ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
497 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተለያየ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የመኪና ስፖኪዮ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች (ልጆች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም ወረዳ 2 ጋዜቦ አደባባይ እና ወረዳ 9 አካባቢ ነው የተያዙት ተብሏል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ የትራፊክ መብራቶች እና ተሽከርካሪ በሚቆምባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ስፖኪዮ ሲሰርቁ እንደነበር አመልክቷል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፈው የተገኙ ህፃናቶች መሆናቸውም ተመላክቷል።

ይህ መነሻ በማድረግ በተደረገ ምርመራ ለህፃናቱ ስምሪት የሚሰጡ የተደራጁ ወንጀለኞች መኖራቸውን ፖሊስ ማረጋገጡን ገልጿል።

አንዳንድ ህፃናት መኪና የሚጠብቁ  እንዲሁም እርዳታ የሚፈልጉ መስለው በመቅረብ ወንጀል እንደሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው   በትራፊክ  መብራቶችም ሆነ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ሲቆሙና በዝግታ ሲያሽከረክሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በስላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም እና የደስታ ይሁንልን!
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቴዘርን ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ ይህንን ቦት ያናግሩ -> t.me/TetherGramBot
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የአፋልጉኝ ተማጽኖ

#Ethiopia | ወጥተን የምንገባበት፤ ሰርተን የምንበላበትን መኪናችንን ሰረቁን!

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A - 75482 አዲስ አበባ የሆነ ኮሮላ 2003 ሞዴል ሲልቨር ከለር የሆነውን መኪናችንን፣ ከቆዬ ፈጨ ወደ ቦሌ ቡልቡላ በሚወስደው መንገድ ወደ ገላን ጉራ ፕሮጀክት መግቢያ በር ላይ ከ4: 30 አስከ 5: 30 ገደማ ባቆምንበት ተሰርቀናል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት፣ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ም / ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ መዝገብ መኪናው ባልታወቀ ግለሰብ መሰረቁን የሚገል ደብዳቤ ልኳል።

መኪናውን ያያችሁ አቅራቢያችሁ ለሚገኝ የሕግ አካል ያሳውቁ!!

ወይም

ከታች በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ!!

ያላያችሁ፣ ላዩት እንዲደርስ በመልካምነት ሼር በማድረግ ያጋሩ!!

0911281980
0912877977
0912112574

አፋልጉን ይላሉ
ሚካኤል እና ባለቤቱ መታሰቢያ
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba

ጓደኛቸውን #በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ተያዙ።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ ነው።

ጓደኛማቻቾቹ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል።

ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡

ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ካበናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ " ወለቴ " ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት አረጋግጧል።

መኪናውም ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማወል ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
3 people died in a traffic accident.
May 13, 2016 in Jimma zone Sokoru woreda Abelti kebele three people died.

In the accident that happened at 7.30 in the morning, seven people were seriously injured in addition to three people who died.
🙏🙏🙏🙏

Let's drive carefully.
በምሽት ተገቢ የተሽከርካሪ መብራት በማይጠቀሙ አሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር ተደረገ:: *54 አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል -----
- (ት/ማ/ባ/ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በትናንትናዉ እለት በምሽት የሌሎች አሽከርካሪዎችን እይታ በማወክ ለትራፊክ ግጭት እና ለትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል ምክንያት በሆኑ አሽከርካሪዎች ላይ በልዩ ኦፕሬሽን ቁጥጥር አድርጓል።

በክፍለከተማዉ በተመረጡና እግረኞች በሚበዙባቸው ቦታዎች ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በተቀናጀ መልኩ ጥብቅ ቁጥጥር ተካሂዷል።

በቁጥጥሩም ረጅም መብራት እያላቸው በማብሪያ ጊዜ ያላበሩ፣ መብራት የሌላቸው፣ እያላቸዉ ያላበሩ፣ ከስታንዳርዱ ውጪ ተጨማሪ መብራት የገጠሙ በድምሩ 54 አሽከርካሪዎች በደንብ 395/2009 በእርከን 1/21 እና በእርከን 4/5 መሰረት የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ይኸዉ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የመንገድ ትራፊክ የግንዛቤና ደንብ ማስከበር ዳይሬክተር አቶ ሀገሬ ኃይሉ አስታዉቀዋል።
👍1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ሲጀመር ‘የኮቴ’ ክፍያ አገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " - ጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር

የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞጆ መግቢያ ‘ #የኮቴ ’ በሚል ታጣቂዎች አስቁመው 2,000 ብር እያስከፈሏቸው መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።

ካሁን ቀደም ገንዘቡን ሲጠየቋቸው የነበረው አንዳንድ ጊዜ በቀን እንደነበር ፣ ከሰሞኑን ግን ቀንም ሌሊትም እየጠየቋቸው ከመሆኑም ባሻገር ድብደባና እንግልት እያደረሱባቸው መሆኑን አስረድተዋል።

ሰሞኑን አንዱን ሹሬር ሞጆ መግቢያ ከሌሊቱ 6 ሰዓት አስቁመው ገንዘብ እንደጠየቁት፣ ‘የለኝም’ ሲላቸው እንዳንገላቱት ገልጸዋል።

ሌላኛው ሹፌር ክፉኛ መመታቱን አመልክተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ “ ኮቴ ” ክፍያው ምንነት ያውቅ እንደሆን የጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበርን ጠይቋል።

ማኀበሩ ፤ " አሁን #ጂቡቲ ስንደርስ የሌላ አገር መሬት ስለምንረግጥ ‘ የኮቴ ’ እንከፍላለን። የተለመደ ነው። እዚህ ግን ‘የኮቴ’ እያሉ 2,000 ነው የሚጠይቁት። ይሄ ደግሞ ተገቢም አይደለም " ብሏል።

" ሞጆ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ድርጊቱ አለ " ያለው ማኀበሩ ፣ አንድ ጊዜም ቢሆን መከፈሉ ከህግ አግባብ ውጪ ሆኖ ሳለ በድጋሚ ሌላ ቦታ ላይ እንደሚያስከፍሏቸው አስረድቷል።

ማኀበሩ ፤ " ሲጀመር ‘ የኮቴ ’ ክፍያ በአገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " ብሎ፣ ከክፍያው ባሻገር አሽከርካሪዎቹ ገንዘቡን በሚጠይቁ መሳሪያ የታጠቁ ታጣቂዎች ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው፣ የክልሉ አካላት ድርጊቱን ቢያውቁም መፍትሄ እንዳልሰጡ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ቅሬታውን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ክልሉ ባለስልጣናት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

Video Credit - ኪያ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
👍1
ከመገናኛ አዲሱ ገበያ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ 19 ሚኒባስ ታክሲዎች ስራቸው እንዲያቆሙ ማድረጉን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ተናገረ
ጥንቃቄ
ጭሮ (አሠበ ተፈሪ ) መግቢያ ላይ የደረሰ አደጋ ነው ቦታው ከርቭ ላይ ሥለሆነ በጨለማ አይታይም ቶሎ ካልተነሣም ተጨማሪ አደጋ ያስከትላል ጥንቃቄ እናድርግ
17/09/2016
አፋልጉን

ይሄ በፎቶ የምታዮት ወንድማችን ዳዊት አስናቀ ይባላል ተወልዶ ያደገዉ እዚሁ አዲስ አበባ ነው ሆኖም ግን ከ3 ቀን በፊት የጠፋ እሰካሁን አልተመለሰም። በጊዜው ኮድ 2-B65248 ኮሮላ መኪና እያሽከረከረ ነበር።

ሰልኩም አይሰራም። በምን ሆኔታ ላይም እንዳለ አናውቅም
በቻላቹሁት አቅም ሁሉ ሸር በማድርግ ወንድማችንን አፋልጉን

ስልክ
:- 0918706526
፡-0913412564
:-0911609294
👍1