✍ከእለታት አንድ ቀን አንዲት በጣም ውሀ የተጠማች እርጉዝ ሴት በጉዟዋ ላይ እያለች ምንም የውሀ ምንጭ በሌለበት አካባቢ ከአንድ ዛፍ ስር ተቀምጣ ነበር፡፡ በውሀ ጥም ምክንያት ጉሮሮዋ ደርቋል፡፡ድንገት ግን ቀስ በቀስ ከዛፉ ቅጠል የሚንጠባጠብ ውሀ አየችና ለጉዞ ይዛው ከነበረ ሻንጣ ውስጥ አንድ የውሀ መጠጫ ብርጭቆ አውጥታ የሚንጠባጠበውን ውሀ ማጠራቀም ጀመረች፡፡ የተጠራቀመው ውሀ የብርጭቆው ግማሽ አካባቢ ደረሰና ለመጠጣት ስትሞክር ድንገት ሳታስበው አንዲት ወፍ መጥታ ልትጠጣ ስትል ሴትዮዋ እጅ ላይ የነበረው ብርጭቆ ወድቆ ተሰበረና ውሀው ፈሰሰ፡፡ በዚህ የተነሳ ሴትዮዋ በጣም ተናደደች፤ወፏንም ከዛፉ ካባረረች በኀላ እንደገና አዲስ ብርጭቆ አውጥታ የሚንጠባጠበውን ውሀ ስታጠራቅም አሁንም ወፏ መጥታ ለመጠጣት ስትል ውሀውን አፈሰሰችው፡: እርጉዟ ሴትዮ አሁንም በጣም ተናዳ ድንጋይ አንስታ ወፏን ለመግደል ሞክራ አልተሳካላትም፡፡ይህ ድርጊት ለሦስተኛ ጊዜ ተፈፀመ፡፡ መጨረሻ ላይ ሴትዮዋ ቀስ ብላ ወፊቷ ሳትነቃባት ድንጋይ ወርውራ ገደለቻት፡፡ ከዚህ በኀላ ውሀውም አለቀና ሴትዮዋም ወደ ነበረችበት ተመልሳ ስትቀመጥ በጣም ትልቅ እና ረዥም እባብ ከዛፋ ቁልቁል ወደሷ ሲመጣባት አይታ ሮጣ አመለጠች፡፡ በዚህ ጊዜ ከዛፉ ይንጠባጠብ የነበረ የእባቡ መርዝ እንጂ ውሀ አለመሆኑ ስላወቀች ህይወቷን ያተረፈችላትን ወፍ በመግደሏ በጣም አዘነች ከልቧም ተፀፀተች፡፡
✍ወዳጆቼ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ለኛ ልክ እንደዚህች ወፍ ነው፡፡መርዙ መቼ እንደምንጠጣው ያውቃል ይሁን እንጂ መርዙ ከመጠጣት ሲያድነን፤እኛ ግን የገጠመንን ትንሽ ችግር በማየት ብቻ እግዚአብሔርን እናማርረዋለን(እንወቅሰዋ
ለን)፡፡ ነገር ግን የሆነውን፣እየሆነ ያለውን እና የሚሆነውን ሁሉ ለበጎ መሆኑን ማወቅ ይገባናል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን እጅ ሳንለቅ እርሱን እንከተለው፤በፍፁም አያሳፍረንም፡፡
እናም "አምላኬ ሆይ ላደረግክልኝ ነገር ሁሉ አመሰግንሀለሁ " እንበለው፡፡
Share this Address with your Friends to JOIN OUR CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር

የኢየሱስ ክርስቶስ ኹሉን ዐዋቂነት (Omniscient)
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ [ነገረ ክርስቶስ ክፍል አንድ መጽሐፌ የተወሰደ]
❖ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን እግዚአብሔር በባሕርዩ ፍጹም ዐዋቂ ሲኾን ዕውቀትም የባሕርይ ገንዘቡ ነው፤ ርሱ በባሕርዩ ኹሉን ዐዋቂ ኾኖ ሰውና መላእክትን ማዕምራን፣ ለባውያን አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡
❖ለቅዱሳኑም በጸጋ ከፍተኛ ዕውቀትን ይሰጣቸው እንደነበር የነቢዩ ኤልሳዕ እና የቅዱስ ጴጥሮስ ዕውቀት ምስክር ነው (፪ኛ ነገ ፮፥፲፪፤ የሐዋ ፭፥፩-፲)፡፡
እነኤልሳእ እነጴጥሮስ እና ሌሎቹም ቅዱሳን የተሰጣቸው ዕውቀት የጸጋ ሲኾን የእግዚአብሔር ዐዋቂነት ግን ከማንም ያላገኘው ማንም የማይነሣው፣ አምላካዊ ዕውቀቱም ሊመረመር የማይችል ማእምረ ኅቡአት ነው፡፡
❖ ይኽነንም ጠቢቡ ሰሎምን በ፩ኛ ነገ ፰፥፴፱ ላይ፡- “አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ኹሉ ልብ ታውቃለኽና ልቡን ለምታውቀው ሰው ኹሉ እንደ መንገዱ ኹሉ መጠን ክፈለውና ስጠው” በማለት ጠቅሶታል፡፡
❖ ነቢዩ ዳዊትም እግዚአብሔር ኹሉን ዐዋቂና ልቡና ያመላለሰውን መርምሮ በባሕርዩ የሚያውቅ ስለመኾኑ “እግዚአብሔር ልቡናንና ኲላሊትን ይመረምራል… እግዚአብሔር ይኽነን አይመረምርም ነበርን? ርሱ ልብ የሰወረውን ያውቃልና” በማለት የእግዚአብሔርን ኹሉን ዐዋቂነት ጽፏል (መዝ ፯፥፱፤ ፵፭፥፳፩)።
❖ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትንም ስናነብብ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሔር ነውና ኹሉን ዐዋቂ እንደኾነ ተጽፏል፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ራሱ ኹሉን ዐዋቂ እንደኾነ አስተምሯል፤ በመኾኑም ኢየሱስ ክርስቶስ ኹሉን ዐዋቂ፣ ልቡና ያሰበውን ኲላሊት ያመላለሰውን የሚያውቅ ምንም ምን የሚሰወረው የሌለ የባሕርይ አምላክ እንደኾነ እናምናለን ይኽነን ስንመለከት፡-
[ማስረጃ አንድ]
✔ “ኢየሱስም ዐሳባቸውን አውቆ እንዲኽ አለ፦ ስለ ምን በልባችኊ ክፉ ታስባላችኊ?” (ማቴ ፱፥፬)
✔ “ኢየሱስ ግን ዐሳባቸውን አውቆ እንዲኽ አላቸው፦ ርስ በርሷ የምትለያይ መንግሥት ኹላ ትጠፋለች፥ ርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ኹሉ ወይም ቤት አይቆምም” (ማቴ ፲፪፥፳፭)
✔ “ኢየሱስም አውቆ እንዲኽ አላቸው፦ እናንተ እምነት የጐደላችኊ” (ማቴ ፲፮፥፰)
✔ “ርሱ ግን ዐሳባቸውን አውቆ እጁ የሰለለችውን ሰው ተነሣና በመካከል ቁም አለው” (ሉቃ ፮፥፰)
✔ “ኢየሱስም የልባቸውን ዐሳብ አውቆ ሕፃንን ያዘ” (ሉቃ ፱፥፵፮-፵፯)
✔ “ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ኹሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና” (ዮሐ ፪፥፳፬-፳፭) እንዲል
[ማስረጃ ኹለት]
❖ ሰዎች በልቡናቸው ያሰቡትን የሚያውቅ ኢየሱስ ክርስቶስ በየብስና በባሕር ኾድ ያለውን ኹሉ የሚያውቅና የሚሰወረው ምንም ምን የሌለ እንደኾነ ለደቀ መዛሙርቱ በብዙ ቦታዎች ላይ የገለጠላቸው ሲኾን፤ ከብዙ በጥቂቱ ብናየው፡-
✔ “ወደ ባሕር ኺድና መቃጥን ጣል፤ መዠመሪያም የሚወጣውን ዓሣ ውሰድና አፉን ስትከፍት እስታቴር ታገኛለኽ፤ ያን ወስደኽ ስለ እኔና ስለ አንተ ስጣቸው አለው” (ማቴ ፲፯፥፳፯)
✔ “በፊታችኊ ወዳለችው መንደር ኺዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችኊ፤ ፈትታችኊ አምጡልኝ” (ማቴ ፳፩፥፪-፫)
✔ “ጴጥሮስ ሆይ፥ እልኻለኊ እንዳታውቀኝ ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዛሬ ዶሮ አይጮኽም አለው” (ሉቃ ፳፪፥፴፬)
✔ “ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ ርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ ርሱ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ ናትናኤልም ከወዴት ታውቀኛለኽ? አለው፤ ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራኽ ከበለስ በታች ሳለኽ አየኹኽ አለው” (ዮሐ ፩፥፵፰-፵፱)
✔ “አዎን ጌታ ሆይ እንድወድኽ አንተ ታውቃለኽ አለው” (ዮሐ ፳፩፥፲፭) እንዲል
[ማስረጃ ሦስት]
❖ ራሱ እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ ዐድሮ በምዕ ፲፯፥፲ ላይ “እኔ እግዚአብሔር ለሰው ኹሉ እንደ መንገዱ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለኊ ኲላሊትንም እፈትናለኊ” በማለት ተናግሯል (ኤር ፲፯፥፲)፤ በመኾኑም በነቢዩ ዐድሮ የተናገረው ልቡናን የሚመረምረው እግዚአብሔር ነውና፤ ይኽነን ለዮሐንስ እንዲኽ ነግሮታል፡-
✔ “አብያተ ክርስቲያናትም ኹሉ ኲላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ኾንኊ ያውቃሉ” (ራእ ፪፥፳፫) እንዲል
በመኾኑም ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ኹሉን ዐዋቂ ነው እላለን፡፡
[ኹሉን የምታውቅ ፈጣሪያችን ክርስቶስ ሆይ ይቅርታኽ ቸርነትኽ በኹላችን ላይ ይሁን !!!

"እግዚአብሔር"
እግዚ=>ጌታ
አብ=>አባት
ሔር=>ቸር አፅናኝ፡ መንፈስ
እግዚአ=>ጌታ ገዥ
ብሔር=>አለም
እያንዳንዳቸው ፊደላት የራሱ የሆነ ትርጉም አላቸው፤እኛም
ስንፅፍቸው የስሙ ስያሜ ሙሉ ትርጉም እንዲኖረው በጥንቃቄ
ቢሆን በረከቱ ለኛ ነው።
👉🏻ስህተት የሆኑ አፃፃፉች፦
=>እ/ር
=>እግ/ር
=>እግዜር
=>እግዛቤር
=>እግዚሀብሔር
=>እግዛሃብሔር
ወንድሞች እህቶች ይህ ስህተት እንደሆነ አውቀን በረከቱን
ለማግኘት፦
👉🏻እግዚአብሔር✔ተብሎ መፃፍ ይኖርበታል፤
"በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ፥ስሜንም አውቋልና
እጋርደዋለሁ፤ [መዝ.61:14]
ስለ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ልኡል ሀያል ቅዱስ እግዚአብሔር
ይመስገን!
አሜን ማለት፦ይሁንልን ይደረግልን……ማለት ነው።
👉🏻ስህተት የሆኑ አፃፃፉች፦
=>አመነ
=>አሚን
=>አመን
=>አሜን አሜን ሁለቴ(2) አሜን ማለት "የሥላሴዎችን
አንድነትና ሦስትነት"አይወክልም፤(ትርጉም አልባ ነው)
በረከቱን ለማግኘት፦
👉🏻አሜን✔
👉🏻አሜን አሜን አሜን✔
👉🏻አሜን ፫ ✔
👉🏻አሜን(3) ✔
…ተብሎ መፃፍ ይኖርበታል፤
የእስራኤል አምላክ ልኡል እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋሉን
ያድለን! አሜን አሜን አሜን
ወስብሐት ለ እግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር ይቆየን
.✞.✞.✞.

የጥንት ነጋዴ ነው አሉ፡፡ አህያውን ጨው ጭኖ ለንግድ ወደ ሌላ ሐገር ሲጓዝ አንድ ወንዝ ያቋርጥ ነበር፡፡ ውኃው እርሱን እስከ
ትከሻው አህያዋን እስከ ጆሮዋ ያሠጥማቸዋል፡፡ አህያዋ ግን ከወንዙ ስትወጣ የተሸከመችውን አሞሌ ጨው ግማሹን ወንዙ እያሟሟ ስለሚወስደው ሸክሙ ይቀላት ነበር፡፡ ይህን ብልጠት ያወቀችው አህይት ወንዙን ስትሻገር ሸክሙ ብዙ እንዲቀላት ውኃው ውስጥ ብዙ እየቆየች ነጋዴውን ታከስረው ነበረ፡፡
ይህንን ያጤነው ነጋዴ አንድ ቀን በጨው ምትክ ጥጥ ጫነላትና መጣ፡፡ እርሷም እንደለመደችው በብልጠቷ እለግማለሁ ስትል
ውኃው ውስጥ ቆመች፡፡ ያ አንድ ተራራ የሚያህል ጥጥ ውኃውን ሁሉ ጠጥቶ አህያዋን ሊያሰምጣት ሲደርስ ተመንጥቃ ወጣች ፡፡ እርሷም ከዚያች እለት ጀምራ ልግመቷን ትታ በሥርዓት መጓዝ ጀመረች ይባላል፡፡
የሰዎችም ጠባይ ይህንን ይመስላል፡፡ ሰው በገዛ ጥበቡ ለመጓዝ በጀመረ በገዛ ራሱ ላይ በሸክም ላይ ሸክም ይጨምራል፡፡

ሁለቱ ወንድማማቾች
# ETHIOPIA | የቤተሰባቸውን የእርሻ መሬት ወርሰው በጋራ
የሚሰሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንድኛው ትዳር መስርቶ
ትልቅ ቤተሰብ ሲኖረው ሁለተኛው ግን ብቻውን ነበር
የሚኖረው፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወንድማማቾቹ ከቤተሰባቸው
የወረሱትን ሀብትና ንብረት በመከፋፈል በየግላቸው ለመስራት
ይስማማሉ፡፡ ያለውንም ሀብት እኩል ተከፋፍለው የየግላቸው ኑሮ
ይጀምራሉ፡፡
ወድያውኑ ግን ብቻውን የሚኖረው ወንድሙ ከራሱ ጋር መነጋገር
ይጀምራል “ያለውን ሀብትና ትርፍ እኩል
መከፋፈላችን አግባብ አልነበረም፡፡ እኔ ብቻየን ነው
የምኖረው የሚያስፈልገኝ ነገር በጣም ትንሽ ነው፡፡ እርሱ ግን
ብዙ የቤተሰብ ሀላፊነት አለበት” በማለት ያስባል፡፡ እናም
በጎተራው ካለው እህል አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ
ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡
በተመሳሳይ ግዜ ሚስትና ልጆች ያሉት ወንድምም በተመሳሳይ
ሁኔታ ያስባል “ይህንን ሀብት እኩል መካፈል አልነበረብንም፡፡ እኔኮ
ትዳር አለኝ፡፡ ሚስቴና ልጆቼ ሁል ግዜ ከጎኔ በመሆናቸው ወደፊት
በደንብ ይንከባከቡኛል፡፡ወንድሜ ግን ብቸኛ ነው፡፡ ወደፊት
አጠገቡ ሆኖ የሚንከባከበው እንኳ የለውም” ሲል ያስባል፡፡
እርሱም እንደዚያኘው ወንድም በጎተራ ካለው እህል አንድ ጆንያ
የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ
ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡ ወንድማማቾቹ በዚህ ሁኔታ ለብዙ
ግዜ ኖሩ፡፡ ከብዙ ግዜ ብኋላ ግን ሁለቱንም አንድ ነገር
ያስገርማቸው ጀመር፡፡
በጎተራቸው ውስጥ ያለው እህል መጠን እየቀነሰ
አለመሄዱ ግራ ያጋባቸዋል፡፡
ሁለቱም የገጠማቸውን ያልተለመደ ነገር ለመመርመር በየግላቸው
እየጣሩ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ የተለመደውን
ተግባራቸውን ለመፈጸም እህል የተሞላበት ከረጢት እንደተሸከሙ
በድንገት ተገናኙ ።
ምንም አይነት ቃላት ሳይለዋወጡ ሸክማቸውን መሬት ላይ
በመጣል በፍቅር ተቃቅፈው አለቀሱ ይለናል መሃዘ ጥበብ
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
***
የመተሳሰብ ፍቅር… በአይምሮህ አስበህ በአንደበትህ
የምታወጣው ቃል ሳይሆን፣ በልብህ የሚንፈራገጥ
የማይወለድ ፅንስ ነው።
***
የአንድ አገር ልጆች ነን!
የኢትዮጽያ ልጆች!

Christmas In Ethiopia
The most remarkable fact about Ethiopia is that we still follow the Julian calendar and therefore observe Christmas on 7th January and not on December 25! Christmas, according to the orthodox Ethiopian Church, is termed as "Ganna". The Christmas celebrations in Ethiopia are conducted in all ancient and modern churches with much fervor. People fast on Christmas Eve which is 6th January, which is broken the next day. Following the tradition each individual enters the church with a candle in his or her hand and is also dressed in white robes. Unlike many other parts of the world, Christmas is not much commercialized in Ethiopia. The focus is more on the family gatherings and the spiritual aspects of the festival. People spend a lot of time praying the Lord and singing in his reverence. A strict observance of fast itself tells of their profound spiritual association with Christmas. Read through the article to learn about the Christmas celebrations in Ethiopia.
Customs, Traditions & Celebrations
The Fast
The day before Christmas or Ganna, people observe a fast which is broken the next day at dawn. So, the fast begins on 6th January and on 7th morning they get dressed in traditional garments called "shamma" and prepare themselves for the church services, after which the fast is terminated. "Shamma" is a thin white cotton cloth, worn like a toga. The priests wear a similar kind of thing, except that it will have both colors of red and white. In the cities, the urban Ethiopians are seen in "western" white clothes.
The Masses
The masses are held as early as 4 A.M in the morning. People gather in the churches close to their houses and as they enter the church they are given candles before the ceremony begins. The ancient churches in Ethiopia are located outside the capital city. These are etched out of solid volcanic rocks, much like the houses in Ethiopia. The modern churches are built in three concentric circles and the choir sings from the outer circle. As people enter the church they walk around it three times in a quiet procession holding the candles. Then they proceed to the second circle, where they stand throughout the ceremony. Seats are not found in Ethiopian churches. Men and women stand separately during the church service. The center is the most sacred place of the church where the priests conduct the Holy Communion. The mass usually lasts for three hours, but sometimes it might exceed.
Christmas Traditional Games
Ganna is traditional Ethiopia game played by men and boys on Christmas Eve. In this game, a curved wooden stick and a wooden ball are used to play, which hold certain resemblances with the game of hockey. "Yeferas suk" is another game in which men ride on horsebacks, shooting spears at each other.
Ganna Dishes
During Christmas "injera", flat spongy bread and "doro wat", which is Ethiopian chicken in red pepper paste, is a prime delicacy. "Wat' is served on "injera", which serves as a base for the stew.

+.• ♥•.+እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ+.• ♥•.+
👐― ⛪ 💚 ⛪ 💛 ⛪ ❤ ― ልደቱ ለእግዚእነ 👐― ⛪ 💚 ⛪ 💛 ⛪ ❤ 👐
↘❤በጌታችንና በአምላካችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተደረገልን ፍፁም ሥርየትና እርቅ ግልጥ ሆኖ የተጀመረው በነገረ ልደት ነው። የጌታችን ልደት በነገረ ድኅነት ትልቅ ስፍራ የያዘና እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ፍፁም ልዩ መሆኑን ያሳየ ነው። መስተፃርራን የነበሩ ሰማይና ምድር፣ ሰውና መላእክት በአንድነት ለምስጋና ታድመዋል። የእረኞች አንደበት ከመላእክት ጋር ለሰማያዊ ምስጋና ብቁ የሆነበት፤ ግዕዛን የሌላቸው እንስሳት ሰራኢ መጋቢያችን፣ በዘባነ ኪሩቤል በሰማያት የምትገለጥ አንተ ነህ ሲሉ እስትንፋሳቸውን የገበሩለት፤ የምድር ነገስታት በሥልጣንህ ሽረት በመንግሥህ ህልፈት የሌለብህ የነገስታት ንጉሥ አንተ ነህ ሲሉ ወርቅን ለመንግሥቱ፣ ዕጣንን ለክህነቱ፣ ከርቤን ለህማሙ ዕጅ መንሻን ያበረከቱለት፤ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ያን ልዩ ክብር የዩበት፤ ይህ ልደት በእውነት ልዩ ነው።
✔✅ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በረቡዕ ውዳሴ ማርያም በጌታ ልደት የተደረገልንን ድንቅ የማዳን ሥራ በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ ነበር ያለው፦ "በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰዉ ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፣ ስለተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋህዷልና ቅድምና የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት።"
🙏ቤተልሔም ማለት ቤተ ህብስት፣ የህብስት ቤት፣ የእንጀራ ቤት ማለት ነው። ይህም ካሌብ እስራኤል ዘሥጋ ምድረ ርስት፣ ኢያሪኮን "ሃይል ዘእግዚአብሔር ኲናት ዘኢያሱ" ብለው በኢያሱ መስፍንነት ሲወርሱ ከኢያሱ የተሰጠችው ምድር፣ ኬብሮን ነበረች። ይህችም የይሁዳ ምድር በኋላም የቅዱስ ዳዊት ከተማ የሆነች ናት። አስቀድሞ ካሌብ ከብታ የምትባል ሚስት አግብቶ በሚስቱ ከብታ አላት ትርጓሜውም የምስጋና ቤት ማለት ነው፤ ይህም ካሌብ በመንፈሰ እግዚአብሔር በዚህች ምድር የሚገለጠውን የክርስቶስ የልደቱን ነገር፣ እና የመላእክትን ምስጋና ስለተረዳ ነበር። በኋላም ካሌብ ኤፍራታ የምትባል ሚስት አገባ ቦታዋን በዚህች ሚስቱ እንደገና ኤፍራታ ብሎ ጠራት። ኤፍራታ ማለት ፀዋሪተ ፍሬ፣ ፍሬ በውስጧ ያለባት ማለት ነው። ይህችውም የእመቤታችን ምሳሌ ናት የህይወት ፍሬ ክርስቶስን ወልዳልናለችና፤ አንቲ ውእቱ ዕፅ ቡሩክ ፍሬኪኒ ፍሬ ሕይወት እንዳለ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን። ቤተልሔም ይህን ስያሜዋን ያገኘችው ካሌብ ከኤፍራታ ባገኘው ልጁ በልሔም ነው፤ ልሔም ማለት ህብስት፣ እንጀራ ማለት ነው ይህም ምሳሌነቱ የጌታ ነው፤ ይኸውም አማናዊ፣ እውነተኛ የሕይወት እንጀራ፣ህብስት ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ሊያድነን የመወለዱ ምሳሌ ነው። "ከሰማይ የወረደ ህያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል እኔም ስለዓለም ህይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።" እንዲል ዮሐ 6፥51።
👉በክርስቶስ ልደት መላእክት ባልተለመደ ሁኔታ ከሰዎች ጋር ተባብረው “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ሰላምም ለሰው ልጅ በምድር እርሱ በሚፈቅደው እያሉ ንጉሥ ክርስቶስን አመሰገኑ። ሉቃ 2፥14። በሰማያት በዘባነ ኪሩቤል የሚገለጥ፤ ፍፁማን ግሩማን በሚሆኑ መላእክት፣ ሊቃነ መላእክት፣ ሥልጣናት፣ አጋእዝት የሚመሰገን ሰማያዊው ንጉሥ ዛሬ ስለእኛ ፍቅር ሲል ሊነገር በማይችል ፍፁም ትህትና ከመ ሕጻናት ታቅፎ፣ ከኀጢአት ብቻዋ በቀር የኛን ባህሪ ባህርዩ አድርጎ ፍፁም አምላክ ሲሆን ፍፁም ሰው ሆኗልና።”ሕፃን ተወልዶልናልና፥ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይኾናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ኀያል አምላክ፥የዘለዓለም አባት፥የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” ትኢሳ 9፥6።
✔ 💟 ይህ የጌታ ልደት የቤተ ክርስቲያን አንድነት ነው። ሁሉ በአንድነት የተሰባሰቡበት በጋራ የዘመሩበት፤ በዚይች በበረት፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በሆነችው ጌታችን ከመሀል ከእናቱ ጋራ እንዲሁም አረጋዊ ዮሴፍ ከማሕበረ ጻድቃን፣ ሰማያውያን መላእክት፣ እረኞች፣ ሰባሰገል ነገሥታት፣ እንስሣትም ሳይቀሩ ባንድነት የተገኙባት የፍቅርና ያንድነት ቤት ናት። ስለዚህ እኛም የክርስቶስ አባግዓ መርዔቱ፣ የመንጋው በጎች፣ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በፍፁም አንድነት መኖር እንዳለብን “ወንድሞች ሆይ፥ዅላችኹ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፤ ባንድ ልብና ባንድ ሃሳብም የተባበራችኹ እንድትኾኑ እንጂ መለያየት በመካከላችኹ እንዳይኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችዃለኹ።” የተባለውም ስለዚህ ነውና። 1ኛቆሮ 1፥10። በማለት ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ያስተምረናል።
↪💟የጌታችንና የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ በዓል በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን። 💟↩

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ሰማዕት ሕጻን ቂርቆስ ወ ኢየሉጣ 15/05/10 ሳሚ ዘቂርቆስ
የሰውን ልጅ ከማህጸን ገና ሳይሰራ ለአገልግሎት መምረጥ የሚችል እግዚአብሔር ክብር ይግባውና (ኤር1፡5) ይህን ታላቅ እና ታምረኛ ሕጻን ቅዱስ ቂርቆስን ከእናቱ ከቅድስት ኢየሉጣ ጋር ለአገልግሎት ቢመርጣቸው በእምነት ይከተሉት ዘንድ አስከሞት ድረስ መታመናቸው (ዮሐ.ራእ2፡10) ሕጻኑ በተለይ ከራሱም አልፎ ለእናቱ የእምነት ጽናት እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ መጸለዩ እና እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በጽናት በሰማዕትነት ማረፉ በእውነት ላላፍርበት ቅዱስ ጳውሎስ እኔን ምሰሉ እንዲል፡፡ (1ቆሮ11፡1) ሳሚ ዘቂርቆስ ተብዬ በስሙ እጠራ ዘንድ የማላፍርበትን የፍቅርን አውልት ለእኔ ብቻ ሳይሆን በክርስቲያኖች ልብ ላይ የተከለ አስገራሚ ሰማዕት (ምስክር) ነውና ሁልጊዜ በ15 ሰማዕቱ ቅዱስ ቂርቆስ ተብሎ መከበሩ የተገባ ነው፡፡ ለዚህም አባቶቻችን ባለውለታዎቻችን ናቸው ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡
ባለ ራእዩ ቅዱስ ዮሐንስ"ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብጹዓን ናቸው፡፡" እንዲል፡፡ (ዮሐ ራእ22፡14) ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነውን የሕጻን ቅዱስ ቂርቆስ ታሪክ እነሆ፡- ሰማይቱ ሕጻን ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምኦን)እናቱ ኢየሉጣ ሳልሳይ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡አንጌቤን ማለት የሴት ወይዘሮ ሀገር ማለት ነው፡፡ማስረጃውም ፀሐይ ዘእስያ መስፍን ዘእስያ ዘእስያ ንጉስ ህፃን ቂርቆስ ደግሞም መስፍን ዘእስያ ዘእስያ መስፍን ቂርቆስ ህፃን ይለዋል፡፡
በህዳር 15 ቀን ተወለደ በዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት (ከ160ዓ.ም-312ዓ.ም) ነበረና ለጣኦት ስገጅ ተብላ እናቱ ተገደደች ከዚያም የሚሰገደው ለእግዚአብሔር እንጂ ለጣኦት እንዳልሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ በመረዳቷ (ማቴ4፡10) ፤ (ዘዳ6፡13) እንዲሁም እንደ ሶስቱ ሕጻናት (ሲድራቅ ሚሳቅ እና አብድናጎም) በእምነት ድፍረት ሊመልስ ወደሚችለው (ዳን 3፡18) ልጅዋ ሸሽታ ሄደች፡፡ በዚያም ሳለች የፈራችው ደረሰባትና እለእስክንድሮስ የተባለው ለጣኦት ስገጂ ብሎ አሰገደዳት፡፡
እሷም ሕጻን ልጅ መጥቶ ይመስክር ብላ ስትል ቅዱስ ቂርቆስ ተጠርቶ ከጫወታ ቦታ መጣ መኮንኑም ሲያየው ሰይፉን እያፏጨ ሕጻኑ እንዲፈራ አስቦ ሰይፉን ወዘወዘውና ለምን አትሰግድም? አለው፡፡ ሕፃኑም የሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ሶስት ዓመት ያልሞላው ሕጻን ሲሆን የአባቶቹን ተጋድሎ አምላኩ እግዚአብሔር በመንፈስ የገለጠለት ሕጻን ነውና "...ከሰይፍ ስለት አመለጡ" እንዳለ (ዕብ11፡34) እሺም አላለውም ምcክንያቱም የታመነውን ቃሉን "እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፡፡" (ያዕ 4፡7) እንዳለ በመንፈስ ያውቀዋልና በእምነቱ ጸና፡፡እኛንም ያጽናን፡፡ በኋላም እንደገና ሕጻኑን እዲሰግድ ቢያስገድደው ህፃኑም እንደ ኢያሱ በእምነት የጸና ልብ ያለው በመሆኑ (ኢያ24፡15) እኛ አንሰግድም ለአንተ ጣኦት መንግስቱ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእሱ ነው የምንሰግደው ብሎ እንቢ አለው፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሐዋርያት ላይ እና ዓለምን በመናቅ ስለስሙ በሚመሰክሩ ሰማዕታት ላይ ሁሉ ስለሚደርስባቸው መከራ ሲናገር "ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋልም በምኩራቦዎቻቸውም ይገርፏችኋል" አንዳለ (ማቴ10፡16) በዚያን ጊዜም 40 ጋን ውሃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ዘይት፣ዝፍት በውስጡ ጨምሮ ከፍላት ወደ እሳትነት ሲለውጥ 150 ሜትር ወደ ሰማይ ሲዘልቅ እንደመብረቅ ሲጮህ ያን ጊዜ ሕፃኑና እናቱ ወደ እሳቱ እንዲያስገባቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ግዜ ሕፃኑ እናቱን እየጎተተ " እናቴ ሆይ ጨክኚ በርቺ የዚህ ዓለም እሳት አያስፈራሽ የሰማያዊን እሳት ፍሪ" ብሎ ቀሚሷን እየጎተታት ይዟት ወደ እቶኑ ገባ፡፡
እቶን ማለት የነጠረ የጋለ ናስ ይመስል ስጋን ከአጥንት ለይቶ የሚያቀልጥ ለአይን በጣም የሚቆጠቁጥ የእሳት ዓይነት ነው፡፡ (ዮሐ.ራእ1፡15) ይህ እሳት 40 ቀን ሙሉ ከበርሜሉ ላይ ጨምሮ ዘይቱን ስላፈላው ዘይቱም ከፍላትነት ወደ እሳትነት ተለውጦ እንደ መብረቅ እየጮኽ ወደ ሰማይ ሲወጣ ፍላቱንና ጩኽቱን አይታ ነው ፊቷን በልብሷ የሸፈነችው፡፡ ኢየሉጣንም ቅዱስ ቂርቆስ ጨክኝ ያለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ከዚህ በኋላ ከበርሜሉ ውስጥ ከፍላቱ ሲገቡ ሶስቱን ሕጻናት የረዳ መልአክ (ዳን 3፡25) ዳዊትም መልአክት በተሰጣቸው ስልጣን ከሞት እንደሚያድኑ እንደገለጸው (መዝ33(34)፡7) መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እየበረረ ወርዶ ከእነሱ ውስጥ ገባ፡፡ ያዕቆብ ልጆቹን እጁን አመሳቅሎ እንደባረካቸው ዳዊትም ለሚፈሩት ከቀስት (ከእሳት) ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጣቸው እንዳለ (መዝ59፡4) እና (ዘፍ48፡14) በመስቀሉ ባረከ ፍላቱ ቀዘቀዘ በረደላቸው፡፡ እንዲያውም እንደ ጥምቀት ሆነላቸው ከዚያም በኋላ እለእስክንድሮስ ኢየሉጣን ከነእናቱ ከእሳቱ አወጣቸውና አሁንም በአፉ በአፍንጫው ቅንጭብ፣ዝፍት ፣መርዝ ከተተበት "ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል...የሚገድል ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም..." እንዳለ (ማር 16፡17) ምግብ ሆነው ደግሞ ጨው በርበሬ ቅንጭብ በዓይኑ ላይ አነደደበት ግን ምንም አልነካውም ቅዱስ ቂርቆስ ግን ማስተማሩን ቀጠለ፡፡
መስፍኑም ተናደደ በዚህም ተናዶ በጥር15 ቀን እሁድ በ 6 ሰዓት በተወለደ በ3 ዓመት ከ1ወር ከ3ቀን ሲሆነው አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠው 3 አክሊላትም ወረዱለት፡፡ በእድሜው ልክ ለሕጻንነቱ ለተጋድሎው ለሃይማኖቱ ጽናት ሲል አንገቱን በተቆረጠም ጊዜ ደም ውሃ ወተት ወጥቶአል፡፡ ጌታችንም "ምን ላድርግልህ?" ብሎ ጠየቀው ቂርቆስም ጌታውን ስጋዬን በምድር ላይ አንዳይቀበር ነው ጌታችንም "ስጋህን በሰረገላ አሳርገዋለሁ" አለው፡፡ እንደ ኤልያስ በሰረገላ አሳረገው አልተቀበረም በበነጋታው እናቱን በ16 ኢየሉጣን አንገቷን ቆረጣት በዚህም ጌታችን ቃል ኪዳን ገባለት " ስምህ በተጠራበት ቤተ መቅደስህ በታነፀበት ቦታ ረሀብ ፤የህፃናት እልቂት ፤የከብት በሽታ፤ የከብት እልቂት አይገባም የእህል ዕጦትም አይደርስም፡፡" ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡
በሀገራችንም በስሙ የተሰሩ ታላላቅ አድባራት ብዛት 11 ገዳማት 5በድምሩ በሀገራችን 76ቤተ ክርስቲያኖች ይገኛሉ፡፡ የቅዱስ ቂርቆስን ታቦት በመጀመሪያ ያመጣው አባት አቡነ ኃይለ መለኮት የተባለው ጻድቅ ነው ያመጣው ከግብፅ ነው፡፡ ታሪክን ታሪክ ያነሳልና የአዲስ አበባ መካነ ሰማዕታት ቅዱስ ቂርቆስ በአዲስ ስሙ ደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርሰቲያን ፅላትን ያዘጋጀው ጻድቅ ሌላ ታቦት እንዳይሰራ እጁ ተቆረጠ ከዚያም በጣና ባሕር በቅቶ ነው በ180 ዓመቱ የሞተው ያስደንቃል፡፡ የጣና ቂርቆስም በስሙ ከእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ወደ እሱ ተዘዋውሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰራ፡፡ የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን፡፡ አሜን፡፡
〰〰〰〰〰〰〰
Share this Address with your Friends to JOIN OUR CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks

ጥር ፳፩ የእመቤታችን ዕረፍትና የሊቃውንት ውዳሴ
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
♥♥♥ የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር፤ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ከቆየች በኋላ፤ ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት።
♥♥♥ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፤ ያን ጊዜ የአምላክ እናት ፊት ተሰብስበው ከእጆቿ በረከትን አገኙ፡፡
♥♥♥ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ጌታም ተገልጾ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ በማለት ተናገረ።
♥♥♥ ከዚያም ጌታ እናቱን "የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ፤ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡
♥♥♥ የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡
♥♥♥ ይኽን ከልጇ በሰማች ጊዜ ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ።
♥❖♥ ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ፡-
“ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና (ለማርያም) ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና
ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”
(በማርያም ዕረፍት ጊዜ ወልድ ከልዕልና ወረደ፤ የንግሥና (የክብር) መጐናጸፊያን በዚያን ጊዜ ሸፈናት) በማለት የዕረፍቷን ነገር አስተምሯል፡፡
♥❖♥ የመልክአ ማርያምም ጸሐፊ በአድናቆት፦
“ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ጻዕር ወጻማ
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ”
(ከሃሊ (ማእምር፣ ጠቢብ) በሚኾን ልጅሽ ቀኝ ዘወትር ለመቀመጥ ያለ ድካምና ያለ ጣር ለኾነ የነፍስሽ መለየት ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፨
♥♥♥ ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፤ የከበረ ሥጋዋም የጠራና መዐዛው ድንቅ ነበር።
♥❖♥ የመልክአ ማርያም ደራሲው ሊቁ፦
“ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ
ዘተመሰለ ባሕርየ"
(ዕንቊን ለተመሰለ የጠራ የሥጋሽ በድን ሰላም እላለኊ) በማለት ያመሰግናል።
♥♥♥ ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት በዚያ አስደናቂ መጎናጸፊያ በክቡራን ሽቱዎች የከበረ ሥጋዋን አጅ እየነሡ ገንዘዋታል። ሊቁም በመልክአ ማርያም ላይ፦
“ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ
በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕጹብ"
(የዋጋው ስሌት እጅግ ውድ በኾነ ያማረ ሽቱ ርግቦች በተባሉ በሐዋርያት እጅ ለተደረገ የሥጋሽ አገናነዝ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያመሰግናል።
♥❖♥
ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-
♥ “ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”
(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)፨
♥ “በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት
ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት
ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት
ወቀበርዋ ውስተ ገነት”
(ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት)፨
♥ “ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ
በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ
ገነዙ በክብር ወበስባሔ
ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ”
(ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ)፨
♥ “ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ
ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ
ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ
ዳዊት ዘመራ በመሓልይ”
(በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት)፨
♥ “ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ
በደመና ብርሃን ጸዐዳ
ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ”
(ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት)፨
♥“ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት
ብፁዓን ሐዋርያት
ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ
በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ”
(ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ) በማለት ሊቁ ማሕሌታይ በሐዋርያት እጅ የተደረገ የሥጋዋን ግንዘት አምልቶ አስፍቶ ጽፏል፡፡
♥♥♥ ከዚያም ወዲያውኑ የድንግልን የከበረ አካል ወደ ላይ በማንሣት ቅዱስ ጴጥሮስ ራሷን፣ ቅዱስ ዮሐንስ እግሮቿን ተሸክመው የተቀሩት ሐዋርያት በእጆቻቸው የዕጣን ማዕጠንት ይዘው በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡
♥♥♥ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡
♥♥♥ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡

♥♥♥ ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡
♥♥♥ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋት በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 በልጃ ሥልጣን ተነሥታ ዐርጋለች።
[ቅዱሳን ሐዋርያት በዕረፍትሽ ሰዓት በክቡራት እጆችሽ እንደተባረኩ በዓለ ዕረፍትሽን በስምሽ በተሠየመች ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበን የምናከብር ልጆችሽን ባርኪን]
[ወጸሐፈ በእንተ ዕረፍታ ለድንግል ገብራ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፤ አመ ፳ወ፩ ለጥር በተዝካረ በዓላ ለእግዝእትነ ማርያም ትንብልናሃ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን ]

ሰይጣን ለምን በእባብ ተመሰለ ?
" እንተ አሳታ ከይሲ ለሔዋን ፤ እባብ ባሳታት በሔዋን " ( ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ )
ምነው ያሳታት ዲያቢሎስ አይደል ለምን እባብ አለው ቢሉ ?
1) በግብሩ ነው። ከይሲ ( እባብ ) በመርዙ እንደሚጎዳ ዲያቢሎስም በግብሩ ይጎዳልና።
2) አንድም በማደሪያው ነው። " ወበስመ ኀዳሪ ይጼዋ ማኅደር ወበስመ ማኅደር ይጼዋ ኀዳሪ ፤ ማደሪያው በኀዳሪው ኀዳሪውም በማህደሩ ይጠራልና " እንዲል
ምንም ሰይጣን ቢያስታት ቅሉ በእባብ ተሰውሮ በልሳነ ከይሲ ተናግሮ ነውና።
3) እባብ ትንሽ ቀዳዳ ያገኘ እንደሆነ ጥልቅ ብሎ ገብቶ ያሰፍታል ሰይጣንም በነብስ ላይ ትንሽ ኃጢአት ያገኘ እንደሆነ ጥልቅ ብሎ ገብቶ ከፍሬ ሃይማኖት ከጸጋ መንፈስ ቅዱስ ይለያታል።
4) አንድም እባብ ከሰውነት አንዱን አካል የነከሰ እንደሆነ በሰውነት ሁሉ ተሰራጭቶ ሰውነትን ሁሉ እንደሚጎዳ ሰይጣንም በአንዲት በሔዋን ባደረገው አመጽ ሰውን ሁሉ ጎድቷልና።
( ትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ )