝብ ፍቅርን ያየሁበት፣ ሰዎች ለስራዎች ቦታ እንዳላቸው የተረዳሁበት ነው ሲል ይናገራል።

መለስ ብሎ የትላንት መንገዱን የሚገልፀው ስማገኘሁ ተወልጄ ያደኩበት አከባቢ የሀዘንም ሆነ የደስታ ስሜቱን የሚገልፅበት መንገድ ሙዚቃ መሆኑ ላይ በእምነት ተቋም ውስጥ ኪቦርድን ጨምሮ ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ጋር መቆራኘቴ የፈጠረልኝ ድርብ አጋጣሚ ወደ እዚህ መስመር ወስዶኛል ሲል ይናገራል።

የመጀመሪያው የሙዚቃ መሳሪያው ደግሞ ክራር መሆኑን የሚገልፀው ስማገኘሁ ሳሙኤል በእዚህ መነሻት ዛሬ ላይ በርካታ የሙዚቃ ስራዎች የሚፈልቁበትን ስቱዲዮውን "ዲታ" ብሎ ለመሰየሙ ምክንያት እንደሆነው ይናገራል።
(ዲታ የሚለው ቃል ወላይትኛ ሲሆን ትርጓሜው "ክራር" ማለት ነው።)

ከህዝብ ጋር በስፋት የተዋወቀበት ቀዳሚ ስራው ደግሞ የአስገኘው አሽኮ(አስጌ ዲንዳሾ) ሙዚቃ መሆኑንም ይነሳል።

የሙዚቃ ባለ ተሰጥኦ ልትባል የምትችለዉ ያደክበትን ማህበረሰብ እንዲሁም የሀገርህን የተለያዪ ብሄሮችን ባህል ጠብቀህ ከዘር እና ጎሳ ጎራ  ሳትይዝ በሙዚቃዉ አለም ራስህን በአለም አቀፍ ለየት ባለ በራስህ ቀለም ስትጓዝና ተቀባይነትህም በአድማጩ ዉስጥ ተፅእኖ ሲፈጥር  ነዉ ሲልም ይገልፃል።

👉ስማገኘሁ ሳሙኤል (Dita Studio)
በጥቂቱ ካቀናበራቸው እና ከድምፃዊያን ውስጥ ሙዚቃ የሰራላቸዉ እዉቅ ወጣት ድምፃዉያን መሀከል

1 ጃኪ ጎሲ
2 ብስራት ሱራፌል
3 አብዱ ኪያር
4 ሄዋን ጃኖ
5 ያሬድ ነጉ
6 ዲዲ ጋጋ
7 አስጌ ዴንዳሾ
8 አንዱአለም ጎሳ
9 አለምዬ
10 ሰላማዊት (ምላሽ)
11 ማሚላ ሉቃስ
12 ኪቺኒ ጎአ
13 ማይኪ ሸዋ
14 ምእራፍ አሰፋ
15 ታሪኩ ጋንጋሲ
16 አለማየሁ ዛሳ
17 ሳሚ ጎ
18 ነፃነት ሱልጣን
19 ቡዜ ማን
20  ኮሜዲያን ታሪኩ 80 (ባማን ደና ) ይገኙብታል::
ከዘመናዊ ሙዚቃዎች ባለፈ የብሔረሰብ ሙዚቃዎችንም ሰርቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music  #dita_studio