የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
ዐቢይ ጾም እየደረሰ ነው፡፡ እንደ ስሙም ሁዳዴ - ሰፊ እርሻ ነው፤ ብዙ በረከት የሚገኝበት መንፈሳዊ እርሻ!

ታዲያ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በየቀኑ ያስተምር ነበር፡፡ ምእመናንም በየቀኑ ትምህርቱን ይከታተሉ ነበር፡፡ ይማሩት የነበረውም በዋናነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነው፡፡ በየቀኑ እንዲያነቡትም ያሳስባቸው ነበር - ሊቁ!

ስለዚህ አባታችንን አብነት አድርገን በዚህ የዐቢይ ጾም ወቅት ከሌሎች መንፈሳውያን መጻሕፍት በተጨማሪ ራሱን መጽሐፍ ቅዱሱን ልናነበው ይገባናል፡፡ በቀን ቢያንስ አንድ ምዕራፍ ማንበብ ብንችል መልካም ነው፡፡ ሊቁ እንደሚነግረንም ለአራቱ ወንጌላት ቅድሚያ ሰጥተን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡

"መጽሐፍ ቅዱስ የመድኃኒት ሳጥን ነውና፡፡"
ዐብይ ጾም

ዐብይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው?

ዐብይ ጾም ለምን ዐቢይ ተባለ?
ጾም ማለት ፡- ለዘላዓለም ሁሉንም ሕዋሳት ከኃጢአት መከልከል፣ለተሰነ
ጊዜ እህል ከመብላት ዉሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት
ከጥሉላት ከስጋ ፣ከወተት፣ከቅቤ፣ከእንቁላል፣በአጠቃላይ ከእንሰሳት
ዉጤት መከልከል ነው።
+
#የጾም_ጥቅም ፦ የሥጋ ምኞትን የምታጠፋ የነፍስን ቁስል የምታደርቅ
ለጎልማሶችም ጸጥታንና እርጋታን የምታስተምር ከእንሰሳዊ ግብር ጠባይ
የምትከለክልና ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባት ደገኛ ሥርዓት ነች፡፡

በብሉይ ኪዳን ብዙ ሰዎች በጾም ተጠቅመዋል እግዚአብሔር የጾምን
ሥርዐት የደነገገው ገና ከጥዋቱ አዳምን በፈጠረበት ወቅት ነው ፡፡ እጸ
በለስን አትብላ ማለት ትዕዛዝ ቢሆንም ትዕዛዙ ግን የጾም ትዕዛዝ ነው
አዳምና ሔዋን ይህን የጾም ሥርዐት በመሻር እጸ በለስን በልተው
በመገኘታቸው ምን እንደደረሰባቸው በቅዱስ መጽሐፍ ላይ የምና ነበው
ነው፡፡
በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳን አበው ጾምን የጸሎት እናት የእንባ ምንጭ
የጽድቅ መሠረት ደገኛ ሥርዐት በማለት ይገልጻሉ፡፡
ጾም በብሉይ ኪዳን ስንመለከት፦
በሕዝብ ላይ የተቃጣውን መከራ ለማቅለል ተጠቅመውበታል መጽ ኢያሱ
7÷6 -9፣ መጽ አስቴር 4÷16 ፣ትንቢተ ዮናስ 1 ፣ መ.ሳሙኤል ካል
12÷17 ዘዳ 9÷9 -18፣ትንቢተ ኢዩኤል 2÷14 ፣መዝ 34(35) ÷ 13
ትን.ዳን 10÷2 መዝ 108÷ 24
ጾም በሐዲስ ኪዳን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሥራው ሁሉ መጀመሪያ ያደረገው ጾምን
ስለሆነ መሥራቹ ክርስቶስ ነው በሐዲስ ኪዳን ጾም የታዘዘ ስለመሆኑ
የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመለከታለን
ማር 2 ÷20 ፣ማር 9÷29 ፣ማቴ 6÷16 ፣ ሉቃ 6÷21 ፣ሐዋ 13÷3
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለጾም ሥርዐትና ደንብ
አውጥታለች በዓመት ውስጥ ሰባት የዓዋጅ አጽዋማት እንዳሉና
ማንኛውም ክርስቲያን እንኝህን አጽዋማት እንዲጾም ታዛለች እነዚህም
አጽዋማት
 ዐቢይ ጾም
 ጾመ ሐዋርያት
 ጾመ ስብከት (ጾመ ነብያት)
 ጸመ ፍልሰታ
 ጾመ ድኅነት
 ጾም ነነዌ
 ጾመ ገሃድ
ከነዚህ አጽዋማት ውስጥ የምንመለከተው ዐቢይ ጾም ነው።
ዐቢይ ጾም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሥርዓት መሰረት የአዋጅ
ፆም የሚባሉ ሰባት አፅዋማት አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም በጊዜው ረዥም
ደግሞም በስያሜው የተለየውን አብይ ጾምን እንመ
1. ዐብይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው
በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ
የተገኘ ነው፡፡
ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡
2. ዐብይ ጾም ለምን ዐቢይ ተባለ
ዐብይ ጾም ዐብይ የተባለበት ሦስት አበይት ምክንያቶች እንመለከታለን
2.1. ጌታቸን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ሥለሆነ ማቴ
4፡2-3
2.2. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት ስለ ሚበልጥ የቀኑ ብዛትም 55
ቀን ነው፡፡
2.3. ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት
የሚባሉት ትዕቢት፣ስስት ፍቅረ ነዋይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል
የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡ ማቴ 4፡3-11
የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች
ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
+
°#ጾመ ሁዳዴ፡- #ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡
°#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል
°#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
°#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት ‹‹የመሸጋገሪያ ጾም፣ ‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››
+
#የዐብይ_ጾም_ሳምንታት
ዐብይ ጾም በያዘው በ55 ቀኑ ውስጥ 7 ቅዳሜና 8 እሁዶቸን ይዟል የእነዚህ የስምንቱ እሁዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
1፣ ዘወረደ
2፣ ቅድስት
3፣ ምኩራብ
5፣ ደብረዘይት
6፣ ገብረ ሔር
7፣ ኒቆዲሞስ
4፣ መጻጉዕ
8፣ ሆሳዕና
+++

ቀደምት ሊቃውንት ሁለት ዓይን የተሰጠን በአንዱ የራሳችን በሌላው
የሌላውን ለማየት ነው፡፡ ሁለት ጆሮ የተሰጠን በአንዱ የራሳችንን
በሌላው የሌላውን ለመስማት ነው፡፡ ሁለት እጅ የተሰጠን በአንዱ
ለመስጠት በሌላው ለመቀበል ነው፡፡ ሁለት እግር የተሰጠን በአንዱ
ወደራሳችን በሌላው ወደ ሌላው ለመሄድ ነው ይሉ ነበር፡፡
፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!

†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት
እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም
ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
++ የማኅጸን ውስጥ ሸንጎ +++

በ መምህር ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ

መንትያ ሕጻናት በእናታቸው ማኅጸን ውስጥ ተጸንሰው እየኖሩ ነው፡፡ አንደኛው ሕጻን ሌላኛውን ጠየቀው ‹‹ከማኅጸን ከወጣን በኋላ ሕይወት አለ ብለህ ታምናለህ?››
ሌላኛው መለሰ ፡- ‹‹እንዴታ! ከማኅጸን ከወጣን በኋላማ የሆነ ሕይወት ሳይኖር አይቀርም፡፡ ምናልባት አሁን ማኅጸን ውስጥ የምንቆየው ለዛኛው ሕይወት ራሳችንን እያዘጋጀን ሊሆን ይችላል፡፡›› አለው፡፡
‹‹የማይመስል ነገር!!›› አለ የመጀመሪያው ሕጻን፡፡ ‹‹ከማኅጸን ከወጣን በኋላ ሕይወት የሚባል ነገር የለም! እስቲ አስበው ከማኅጸን ውጪ የሚኖረው ምን ዓይነት ሕይወት ነው?›› አለ እየሳቀ፡፡
ሁለተኛው መለሰለት ‹‹እኔም አላውቀውም ግን እዚህ ካለው የተሻለ ብርሃን እዚያ ያለ ይመስለኛል፡፡ ምናልባት በዚያኛው ሕይወት በእግራችን ለመሔድ ፣ በአፋችን ለመጉረስ የምንችል ይመስለኛል፡፡ ምናልባት አሁን ልንረዳቸው የማንችላቸው ሌሎች ስሜቶችም ሊኖሩን ይችሉ ይሆናል፡፡››
የመጀመሪያው ሕጻን በብስጭት ቀጠለ ‹‹ይኼ ቅዠት ነው፡፡ በእግር መሔድ የማይቻል ነገር ነው፡፡ ጭራሽ በአፍ መጉረስ? የማይሆን ነገር ታወራለህ እንዴ?! ምግብ የምንበላውንና የሚያስፈልገንን ነገር የምናገኘው በእትብታችን በኩል ነው፡፡ እትብታችን ደግሞ በጣም አጭር ነው፡፡ ከማኅጸን ከወጡ በኋላ ሕይወት አለ የሚለው ነገር አሳማኝ አይደለም፡፡››
ሁለተኛው ሕጻን ግን ውትወታውን ቀጠለ ‹‹እኔ ግን የሆነ ነገር የሚኖር ይመስለኛል፡፡ ምናልባት ማኅጸን ውስጥ ካለው ነገር የተለየ ነገር የሚኖር ይመስለኛል፡፡ ምናልባትም እትብትም ላያስፈልገን ይችል ይሆናል፡፡››
የመጀመሪያው ሕጻን ግን አልተረታም ‹‹አይዋጥልኝም! እሺ የምትለውን ልቀበልህና እንዳልከው ከማኅጸን ውጪ ሕይወት ካለ እዚያ ደርሶ የተመለሰ ሰው ለምን አናገኝም? ከማኅጸን መውጣት የሕይወት መጨረሻ ነው፡፡ ከማኅጸን ከወጣን በኋላ በጨለማ ውስጥ በዝምታ ከመጣል በስተቀር ምንም ነገር የለም፡፡ ወዴትም አንሔድም!››
‹‹በእርግጥ ምንም አላውቅም›› ቀጠለ ሁለተኛው ሕጻን ‹‹ነገር ግን ከማኅጸን ከወጣን በኋላ እናታችንን እናገኛለን፡፡ እስዋ ትንከባከበናለች፡፡››
‹‹እናት? በእናት መኖር ከልብህ ታምናለህ ማለት ነው? በጣም የሚያስቅ ነገር ነው!!! እሺ እናት ካለች አሁን የት ነው ያለችው?
ሁለተኛው ቀበል አድርጎ ‹‹እናታችንማ በዙሪያችን አለች፡፡ በእርስዋ ተከብበን ነው ያለነው፡፡ የተገኘነው ከእርስዋ ነው፡፡ የምንኖረውም በእርስዋ ውስጥ ነው፡፡ ያለ እርስዋ ያለንበት የማኅጸን ውስጥ ዓለም ሊኖር አይችልም፡፡›› አለው፡፡
‹‹አላየኋትማ! የት አለች? ስለዚህ አለች የሚለው ነገር አሳማኝ አይደለም!›› አለ የመጀመሪያው ሕጻን
ሁለተኛው ሕጻን ግን ይህን አለ ‹‹በማኅጸን ውስጥ ስትኖር አንዳንድ ጊዜ በዝምታ ውስጥ ሆነህ በጥሞና የምታዳምጥ ከሆነ የእናትህን መኖር ትገነዘባለህ ፤ በፍቅር የተሞላ ድምጽዋን ከላይ ሆኖ ሲጠራህ ትሰማዋለህ›› ብሎ ክርክሩን ቋጨው፡፡
ይህች ዓለም እንደ ማኅጸን ናት ፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ለወዲያኛው ኑሮ የምንዘጋጅበት አጭር ጊዜ ነው፡፡ ብዙዎች ለማመን ቢቸገሩም ከሞት በኋላ ዘላለማዊ ሕይወት አለ ፤ በጥሞና በተመስጦ ከፈለግነው የዓለም መጋቢና ሠራዒ አምላክ ልዑል እግዚአብሔርም አለ፡፡ የምንሞትበት ቀን ከጠባቡ ወደ ሰፊው የምንሔድበት ለዘላለም ሕይወት የምንወለድበት የልደታችን ቀን ነው፡:
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት።
ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።

ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው።
"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል?

"የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት ይባላል? ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን?

በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን? በፍጹም አይሆንም! የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን? እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ?

አባ ጊዮርጊስ "ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣ ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ?" ይል የለምን? ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም።

"ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ" (መዝ 48:12)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 13-የሀገረ ሶርያው ሰማዕቱ ቅዱስ አውሳብዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም ‹‹ሁለተኛው አውሳብዮስ›› የሚባለው ሲሆን መናኔ መንግሥት ወብዕሲት ነው፡፡ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከሞት አስነሥተውት በሰማይ 14 ዓመት ተመልሶ ወደ ምድር መጥቶ 40 ዓመት የኖረ ሲሆን በተአምራቱና በትምህርቱ 85 ሺህ አረማውያንን አሳምኖ ያጠመቀ ነው፡፡
+ የከበረ ቅዱስ ሰርግዮስ ከእናትና ከአባቱ ከወንድሞቹም ጋር በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት በአባቱ በህርማኖስ ትእዛዝ ሰማዕትነትን የተቀበለው ታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፊቅጦር ልደቱ ነው፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ሰርግዮስ፡- የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አባቱ ቴዎድሮስና እናቱ ማርያም ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ እርሱንም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር አሳደጉት፡፡ ቅዱስ ሰርግዮስ 20 ዓመት ሲሆነው በጌታችን ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ ወደደ፡፡ በከሃዲውም መኮንን በቆጵርያኖስ ፊት ቀርቦ የጌታችንን እውነተኛ አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ ጽኑ ሥቃይን ካሠቃየው በኋላ አሠረው፡፡ በእስር ቤትም ሳለ ጌታችን የቅዱስ ሰርግዮስን ነፍስ ወደ ሰማይ አምጥቀው የቅዱሳን ሰማዕታትን መኖሪያ ያሳዩአት ዘንድ መላእክቱን አዘዛቸው፡፡ የቅዱስ ሰርግዮስ ነፍስ የዘላለም መኖሪያዋን አይታ ተጽናናች፡፡ በሥጋውም ከሕማሙና ከቁስሉ ሁሉ ተፈወሰ፡፡
ቀሲስ አባ መጹን እና ሁለት ዲያቆናት የቅዱስ ሰርግዮስን ተጋድሎ በሰሙ ጊዜ ተነሥተው ወደ ከሃዲው የአትሪብ ገዥ በመሄድ በጌታችን ታመኑ፡፡ መኮንኑም ሕዝቡ በተሰበሰበበት የጸና ግርፋትን ገረፋቸው፡፡ ሕዝቡም ስለቄሱና አብረውት ስላሉት ሰማዕታት ሲያዝኑ ዞሮ ገሠጻቸውና በሃይማኖት ጸንተው መኖር እንዳለባቸው ነገራቸው፡፡ በውኃም ላይ ጸሎት አደረገና በሕዝቡ ላይ በረጨ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ከዚያም የጌታችን አምላክነት በመመስከር ጮኹ፡፡ መኮንኑም እጅግ ተናዶ ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጣቸውና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ ቄሱን ግን ይዞ ከውሽባ ቤት የእሳት ማንደጃ ውስጥ ጨመረው፡፡ የታዘዘ መልአክም መጥቶ በጌታችን ስም 3 ጊዜ ምስክር እንደሚሆን ነግሮት ከእሳት አወጣው፡፡ መኮንኑም ቄሱን ወደ እስክንድርያ ልኮት ቄሱ ምስክርነቱን በዚያ ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀዳጀ፡፡
ከዚህም በኋላ መኮንኑ ቆጵርያኖስ የከበረ ቅዱስ ሰርግዮስን ከእስር አውጥቶ እጅግ አሠቃየው፡፡ የነሐስ መንኮራኩሮችን አምጥተው ከውስጣቸው አስገብተው አበራዩት፤ ሕዋሳቱም 4 ክፍል ሆኖ ሥጋው ሁሉ ተቆራረጠ፡፡ ነገር ግን ጌታችን ፈወሰውና ያለ ምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ አስነሣው፡፡ ዳግመኛም እንዲሰግዲለት ጣዖትን አመጡ፡፡ ቅዱስ ሰርግዮስ ግን ጣዖቱን ቢረግጠው ከመሬት ወድቆ ደቀቀ፡፡ ‹‹አምላኬ›› ብሎ ያመልከው የነበረው መኮንኑ ቆጵርያኖስ ይህንን ሲያይ በመገረም ‹‹አምላክ ቢሆንስ ራሱን እንኳን ባዳነ ነበር ከእንግዲህስ በሰርግዮስ አምላክ አምኛለሁ›› ብሎ መሰከረ፡፡
ከዚህም በኋላ የንጉሡ የጭፍሮች አለቃ የከበረ ቅዱስ ሰርግዮስን ፈልጎ ያዘውና ቆዳውን ገፎ በተቀቀለ ኮምጣጤና ጨው ቁስሉን በማሸት በእጅጉ አሠቃየው፡፡ ነገር ግን ጌታችን መከራውን ያስታግስለትና ያጸናው ነበር፡፡ የቅዱስ ሰርግዮስን ተጋድሎ ሰምተው እናቱና እኅቱም ወደ እርሱ መጥተው ባዩት ጊዜ አለቀሱ፡፡ ከኀዘንም ብዛት እኅቱ ነፍሷ አለፈች፡፡ እናቱም ወደ ጌታችን በጸለየች ጊዜ ድና በሕይወት ተነሣች፡፡ በዚያንም ወቅት የሰማዕታትን ገድል የሚጽፍ የከበረ ዮልዮስ መጣ የቅዱስ ሰርግዮስን ገደል ከራሱ ተረዳ፡፡ ስለ ሥጋውም እንደሚያስብ ቃል ገባለት፡፡ ከዚህም በኋላ የከበረ ቅዱስ ሰርግዮስን በመንኮራኩር ውስጥ አሠቃዩት፡፡ በጆሮቹም የእሳት መብራቶችን ጨመሩበት፣ የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች በጉጠት ነቀሏቸው፡፡ በአንገቱም ከባድ ድንጋይ አንጠልጥለው ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከታች እሳት አነደዱበት፡፡ በዚህም ወቅት ጌታችን ከመከራው አስታግሶ ጤነኛ አድርጎ አስነሣው፡፡ ይህንንም ያዩ ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡ የጭፍሮቹም አለቃ ቅዱስ ሰርግዮስን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡ ቅዱስ ሰርግዮስም ይህንን ሲሰማ እጅግ ደስ ተሰኘ፡፡ አባቱና እናቱ ወንድሞቹም ከሀገሩ ሰዎች ጋር ሆነው ሊሰናበቱት መጡ፡፡ አፉን በልጓም ለጉመው ወደሚሰየፍበት ቦታ ሲወስዱት ደረሱ፡፡ እነርሱም የንጉሡን ጣዖታት ረገሙ፡፡ የጭፍሮቹም አለቃ የቅዱስ ሰርግዮስ ቤተሰቦችን ከእርሱ ጋር አብረው እንዲሰየፉ አዘዘና ሁሉም ተሰይፈው በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ፡፡
በሰማዕትነታቸውም ወቅት እንዲህ ሆነ፡- ከሕዝቡ ውስጥ አንድ ታናሽ ሕፃን እግዚአብሔር ዐይኖቹን ገልጦለት የቅዱሳን ሰማዕታትን ነፍሶቻቸውን መላእክት ወደ ሰማያት ሲያወጧቸው አይቶ ‹‹ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!›› እያለ በከፍተኛ ቃል ጮኸ፡፡ እናትና አባቱም የጭፍሮቹ አለቃ የሕፃኑን ድምጽ ሰምቶ እንዳያጠፋቸው አፉን አፈኑት፡፡ ነገር ግን ሕፃኑ በላዩ እስከተኙበትና ነፍሱን እስካሳለፈ ድረስ በመስከር መጮኹን አላቆመም ነበር፡፡ ከሰማዕታቱም ጋራ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ አውሳብዮስ ዘሀገረ ሶርያ፡- ይኽም ቅዱስ የሶርያው መስፍን ልጅ ነው፡፡ ወላጆቹ በተግሣጽና በጥበብ ካሳደጉት በኋላ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ በታላቅ ክብር አጋቡት፡፡ በሠርጉም ዕለት መንፈስ ቅዱስን የተመላች ቅድስት ወደሆነችው እኅቱ ወደ አውሎፊያ ዘንድ ገብቶ ‹‹እስቲ ምከሪኝ ልቤ ይህን ጋብቻ አይሻውም ዓለምን ንቆ መተውን እንጂ›› አላት፡፡ እኅቱም ‹‹የዚህ የኃላፊው ዓለም ጣዕም ምን ይጠቅምሃል? እንደ ሊቀጳጳሳት ድሜጥሮስ በድንግልና መኖር ይሻልሃል›› አለችው፡፡ ምሽትም በሆነ ወደ ሙሽራይቱ ጫጉላ ቤት ገብቶ የእነርሱ ውበትና ደምግባት እንደሚጠፋ ከዚህም ይበልጥ የሚጠቅማቸውን የጽድቅ ሥራ በመሥራት ድንግልናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ሙሽራይቱን አዋያት፡፡ ሙሽራይቱም በሀሳቡ ተስማምታ ድንግልናቸውን በመጠበቅ በጾም በጸሎት እየዋሉ ሌሊትም ከባሕር ውስጥ ገብተው ቆመው ሲጸልዩ ያድሩ ጀመር፡፡ አትራ ወደምትባል ቤተ ክርስቲያን ሄደው አራት እልፍ ይሰግዳሉ፡፡
በአንዲት ዕለት የሶርያው ንጉሥ ሚስት ቅዱስ አውሳብዮስን አይታው እጅግ ወደደችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ ሁለቱን ልካ ካስመጣችው በኋላ በወርቅ አጊጣ በሐር በተነጠፈ አልጋ ላይ ሆና ጠበቀችው፡፡ ከእርሷም ጋር እንዲተኛ ስትጠይቀው ‹‹እኔስ ሚስቴንም እንኳን በግብር ያላወኩ ነኝና ተይኝ ንጉሡ ባልሽ በቤት ባይኖር ሰውም ባያየን እግዚአብሔር ግን ያየናልና እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ?›› በማለት ትቷት ሊወጣ ሲል ልብሱን ያዘችው፡፡ እርሱም ሮጦ በማምለጥ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ እርሷ ግን በመጮህ ባሮቿ ሲመጡላት ‹‹ክፉ ነገርን አድርጎብኝ ሄደ›› ብላ በሐሰት ተናገረች፡፡ ጭፍሮቿም ቅዱስ አውሳብዮስን ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው እየደበደቡ ወደ ንግሥቲቱ አመጡት፡፡ እጆቹንና እግሮቹንም አሥረው ከከተማ ውጭ በአራት ዕንጨቶች ላይ አሰቀለችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ አንዲቱ በንግሥቲቱ ተልካ ሄዳ አውሳብዮስን ‹‹ከተሰቀልክበት እንዲታወርድህ ለእመቤቴ ያለችህን እሺ በላት›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹የአመንዝራን ቃል አልሰማም›› አላት፡፡ ንግሥቲቱም እሺ እንዳላላት ስታውቅ አንገቱን በገመድ አሳንቃ 160 ፍላጻዎችን በሰውነቱ ውስጥ እንዲጭምሩበት
አደረገች፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮለት ፍላጻዎቹን ከሰውነቱ ውስጥ አወጡለትና ፍጹም ጤነኛ ሆነ፡፡
ንጉሡም ከሄደበት ሲመለስ ንግሥት ሚስቱን አውሳብዮስን ለስቅላትና ለሞት ያበቃችው በምን ምክንያት እንደሆነ ሲጠይቃት ‹‹አንተ በሌለህበት ወደ መኝታ ቤቴ ገብቶ ሊናገሩት የማይገባ ነገር ጠየቀኝ በከለከልኩትም ጊዜ በሥራዩ አሳመመኝ›› አለችው፡፡ ንጉሡም ተቆጥቶ ቅዱስ አውሳብዮስን ከተሰቀለበት አስወርዶ ካስመጣው በኋላ ለምን ይህን እንዳደረገ ጠየቀው፡፡ አውሳብዮስም እውነቱን በነገረው ጊዜ ጭፍሮቹን ምስክር ይሆኑ ዘንድ ሲጠይቃቸው ንግሥቲቱ ስትጮህ ወደ ውስጥ ሲገቡ ያጋጠማቸውን መሰከሩ፡፡ ንጉሡም የሚስቱን ነገር አምኖ በመቀበል በንዴት የቅዱስ አውሳብዮስን ሰውነቱን በሰይፍ አስቆርጦ ሥጋውን እንደ ላም ሥጋ ቆራርጦ በምንቸት አድርጎ በእሳት እንዲበስል አደረገው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከምቸቱ አውጥተው ከሞትም አድነው በማስነሣት ፍጹም ጤነኛ አደርገው አቆሙት:: ከሞት ከተነሣም በኋላ በሀገሩ ውስጥ ሲሄድ ሰዎች አይተውት ለንጉሡ ስለነገሩት ንጉሡ ድጋሚ ካስመጣው በኋላ አራት ዛንጅሮች በአካላቶቹ ውስጥ በማስገባት እጅና እግሩን አሳስሮ በእሳት ውስጥ ጨመረው፡፡ የከበሩ ሁለቱ ቅዱሳን መላእክት አሁንም መጥተው ፈወሱት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14 ዓመት ኖረ፡፡ ከዚያም ወደ ምድር ተመልሶ መጥቶ ወንጌልን እያስተማረ 40 ዓመት ኖረ፡፡ በእርሱም ትምህርት 85 ሺህ አረማውያን አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ቅዱስ አውሳብዮስ በመጨረሻ ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን ፈጽሞ የካቲት 13 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ እስከ ሰባት ትውልድ እንደሚምርለት ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶለታል፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ አውሳብዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ዳግመኛም በዚህች ዕለት በአባቱ በህርማኖስ ትእዛዝ ሰማዕትነትን የተቀበለው ታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፊቅጦር ልደቱ ነው፡፡ (የዕረፍቱን ዕለት ሚያዝያ ሃያ ሰባትን ገጽ — ላይ ይመለከቷል)
የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ባለሟል በነበረው በገዛ አባቱ እጅግ ተሠቃይቶ ምስክርነቱን የፈጸመው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፊቅጦር ዕረፍቱ ነው፡፡ ኅርማኖስ የተባለው ወላጅ አባቱ የክርስቲያኖችን ደም እንደ ውኃ ያፈስ የነበረው የዲዮቅልጥያኖስ ልዩ አማካሪና የሠራዊቱ አለቃ ነበር፡፡ እናቱ ማርታ ግን በክርስቶስ አምና የተጠመቀች ክርስቲያን ነበረች፡፡ እንዲያውም ልጇን ቅዱስ ፊቅጦርን ከመውለዷ በፊት የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ወዳለበት ሄዳ ‹‹እመቤቴ ማርያም ለኢየሱስ ክርስቶስ ደስ የሚያሰኘውን ልጅ ስጪኝ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ደስ የማያሰኝ ልጅ ከሆነ ግን ማኅፀኔን ዝጊልኝ›› ብላ በጸለየችው ጸሎት ነው ቅዱስ ፊቅጦርን ያገኘችው፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር በዓለም ላይ ያሉ በክርስቶስ ያመኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን ንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ በግፍ ያስገድል በነበረበት ወቅት የተገኘ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡ ፊቅጦርን ገና 15 ዓመት እንደሆነው ንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ ‹‹ከፍ ባለ ስልጣን አስቀምጥሃለሁ፣ እጅግ ብዙ ወርቅና ንብረትም እሰጥሃለሁ፣ በእስክንድርያም ላይ ገዥ አድርጌ እሾምሃለሁ ክርስቶስን ማመንህን ተውና ወደ ቤተ መንግሥቴ ግባ›› ቢለውም ቅዱስ ፊቅጦር ግን ብዙ መከራንና ሥቃይን ተቀብሎ ሰማዕት መሆንን መረጠ፡፡ ቅዱስ ፊቅጦርም ዲዮቅልጥያኖስን ‹‹ክርስቶስን በምታፈቅረው ጊዜ አፈቀርኩህ ወደ አንተም መጣሁ፤ ክርስቶስን በጠላኸው ጊዜ ግን እኔም ጠላሁህ፣ ቤትህንም ጠላሁ›› ብሎታል፡፡
ከብዙ ጊዜም በኋላ ዲዮቅልጥያኖስ ቅዱስ ፊቅጦርን በመንግሥቱ ውስጥ ሦስተኛ ማዕረግ አድርጎ ሾመው፡፡ እርሱ ግን ይጾማል ይጸልያል እንጂ በንጉሡ ቤት አይበላ አይጠጣም ነበር፡፡ ዕድሜውም 27 ብቻ ነበር፡፡ አባቱንም ከጣዖት አምላኪነቱ እንዲመለስ ቢመክረው ሄዶ ለንጉሡ ከሰሰው፡፡ ፊቅጦርም ‹‹ለአንተ ለጣዖት አምላኩ አገልጋይ አልሆንም›› በማለት በንጉሡ ፊት ትጥቁን ፈቶ ጣለ፡፡ የቅዱስ ፊቅጦር ወላጅ አባቱ ኅርማኖስ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ የቅርብ እንደራሴና መስፍን ስለነበር ልጁ ፊቅጦርን የንጉሡን ሹመትና ልመና እንዲቀበል ብዙ ሲያግባባው ነበር፡፡ አባቱም ልጁ በሀሳቡ እንዳልተስማማለት ሲያውቅ ከዲዮቅልጥያኖስ ጋር ተማክሮ ልጁን ቅዱስ ፊቅጦርን ወደ እስክንድርያና ወደ ተለያዩ ሀገሮች በግዞት ተልኮ በዚያም ተሠቃይቶ እንዲሞት ፈደበት፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
የካቲት 14-ሃይማኖታቸው ለቀና ምእመናን ሁሉ መምህራቸው የሆኑ የአንጾኪያው ሊቅ አቡነ ሳዊሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 14-ሃይማኖታቸው ለቀና ምእመናን ሁሉ መምህራቸው የሆኑ የአንጾኪያው ሊቅ አቡነ ሳዊሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ እርሳቸውም በትምህርታቸውና በተአምራታቸው ቤተ ክርስቲያንን እንደፋና አብርተውላት በዓለም መድረክ አንድ ያደረጓት ናቸው፡፡
+ አፎን በሚባለው ሀገር የሚኖረውንና መቃርስ የሚባለውን ሰው የሞተ ልጁን በጸሎታቸው ከሞት ያስነሡለት አባ ያዕቆብ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ልጁ ከሞት የዳነለት መቃርስም ለምጽዋት ብሎ ግማሽ ንብረቱን ቢሰጣቸው ለምእመናን ማሪፊያ መጠጊያ የምትሆን ቤተ ክርስቲያን ሠርተውበታል፡፡ እኚህም አባ ያዕቆብ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 50ኛው ናቸው፡፡
አቡነ ሳዊሮስ፡- እጅግ ክቡር የሆኑት የአንጾኪያው ታላቁ አባት የአቡነ ሳዊሮስ ትውልዳቸው ከሮሜ ሀገር ሲሆን አባታቸው ሳዊሮስ የሚባሉ ኤጲስ ቆጶስ ናቸው፡፡ አባታቸው ሳዊሮስ ስለ ንስጥሮስ የከፋ ክህደት በኤፌሶን ከተማ ጉባኤ በተደረገ ጊዜ ከሁለት መቶው እጅግ ከከበሩት ሊቃውንት ቅዱሳን አባቶች ጋር ተሰብስበው ሃይማኖትን አቅንተዋል፡፡ ንስጥሮስንም በቃላቸው ትምህርትና የተለያዩ ተአምራትን እያሳዩ አስተምረው ሊያሳምኑት ቢሞክሩ ሰይጣን በልቡ ስላደረ ከክህደቱ ሊመለስ አልቻለም ነበርና ቤተ ክርስቲያንን እንዳያውክ ምእመናንም በክህደት በመርዙ እንዳይበክል ብለው ቅዱሳኑ በኅብረት አውግዘው ለዩት፡፡
ታላቁ አቡነ ሳዊሮስም ለጉባኤው በኤፌሶን ከተማ እንደመጡ ‹‹ከአንተ የሚወለድ ልጅህ ስሙም እንደ ስምህ ሳዊሮስ ተብሎ የሚጠራ ልጅህ የቀናች ሃይማኖትን ያጸናታል›› የሚል ታላቅ ራእይን ተመለከቱ፡፡ ይህም ታላቁ አቡነ ሳዊሮስ ባረፉ ጊዜ ልጃቸውን ሳዊሮስ ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም ከቤተ ክርስቲያን ውጭ የሆኑትን የጥበብና የፍልስፍና ትምህርቶቸን በሙሉ ጠንቅቆ ተማረ፡፡ በአንዲት ዕለትም ከመምህሩ ዘንድ ወጥቶ በመንገድ ሲጓዝ በዋሻ ውስጥ የሚኖርና ራሱን እስረኛ ያደረገ አንድ ታላቅ ጻድቅ ሰው አገኘ፡፡ ያም ጻድቅ ሰው ሳዊሮስን ‹‹የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሃይማኖታቸው ለቀና ምእመናን መምህራቸው የሆንክ ሳዊሮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው›› አለው፡፡ ያም ጻድቅ ሰው ሳዊሮስን ከነጭራሹ ሳያውቀው በስሙ ስለጠራውና የሚደረግለትንም ከመሆኑ አስቀድሞ ትንቢት በመናገሩ በጣም ተደነቀ፡፡
ከዚህም በኋላ ሳዊሮስ የትሩፋት ሥራዎችን መሥራት ጀመረ፡፡ ወደ አቡነ ሮማኖስ ገዳም ገብቶ መነኮሰና በጾም በጸሎት በእጅጉ ይተጋ ጀመር፡፡ በገዳሙም ጽኑ በሆነ በመንፈሳዊ ተጋድሎ እየበረታ ሲሄድ ዜናው በሁሉ ዘንድ መሰማት ጀመረ፡፡ የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳሳት በሞት ባረፉ ጊዜ የከበሩ ሊቃውንት ኤጲስቆጶሳት በአንድ ሀሳብ ሆነው ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው አቡነ ሳዊሮስን የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ይሾሙት ዘንድ ወደዱ፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔርም ያለ ፈቃዱ በግድ ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት፡፡
በአቡነ ሳዊሮስ በሹመታቸው ዘመን እስከ ዓለም ዳርቻ ያለች ቤተ ክርስቲያን ብርሃን ሆኑላት፡፡ የመለኮት ነገር የሚናገሩት ድርሰቶቻው እጅግ ድንቅ ናቸው፡፡ በየሀገሩ ወዳሚገኙ መናፍቃን ከሃድያን ትምህርታቸው በሚደርስ ጊዜ ሁለት አፍ እንዳለው ስለታም ሰይፍ ሥራቸውን ይበጥሳልና፡፡ የአቡነ ሳዊሮስን ትምህርታቸውን የሰማ መናፍቅ በውስጡ ያደረበት የጥርጥር መንፈስ መድረሻ ያጣል፡፡ አቡነ ሳዊሮስ በትምህርታቸውና በተአምራታቸው ቤተ ክርስቲያንን እንደፋና አብርተውላት በዓለም መድረክ አንድ አድርገዋታል፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ጠያቂ፡-ጠበል ምንድን ነው?

ኦርቶዶክስ፡– ጠበል ማለት በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ህሙማን የሚፈወሱበት ተአምራት የሚደረጉበት ቅዱስ ውሃ ነው::

ጠያቂ፡–መጽሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለህ?

ኦርቶዶክስ ፡- በሚገባ..ንዕማን ለምጻም እንደነበር እና በጠበል ሐይል እንደዳነ መጽሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል
"ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፥ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ። ኤልሳዕም ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህም ይፈወሳል፥ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ…… ወረደም፥ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ።”2ነገሥት 5፡1-19
እንዲሁም ክርስቶስ በ ዮሐንስ 9:1-8
"ኢየሱስ ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና። ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው… ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።
ክርስቶስ በቃሉ ብቻ አይንህ ይብራልህ ብሎ ማዳን ይችላል ግን በብሉይ ኪዳን ህመምተኞች ይፈወሱበት ፣ተአምራት ይደረግበት የነበረው ጠበል በሐዲስ ኪዳንም የተባረከና ፈቅዶ የሰጠን ጸጋ መሆኑን ለማስረዳት “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው፡፡

ጠያቂ ፡— ታዲያ ጠበሎች ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠራት ሲኖርባቸው ለምን የማርያም ጠበል፤የሚካኤል ጠበል ፤የጊዮርጊስ ጠበል ይባላል?

ኦርቶዶክስ ፡–መልሱ አጭር ነው ይኸውም በጠበሉ ቅዱሳን እንዲታሰቡበት ነው

ጠያቂ ፡–መጽሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለህ?

ኦርቶዶክስ ፡- አዎ በሚገባ ..ቅድስት ቤተክርስትያን ሁሉ ነገሯ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ነው
"እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና። በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።”(ኢሳይያስ 56:4-5 )
እንዲሁም “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” (ምሳሌ 10:7) በሚለው መጽሀፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሰረት በጸበሉ ቅዱሳኑ መጠራታቸው መታሰቢያቸው እንዲሆን ነው፡፡ጠበሉን የፈጠረው መድሐኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እና በጠበሉም አድሮ ህሙማንን የሚፈውሰው እና ተአምራትን የሚያደርገው የእግዚአብሔር ሐይል መሆኑን በደንብ እናውቃለን፡፡

ጠያቂ–አመሰግናለው ወንድሜ

ኦርቶዶክስ–ቅድስት ቤተክስትያን ለሁሉም ጥያቄ መልስ አላት፣ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቀደመችው እውነተኛይቱ መንገድ! ለኛ ለምናምነው ፀበሉን በእምነትና በንፅህና በፈሪሃ እግዚአብሔር ከተጠቀምንበት ፈውስ እንደሚሆነን አንጠራጠም።ፀበሉ ሁላችንን ከስጋዊና ከመንፈሳዊ ደዌ ይፈውሰን! ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር!!!
ተዋህዶን እንደኔ የምትወዱና በተዋህዶ መልስ ሁሌም የምትኮሩ የተዋህዶ ልጆች መልዕክቱን share አድርጉ! እግዚአብሔር ሁላችንን በተዋህዶ ያፅናን! እኛን በጎቹን ከነጣቂ ተኩላዎች ይጠብቀን!!! https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
🌺 የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አትጥራ!

የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት ሲባል ምን ማለት ነው? የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም የከበረ በመሆኑ እንደተገኘ የሚጠሩት፣ እንደአጋጠመ የሚናገሩት አይደለም፡፡ ይልቁንም በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በትሕትና ሆነው ሊጠሩት የሚገባ ክቡር ስም ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም ያለአግባብ በነገራቸው ሁሉ ውስጥ ሲያስገቡት፣ ሥፍራም ጊዜም ሳይመርጡ እንደፈለጉት ሲጠሩት ይስተዋላሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች እምነትና ፊሪሃ እግዚአብሔር አላቸው ለማለት አያስደፍርም፤

ከዚህ ቀጥለን ሰዎች ስሙን በከንቱ የሚጠሩባቸውን ሁኔታዎች ባጭር ባጭሩ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ሀ. መሐላ፡- መሐላ ስመ እግዚአብሔር በከንቱ ከሚጠራባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡ በዘመነ ብሉይ የአምልኮ ጣዖትን ከንቱነት ለመግለጥ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡ በስሙ እንዲምሉ ያዝዝ ነበር (ዘዳ 6&13፤ ኢሳ 45&23)፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ በእግዚአብሔር መማል ብቻ ሳይሆን መሐላ በጠቅላላው የተከለከለ መሆኑን መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ ይህ የሐዲስ ኪዳን ዘመን አረማዊነትና አምልኮ ጣዖት ጠፍቶ ወንጌል የተሰበከበት፣ ክርስትና በዓለም ሁሉ የታወቀበት ነውና መማል አላስፈለገም፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ #ከቶ አትማሉ፤… ቃላችሁ አዎን፣ አዎን ወይም አይደለም፣ አይደለም ይሁን፣ ከዚህም የወጣ ከክፉው ነው$ በማለት መሐላን ከልክሏል (ማቴ 5&34-37)፡፡ ስለሆነም በየሰበቡ የእግዚአብሔርን ስም፣ የቅዱሳንን ስም፣ የመላእክትን ስም ሁሉ እየጠሩ መማል የተከለከለ ነውና ከዚህ መቆጠብ ይገባል፡፡ በተለይም በየአጋጣሚው ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ መማል የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት መሆኑን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
"ደብረ ዘይት"

👉አምስትኛው ሳምንት

ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡
ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ
የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:-ደብረ ዘይት
(የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ
ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ
ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ
ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሰረት
ነገረ ምጽአቱን (የመምጣቱን ነገር) እንድናስታዉስ ወይም
እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነዉ።
ጌታችን “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ
በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያዉቅ
የለም” ማቴ. 24፡36 ብሏል። ይህን ማለቱም በየዘመኑ
የሚነሱ ክርስቲያኖች ሩቅ ነዉ ብለዉ እንዳይዘናጉ ጊዜዉ
ሲቀርብ የሚነሱት ደግሞ ደረሰብን ብለዉም እንዳይሸበሩ/
እንዳይታወኩ ለመጠበቅ ነዉ። ከላይ እንደጠቀስነው ጌታችን
በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸዉ ወደ
እርሱ ቀርበዉ “የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱ
ምንድር ነዉ? አሉት።” ማቴ. 24፡3 እርሱም በስፋትና
በጥልቀት ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ
ምልክቶች አስተማራቸዉ። https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ወዳጄ ያለህን ሁሉ ልብ ብለህ ተመልከት!

ከጎንህ ያለች ሚስትህ - የላጤዎች ምኞት ናት

ያልተደሰትክበት ልጅህ - መውለድ የማይችሉ ምኞት ነው

ትንሿ ቤትህ - ቤት የሌላቸው ና በጎዳና የሚኖሩ ምኞት ናት

አድካሚ ስራህ - ስራ የሌላቸው ምኞት ነው

ውድ የሆነው ጤናህ - ጤና ለአጡ ሁሉ ምኞት ነው

ደስታህ ና ሳቅህ - የአዘኑ ና የተጨነቁ ምኞት ነው

ፈጣሪ የደበቀልህ ነገር - የተዋረዱትና የተጋለጡት ምኞት
ነው

በነፃነት መንቀሳቀስህ - በእስር ያሉ ሁሉ ምኞት ነው።

ወዳጄ ሆይ አስተውል አንተ ያለህ የሌላቸው ብዙዎች አሉና ስላለህ ነገር ሁሉ ማመስገንን አትርሳ!!! https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ብዙ ሰዎች ደስ ተሰኝተውና እርስ በእርሳቸው፡- “ግማሹን ጾም ፈጽመናል፤ የጾሙ እኩሌታ አለፈ” ሲባባሉ ተመልክቻለሁ፡፡ እኔ ግን እነዚህ ሰዎች በዚሁ ምክንያት ደስ ሊላቸው እንደማይገባ እመክራቸዋለሁ፤ የጾሙ እኩሌታ ማለፉን ሳይኾን የኃጢአታቸው እኩሌታ መኼዱን [መወገዱን] ያስቡ፤ እንደዚያ ከኾነም ሐሴት ያድርጉ፡፡ ደስ ልንሰኝበት የተገባው ነገር ይኼ ነውና፡፡ ሊታይ የሚገባው ይኼ ነው፤ ጥንቱም እነዚህን ኹሉ ነገሮች የምናከናውናቸው ስሕተቶቻችንን እንድናስተካክል፣ ጾሙ ሲጀምር እንደ ነበርንበት ሳይኾን እንድንነጻበት፣ ክፉ ልማዶቻችንን ወደ ጎን አድርገን የተቀደሰውን በዓል [በዓለ ትንሣኤን] እንድናከብር ነውና፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ግን ጾሙን መጨረሳችን በራሱ ለእኛ ታላቅ ጉዳትን ይዞ ከመምጣት ውጪ ሌላ ምንም ረብ ጥቅም አይሰጠንም፡፡ ስለዚህ ብዙ ጊዜ መጾማችንን ብቻ አንመልከት፤ ይህ ምንም ትልቅ ነገር አይደለምና፤ ይልቁንስ በዚህ ጾም ራሳችንን አሻሽለን እንደ ኾነ፣ ጾሙ ከተፈታ በኋላም የዚሁ ፍሬ ጎምርቶ ይታይብን እንደ ኾነ ሐሴት እናድርግ፡፡ የክረምት ጥቅሙ ይበልጥ የሚታወቀው ወራቱ ካለፈ በኋላ ነውና፡፡ የዚያን ጊዜ የአበባው ማበብ፣ የአዝመራው ማፍራት፣ ሌሎች ዕፅዋትም በቅጠላቸውና በፍሬያቸው በወርሐ ክረምት ያገኙትን ጥቅም ግልጽ አድርገው ይናገራሉና! በእኛም ዘንድ ልክ እንደዚህ ይኹን፡፡ በወርሐ ክረምቱ በብዛትም በዓይነትም የተለያየ ዓይነት የዝናብ ጠብታዎችን ተቀብለናል፤ ብዙ ተከታታይ ትምህርቶችን ተምረናል፤ መንፈሳዊ አዝርእት ተዘርተዉብናል፤ የቅምጥልነት እሾኽም ቈርጠን ጥለናል፡፡
ስለዚህ ጾሙ በተፈታ ጊዜ የጾሙ ፍሬ ይከብበን ዘንድ፣ ከጾሙ የሰበሰብናቸውን መልካም ነገሮችም ጾሙን ራሱን እናስታውሰው ዘንድ የሰማነውን ነገር አጽንተን በመያዝ እንትጋ፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ፍቅር
.
..... ፍቅር ማለት ውበት አይደለም
==> ፍቅር ማለት ጥቅም ፍለጋ አይደለም
==> ፍቅር ማለት ዝሙት ፍለጋ አይደለም
==> ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍ አይደለም
==> ፍቅር ማለት ስለወደዱን መውደድ አይደለም
==> ፍቅር ማለት ስላከበረን ማክበር አይደለም
==> ፍቅር ማለት ስላገዘህ አንተም ቀን ጠብቀህ
ብድር መመለስ አይደለም
==> ፍቅር ማለት ከማንነት የፀዳ፤
==> ፍቅር ማለት ከማዳላት የራቀ፤
==> ፍቅር ማለት ከመፍረድ እጁን
ያወጣ፣በመከራም፣በሀዘንም
፣በጭንቀትም፣በደስታም፣መ
ተሳሰብ፣መተጋገዝ፣መረዳዳት...አንተ ያላገኘሀውን ነገር
ሌሎች እንዲያገኙት መመኘት፤ጠላትህን
መውደድ፣ስለወንድምህ እራስህን አሳልፈ
መስጠት፣የወንድምህን በደል መሸከም ባንተ እንዲፈፀም
የማትፈልገውን በሌላ አለመፈፀም..ተመልሶ በራስህ
መፈፀሙ አይቀርምና።።።።። https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
6ተኛ ሳምንት ገብር ኄር – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስያሜ የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ኄር ይባላል፡፡ ሰያሜውን የሰጠውም ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ጾመ ድጓ በተባለው ከአምስቱ መጻሕፍቶቹ አንዱ በሆነው ጾመ ድጓ መጽሐፍ ሳምንቱን የዐቢይ ጾም ሳምንታት ስያሜዎች ከነሥርዓተ ማኅሌቱ አዘጋጅቷል፡፡ ስለዚህ በስድስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ከዋዜማው ቅዳሜ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን፡- የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ገብርኄርን የሚያወሳ ነው ማለት ስለ ታማኝ አገልጋይ ነው፡፡ በማቴ.25፥14-25 የተገለጸውና በዕለቱ የሚነበበው ወንጌልም የሚነግረን ይህን ነው፡፡
“አንድ ባዕለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው፣ ሁለት መክሊት የሰጠውም አለ፣ አንድ መክሊትም የሰጠው አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሩቅ አገር ሄደ፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ አስር አደረገ፡፡ ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ፡፡ አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ በሻሽ ጠቅልሎ የጌታውን መክሊት ቀበራት፡፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጥቶ ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ አምስት አተረፍኩ አለው፡፡ “ገብርኄር ወምዕመን ዘበሁድ ምዕምነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እሰይመከ ባዕ ውስተ ፍስሐሁ ለእግዚእከ” “አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ ጌታዬ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ ወጥቼ ወርጄ ሌላ ሁለት አትርፌ አራት አድርጌአለሁ፡፡ “አንተ ታማኝ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡
አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ቀርቦ “ጌታዬ አንተ ክፉና ጨካኝ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ እንደሆንክ ስለአወቅሁ መሬቱን ቆፍሬ ቀበርኋት እነኋት መክሊትህ” አለው፡፡ “አንተ ሰነፍ ባሪያ መክሊቴን በጊዜ ልትሰጠኝ በተገባህ ነበር እኔም ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍ በሰጠሁት ነበር”፡፡
ንዑ የዚህን ሀኬተኛ መክሊት ውሰዱና አስር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ይሰጡታል ይጨመርለታል ለሌለው ግን ያለውን ይቀሙታል፡፡ ንዑ ይህን ሰነፍና ሃኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አሥራችሁ ጽኑዕ ጨለማ ወደአለበት ውሰዱት ጩኸትና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጨምሩት” አለ ማቴ.25፥14-25፡፡
ባዕለ ጸጋ የተባለው ጌታ ነው፡፡ መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ ያተረፉት በሚገባ በታማኝነት ያገለገሉ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው መክሊቱን የቀበረው ደግሞ በታማኝነት በተሰጠው ጸጋ ማገልገል ሲገባው ያላገለገለ ነው፡፡ ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው መጣ ማለት በዕለተ ምጽአት ለሁሉም በአገለገለው አገልግሎት ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ ያሳየናል፡፡
ያገለገሉትን ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አላቸው ማለት ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፡፡ ሰነፎች ደግሞ ጥርስ ማፋጨት ስቃይ ጽኑዕ ጨለማ ባለበት ሲዖል መግባታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ከላይ ያነሳነው የቅዱስ ወንጌል ቃል፡- “ታማኝ አገልጋይ ማነው”? ይህ እያንዳንዱ በአርዓያ እግዚአብሔር የተፈጠረ የሰው ልጅ ጥያቄ ነው የዚህን አምላካዊ ጥያቄ መልስ መስጠት ከሰው ልጆች ይጠበቃል፡፡
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ጊንጥ አና ጊንጠኞች!!
//ዳንኤል ክብረት//

ብዙ ጊዜ ጊንጥ የሚለውን ቃል ስሰማ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም ነበር ዛሬ ግን ጊንጥ አሪፍ ነገር አስተማረኝ፡፡ ይህንን እንድል ያስገደደኝ የዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አጭር ታሪክ ነው ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
አንድ ሽማግሌ ውሃ ውስጥ ሊሰምጥ ያለ ጊንጥ ያዩና ሊያድኑት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም ጊንጡን ከውሃው ለማውጣት እጃቸውን ዘርግተው አነሱት በዚህ ጊዜ ጊንጡ ነደፋቸው እሳቸውም ደንግጠው ለቀቁት ጊንጡም ተመልሶ ወደውሃው ገባ፡፡ ሽማግሌው አሁንም የጊንጡን ውሃ ውስጥ መስመጥ ተመልክተው ድጋሚ እጃቸውን ለእርዳታ ዘረጉለት አሁንም በድጋሚ ጊንጡ ነደፋቸው ሲለቁት አሁንም ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ ይህንን የሽማግሌውን ትእይንት የሚመለከት አንድ ሰው ወደ ሽማግሌው ጠጋ ይልና ‹‹ይህ እኮ ክፉ ፍጥረት ነው ጊንጥ እሱን ለማዳን ሲሉ እርሶ እየተጎዱ እኮ ነው›› አላቸው።
ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የጊንጡ ተፈጥሮ መናደፍ ነው፡ የኔ ተፈጥሮ ደግሞ መርዳትና ማገዝ ነው፡ ስለዚህ ተፈጥሮዬ ክፉ አደለምና ጊንጡን ከመርዳት አላቋርጥም አረዳዴን ግን አስተካክላለሁ›› አሉና ጥቂት አሰብ አድርገው ተነስተው ከዛፉ ላይ አንድ ቅጠል ቀንጥሰው በቅጠሉ ጊንጡን ይዘው አወጡትና ህይወቱን አተረፉለት፡፡
እኛም እንዲህ ነን ሰውን ለመርዳት ስንሄድ ብዙ ጊንጦች ይነድፉናል፡ ደግ ልናደርግ ስንጓዝ ብዙ እንቅፋቶች ይመቱናል፡፡ ነገር ግን ጊንጡ እንዳይነድፈን እናደርጋለን እንጂ እንቅፋቱ እንዳይመታን እንጠነቀቃለን እንጂ እንዴት ደግ ማድረግ እናቆማለን ???
አንተም አንቺም ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ ያለን ሰዎች በሙሉ ስንፈጠር ደግና መልካም ነን፡፡ ግን ሰውን ክፉ የሚያደርገው ተፈጥሮው ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ለዛ እኮ ነው በነዚህ ጊንጦች ስለተነደፍን መልካም ለማድረግ ቅስቀሳ በጎ ለመስራት ማጣራት መጠራጠር በሌላ አይን መመልከት ጀመርን፡፡
እስኪ የዛሬዋን አዲስ ቀናችንን እንዲህ ብንውላትስ ሰው ስንረዳ እንደጊንጥ በሚሆኑ ሰዎች ተሸንፈን መልካም ከማድረግ ከምንቆጠብ የምንረዳበትን መንገድ ለይተን ብናውቅስ፡፡ በነገራችን ላይ ለሰው በጎ ማድረግ ሲባል በገንዘብ ብቻ ይመስለናል አይደለም በየቤቱ ገንዘብ ኖሮት ሰው የናፈቀው ህሊና አለ ስለዚህ አንዳንዶች ፈገግታችንን አንዳንዶች እኛነታችንን አንዳንዶች መሰማትን ይፈልጋሉና በየደረስንበት ለመልካም ነገር ጊንጥ ፈርተን እምቢ እንዳንል፡፡
መልካም የምታደርጉ ሁሉ ግን ጊንጡንም ቢሆን ከማዳን አትቦዝኑ። https://t.me/ethiopianorthodoxbooks