ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን “የህይወት ዋጋው ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትም መልስ በመስጠት ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ “እንካ ይህንን የድንጋይ ቁራጭ...ወደ ገበያ ውሰደው፡፡ ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር” አለው፡፡ ልጁም ድንጋዩን ወሰደ፡፡ ወጥቶም በገበያ መሃል ቆመ፡፡ አንዲት ሴትም መጣች፡፡ “ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው? ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳያት፡፡ እሷም አለች “ሁለት ብር?
እወስደዋለሁ!!”
ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በገበያ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም አለው “አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ ሙዚየም ሂድ፡፡ ዋጋውን ሲጠይቁህም ሁለት ጣቶችህን አሳይ”፡፡ ልጁም ወደ ሙዚየም ወጣ፡፡ ገዢም መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “ሁለት መቶ ብር? እወስደዋለሁ!” አለው፡፡ ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ ማዕድናት መሸጫ ሂድ ለባለቤቱም አሳየው”
አለው፡፡ ልጁም ሄደ፡፡ ለሱቁም ባለቤት አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም “ይህ እኮ አለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡ “ከየት አገኘኸው? ስንትስ ትሸጠዋለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡
የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን ድንጋይ በሁለት መቶ ሺህ ብር እወስደዋለሁ፡፡”
ልጁም በመገረም እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያጋጠመውን ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡
አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣ ሃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣ የተወለድክበት ቦታ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ ዋናው ራስህን የምታስቀምጥበት ቦታ፣ ራስህን የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም በምትመርጥበት መንገድ ነው፡፡ ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡ ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ ሁለት ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ ድንጋይ በውስጡ ይዟል፡፡ ልዩነቱም ያለው ውስጣችን
ያለውን የከበረ ድንጋይ አይተው ዋጋ በሚሰጡን ሰዎች መሃል መገኘትን ስንመርጥ ነው፡፡ ራሳችንን በገበያ ወይም በከበሩ ማዕድናት ሱቅ የማስቀመጥ ምርጫው አለን፡፡ በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያለውንም ውድ ዋጋ ለማየት ምርጫው የኛው ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም የከበረ ዋጋቸውን እንዲረዱ ማድረግ
እንችላለን፡፡ አብረህ የምትውላቸውን ሰዎች በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ ይህ በህይወትህ ልዩነትን ይፈጥራልና፡፡
👇👇👇👇👇
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️

☞ሰውን ሰው ያደረገው ስራ አይደለም አህያም ይሰራል:
☞ሰውን ሰው ያደረገው ንግግር አይደለም በቀቀንም ይናገራል::
☞ሰውን ሰው ያደረገው እብደት አይደለም ውሻም ያብዳል::
☞ሰውን ሰው ያደረገው ብልሐትአይደለም ዶልፊንም ብልሕ ነው::
☞ሰውን ሰው ያደረገው እንባ አይደለም አዞም ያነባል::
☞ሰውን ሰው ያደረገው ጭንቀት አይደለም ፍየልም ይጨነቃል።
☞ሰውን ሰው ያደረገው ስለነገ ማሰቡ አይደለም ጉንዳኖችም ስለመጪው ክረምት አስበው በበጋ በቂ ምግብ ያዘጋጃሉ።
☞ሰውን ሰው ያደረገው....አስተሳሰቡ እና አመለካከቱ ነው። ሰውን ሰው ያደርገው አምላክ(ፈጣሪ) ብቻ ነው ምክንያቱም መልካም ጥበብ እና ማስተዋል ከፈጣሪ ዘንድ ነውና። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️👇👇👇👇

ይህ ሕይወት ምንድን ነው?
✍ የሰው ልጅ ዛሬ ይወለዳል ከእለታት አንድ ቀን ይሞታል
✍ የሰው ልጅ ዛሬ በመሬት ላይ ቤት ሰርቶ ይኖራል ከእለታት አንድ ቀን ከምድር በታች ይገኛል
✍ የሰው ልጅ ዛሬ ታሪክ ያነባል ከእለታት አንድ ቀን የእርሱ የህይወት ታሪክ ይነበባል
✍ የሰው ልጅ ዛሬ በቤቱ ሊያርፍ ይችላል ከእለታት አንድ ቀን በሳጥን ውስጥ ሆኖ "ነፍስ ይማር" ይባላል
✍ የሰው ልጅ ዛሬ ባለሀብት ሊሆን ይችላል ከእለታት አንድ ቀን ሀብቱን ላይጠይቅ ጥሎ ይሄዳል
❖ ታዲያ ህይውት ምንድን ነው?
ሰው ሆይ ነገን ላታያት ስለምትችል ዛሬን አቅድ ህይወትህን በሚገባ ካቀድክ ከሞትኩ በኃላ ምን እሆናለሁ ብለህ አትፈራም
ይህን ስታስበው
1, የዘላለም ህይወት=በነጻ
2, የቤተክርስቲያን መግቢያ=በነጻ
3, የክርስቶስ የማዳን ስራ=በነጻ
4, የእግዚአብሔር ፍቅር = በነጻ
5, ምትተነፍሰው አየር= በነጻ
1, ሲጋራ = በክፍያ
2, የሴተኛ አዳሪ=በክፍያ
3, መጠጥ=በክፍያ
4, የሌሊት መዝናኛ መግቢያ= በክፍያ
5, አለምን ለመግዛት የሚያስፍልግ ሀይል= በክፍያ
ታዲያ ሰዎች ለምን ለጋህነም ይከፍላሉ ገነት ነጻ እየሆነ ?
በሚገባ አስብ
በክርስቶስ የመስቀል✞ ስራ እመና ትድናለህ
ስለ ፍቅር ቀን
የአባቶች ቀን
የአርበኞች ቀን
የእናቶች ቀን
የነጻነት ቀን
የአርሶ አደሮች ቀን
የወዛደሮች ቀን
የእዚህ ቀን የእዚያ ቀን እየተባለ ይታሰባል።
✔የፍርድ ቀንስ?
ሰው ሆይ እግዚአብሔር ጻድቅ ፈራጅ እደሆነ ታውቃለህ? ለመሆኑ የፍርድ ቀንንስ አስበህ ታውቃለህ? ጻድቁ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ የኃጢአት ዋጋ እንደከፈለልህ ታውቃለህ? የአንተንስ ጩኧት እንደጮኧልህ አስተውለሀል?
☞ ያቺ የፍርድ ቀን ለአንተ የደስታ የእረፍት ወይስ የሀዘን ቀን ናት?
☞ ለአንተ የደስታ ቀን ከሆነ ለቤተሰቦችህስ ለወዳጆችህስ?
✔እባክህ ስለዚህ የፍርድ ቀን ንገራቸው ቀራንዮን ጠቁም ስለማያልቀው የመስቀል ላይ ፍቅር መስክር ዘምር የአንድ ሰው መዳን በሰማያት ትልቅ ደስታ ነውና
"በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:2፤)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@ethiopianorthodoxbooks 👈
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
👉@ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

❖♥ ታቦተ ጽዮን የአምላክ እናት♥❖
[በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖✔♥ የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ የኾነቺው በወርቅ የተለበጠችው ይቺ የእግዚአብሔር ታቦት፤ በንጽሕና በቅድስና የተጌጠችው የእግዚአብሔር ወልድ እናት የኾነቺው የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡
❖✔♥ በመጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፪ ቊጥር ፲፪ትን እንደምናነበው፤ ታቦተ ጽዮንን ያገለግሉ የነበሩት የካህኑ የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በሠሩት ታላቅ ኀጢአት ምክንያት እግዚአብሔር ዐዝኖባቸው የክብሩ መገለጫ የኾነችው ታቦት በፍልስጤማውያን እጅ እንድትማረክ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቤንኤዘር ወደ አዛጦን በመውሰድ በድፍረት ከዳጎን አጠገብ አኖሯት፤ ነገር ግን ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ወድቆ ተገኘ፤ እነሱም እንደገና ዳጎንን ወደ ስፍራው መልሰው ኼዱ፤ በነጋታው ለማየት ሲመጡ የዳጎን እጅ እግሩ ተቆራርጠው ደረቱ ለብቻው ወድቆ ተገኘ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይኽነን ታሪክ ይዞ ‹‹የእግዚአብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው?›› (፪ቆሮ ፮፥፲፮) በማለት የታቦትን ክብር አስተምሮበታል፡፡
❖✔♥ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅም በሰቈቃወ ድንግል መጽሐፉ ላይ የአምላክ ማደሪያ የኾነችው ታቦት ወደ ፍልስጤም ሀገር ኼዳ ዳጎንን ሰባብራ እንዳጠፋች ኹሉ፤ አማናዊት የጌታ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን ይዛ ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ የግብጽ ጣዖታት ኹሉ እየተሰባበሩ መውደቃቸውን ሲገልጹ፡-
"ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ
ወድቁ አማልክተ ግብጽ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ
ወተኀፍሩ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ"
(ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የኼደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦት ታቦተ ጽዮን፤ የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፤ በዚች ታቦት የተመሰለች ድንግል ማርያምም ኹሉን ማድረግ ከሚችል ከልጇ ጋር ግብጽ ወደሚባል አገር በኼደች ጊዜ፤የሐሰተኛ ሰይጣን ዘፋኖች የኾኑ የግብጽ ጣዖታት ፈረሱ፤ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ኹሉ ዐፈሩ) በማለት አነጻጽሯል፡፡
❖✔♥ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ስለሠሩት ታላቅ የድፍረት ኀጢአት እግዚአብሔር ቀጣቸው ብዙዎቹ ሞቱ፤ ያልሞቱትም በእባጭ ተመቱ፤ የአይጥ መንጋም ምድራቸውን አጠፋባቸው፤ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራው በምን እንስደደው? ብለው በመማከር፤ የሚያጠቡ ቀንበር ያልተጫነባቸው ኹለት ላሞችን በመውሰድ፤ በዐዲስ ሠረገላ ጠምደው እንቦሶቻቸውን (ጥጆቻቸውን) ከቤት ዘግተው በማስቀረት፤ ታቦተ ጽዮንን እጅ መንሻውን በሠረገላው ላይ ጫኑ፤ ያን ጊዜ እነዚኽ ላሞች ጥጆቻቸውን ሳይናፍቁ ወደቀኝ ወደግራ ሳይሉ እምቧ እያሉ ወደ ቤተ ሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ገሠገሡ፤ ሠረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኢያሱ እርሻ ሲደርስ ያን ጊዜ ሌዋውያን ታቦት ጽዮንና ዐብሮ የነበረውን የወርቅ ዕቃ አውርደው በታላቅ ደንጊያ ላይ በማኖር፤ ሠረገላውን ፈልጠው ጊደሮቹን ሠውተዋቸዋል፡፡
❖✔♥ ይኽም ለጊዜው ቢደረግም ለኋላው ግን ምሳሌ ነበር፤ ላሞቹ የሰማዕታት፤ ልጆች የልጆቻቸው፤ ሠረገላ የመስቀል፤ ልጆቻቸውን ከወደኋላ እንዳስቀሩ፤ ሰማዕታትም የልጅ የገንዘብ ፍቅር አያስቀራቸውምና፣ ሠረገላውን ፈልጠው እንደሠዋቸው ራሳቸውን በመስቀል ይሠዋሉና በማለት የብሉይ ኪዳን መተርጒማን ያመሰጥሩታል፡፡
❖✔♥ የመልክአ ማርያም ደራሲ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችውን የኻያ መንፈቅ ማለት ዐሥሩ ቃላት የተጻፉባቸው ጽላት የተቀመጡባትን የእግዚአብሔርን ታቦት ጊደሮቹ ከልጆቻቸው ይልቅ በማስበለጥና በመውደድ ይዘዋት ወደፊት እንደነጎዱ፤ ርሱም የልዑል ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ጥልቅ ፍቅር በድርሰቱ ላይ፡-
"ማርያም ጽዮን ታቦት ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ
ዕጐላት እምዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ
አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ"
(የኻያ እኩሌታ የሚኾን የእውነት ቃል ማደሪያ ጽዮን ማርያም ሆይ፤ ጊደሮች ከጥጆቻቸው ይልቅ አንቺን እንደአፈቀሩ፤ ወድጄሻለኹና ከዛሬ ዠምሮ ፈጽሞ ውደጅኝ) በማለት ገልጦታል፡፡
❖✔♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በምስጢር በመራቀቅ "አንቲ ውእቱ ጽዮን ታቦተ አምላከ እስራኤል እንተ ነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤ ወበህየ አውደቀቶ ለዳጎን..." (ወደ ኢሎፍሊ ምድር የኼደች የእስራኤል አምላክ ታቦት (ማደሪያ) ጽዮን አንቺ ነሽ፤ በዚያም ዳጎንን የጣለችው ጣዖት አምላኪዎቹንም የቀሠፈቻቸው፤ በአመጣጧም ከአዛጦን ሰዎች ካሳን የተቀበለች፤ ከካሳዋም ጋር እንቦሳ ባላቸው ላሞች አስጭነው የሸኟት፤ ከርሷም ጋር የወርቅ ሳጥኖችን በጐኗም፤ የበድን ሣጥን ሥርዐትን አልሠሩም፤ ነገር ግን በርሷ ዘንድ ካለ ከወርቅ መሣሪያና ከሣጥን ጋራ ላኳት፤ በእንግድነቷ ወቅትም በአሳደራት ጊዜ ወደ ቤቱ በመግባቷ እግዚአብሔር የአቢዳራን ቤት ባረከ) በማለት የምሳሌዋን እሙንነት በሰፊው ገልጧል፡፡
❖✔♥ ይኽቺም የእግዚአብሔር ታቦት በቤተ ዐሚናዳብ ኻያ ዓመት ተቀምጣለች፤ ከዚያም የሳኦል ዘመን ዐልፎ የእግዚአብሔር ወዳጅ ዳዊት በነገሠ ጊዜ በዐዲስ ሠረገላ አድርገው ከቤተ ዐሚናዳብ አውጥተው በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በነጋሪት፣ በጸናጽል እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይዘዋት ሲመጡ፤ የእግዚአብሔርን ታቦት ኦዛ በድፍረት በመያዙ እግዚአብሔር ቀሥፎት ወዲያውኑ በታቦቷ አጠገብ ሕይወቱ አልፏል፤ ያን ጊዜ ነቢዩ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ያደረገችውን ተአምራት ተመልክቶ፤ እግዚአብሔር በርሷ እንዳደረ በማመን በፍርሃት ተውጦ "የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?" በማለት ለታቦቷ ያለውን ታላቅ ክብር ገልጧል (፪ ሳሙ ፮፥፱-፲)።
❖✔♥ በዘመነ ሐዲስም በተመሳሳይ መልኩ ጌታን በማሕፀኗ የተሸከመች የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ አማናዊት ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ኤልሳቤጥ ልክ እንደ ዳዊት መንፈስ ቅዱስ መልቶባት፤ የጌታ ታቦት (ማደሪያው) መኾኗን ተረድታ፤ ድምፅዋን አሰምታ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል?" በማለት ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላትን ታላቅ አክብሮት እንደ ዳዊት ገልጣለች (ሉቃ ፩፥፵፫-፵፮) ፡፡
❖✔♥ ከዚያም ዳዊት ይኽነን ታላቅ ቃል ከተናገረ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት በአቢዳራ ቤት ለሦስት ወር ያኽል እንደተቀመጠች (፪ ሳሙ ፮፥፲፩)፤ በተመሳሳይ መልኩ የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያምም በካህኑ በዘካርያስ ቤት ለሦስት ወር ተቀምጣለች (ሉቃ ፩፥፶፮)፡፡ ኦዛ ተቀሥፎ ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቢዳራ ቤት ገብታ ቤቱ ለሦስት ወር በበረከት እንደተመላ ኹሉ፤ በተመሳሳይ መልኩ ዘካርያስም የመልአኩን ቃል ባለመቀበሉ ከተረገመ በኋላ (ሉቃ ፩፥፳)፤ እውነተኛዪቱ የአምላክ ታቦት ድንግል ማርያም ቤቱ ለሦስት ወር ተቀምጣለች፡፡
❖✔ ♥ እግዚአብሔር በታቦቷ ምክንያት የአቢዳራን ቤት እንደባረከ ኹሉ የዘካርያስንም ቤት በእመቤታችን ምክንያት የባረከው መኾኑን ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በመጽሐፉ ሲገልጽ ‹‹ድንግል በምስጢር የተመላ ታቦትን ኾና ትኖራለች፣ የካህናት ወገኖችም ደስ ይላቸዋል፣ ያከብሯታልም›› በማለት ታቦትነቷን አጒልቶ አስተ ❖✔♥ በተጨማሪም የእግዚአብሔር ታቦት ከቤተ አቢዳራ ወደ ዳዊት ከተማ ስትገባ፤ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ከደስታው ብዛት የተነሣ የጌታ የክብሩ መገለጫ በኾነችው በታቦቷ ፊት እየዘለ

ለ እንዳመሰገነ ኹሉ (፪ሳሙ ፮፥፲፪-፲፭)፤ አካላዊ ቃልን በማሕፀኗ የተሸከመች የአምላክ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ወደ ተራራማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ታላቁ ነቢይ መጥምቁ ዮሐንስ በእናቱ ማሕፀን ኾኖ ከደስታው ብዛት የተነሣ እየዘለለ አመስግኗል (ሉቃ ፩፥፵፩-፵፭)፡፡
❖✔♥ ይኽነን ምስጢር ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሲያብራራ፦ "ንጉሡ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ይዘል ነበር፤ ከልቡ ደስታ የተነሣ ለንጉሣውያኑ ደንብ አልታዘዘም፤ እንዲኹ ዮሐንስ ደግሞ ገና ፅንስ ሣለ ከደስታው የተነሣ ከዳዊትም በላቀ ኹኔታ ዘለለ፤ ፅንስ ቢኾንም የእርሱ ባልኾነው በዚኽ ዕድሜ አልተገታም፤ ድንግል እና ቡርክት የኾነችው እናት የእግዚአብሔር ቤት ምስጢራት ከመሉባት ታቦትም በላይ ውብ ነበረች፤ ዳዊትም በአክብሮት በታቦቱ ፊት ዘለለ፤ ይኽም ዮሐንስ በማርያም ፊት ሊዘል እንዳለ አስቀድሞ ያሳይ ነበርና፤ ከዳዊት በቀር ንጉሥ መዝለሉ ተሰምቶ አይታወቅም፤ ሕፃን መዝለሉም እንዲኹ፤ ነቢያት ካህናት የእግዚአብሔርን ልጅ መንገድ አስቀድመው አመለከቱ፤ ርሱም በመጣ ጊዜ ይሹት የነበሩትን ምልክቶች ፈጸማቸው፤ የጌታውን የንጉሡን ምልክት ይጠቁም ዘንድ፤ ዳዊት በደስታ በታቦቱ ፊት ዘለለ፤ዮሐንስ በማርያም ፊት የሚያደርገውን ነገር ምሳሌ በመኾን አሳየ፤ ያቺም ብላቴና እንዲኹ የእግዚአብሔር ታቦት ነበረችና፤ የምስጢራት ጌታ በርሷ ዐደረ፤ ከዚኽም የተነሣ ልክ እንደዚያ ጀግና ንጉሥ ሕፃኑ በርሷ ፊት በደስታ ዘለለ፤ ርሷ በቅዱስ ቃል እንደተመላ ታቦት የተሸከሟት ነበረች፤ የትንቢት ምስጢራት ፍቺ በርሷ ዐደረ) በማለት ይኽ ምሁር ቅድስት ድንግል ማርያምን በምስጢር የተመላች የአምላክ ታቦት መኾኗን በማብራራት ገልጦታል፡፡
❖✔ ዳግመኛም ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በደስታ ሲያመሰግን አይታ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ብትንቀው እግዚአብሔር ተቈጥቷት በሕይወቷ ዘመን ኹሉ የልጅ ጸጋ እንዳታገኝ በምክነት ቀጥቷታል (፪ሳሙ ፮፥፳-፳፫)፡፡ ይኸውም ማደሪያው የኾነች ታቦቷን በድፍረት ሊነካት የሞከረውን ኦዛን የቀሠፈ፤ ዳግመኛ የጌትነቱ መገለጫ በኾነች በታቦቷ ፊት ያመሰገነ ዳዊትን የናቀች ሜልኮልን በምክነት የቀጣ አምላክ፤ ዛሬም ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን፤ የድንግልና ጡቶቿን የመገበችውን፤ በዠርባዋ ያዘለችውና በደረቷ የታቀፈችውን ቅድስት እናቱን በድፍረት የሚነቅፉ፤ ሔዋንን ያሳተ እባብ መርዝ ክሕደቱን በአፋቸው የረጨባቸው በልቡናቸው ያሳደረባቸው፤ ነቢያት ሐዋርያት ያስተማሩትን የሚያጣምሙ ፀረ ማርያሞች ለዚኽ ድፍረታቸው ንስሓ ካልገቡ የዘላለም ቅጣትና፤ በዚኽ ዓለምም ከድንግል ማርያም አማላጅነት የሚገኘውን ታላቅ በረከት በማጣት እንደ ሜልኮል የበረከትና የጸጋ ምክነት ያጋጥማቸዋል፡፡
❖✔ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ስለሚደርስባቸው ዘላለማዊ ምክነት በመዝ ፻፳፰፥፭-፰ ላይ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ይፈሩ፤ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ፤ በሰገነት ላይ እንደበቀለ ሣር ሳይነቀል እንደሚደርቅ ለሚያጭደው እጁን፤ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ ዕቅፉን እንደማይመላ ይኹኑ፤ በመንገድም የሚያልፉ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይኹን በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም›› በማለት እንደተናገረ ጽዮን የተባለች የድንግል ማርያም አማላጅነት የሚቀዋወሙ የዲያብሎስ የግብር ልጆች መናፍቃን እንደ ሜልኮል ከእግዚአብሔር ጸጋ የራቁ ናቸው።
❖✔ ከሊቃውንትም አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ፡-
"እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦት ሕግ ከመ ዘፈነ
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ሥነ
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቊርባነ
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ ››
(አንቺን ያስገኘ የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት ሜልኮል እስከናቀችው ድረስ በእግዚአብሔር የሕግ ታቦት ፊት እንዳመሰገነ፤ ድንግል ሆይ እኔም በሥዕልሽ ፊት እዘምራለኍ፤ ድንቅ ታምርሽንና የቀረበ መንፈሳዊ ምስጋናሽን የሚንቅ በመላእክትና በሰው አንደበት የተረገመ ይኹን) በማለት ገልጿል፨
❖✔ በተጨማሪም ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በምስጢር በመራቀቅ ቅድስት ድንግል ማርያምን “በምስጢር የተመላች ታቦት፣ የቃል ኪዳን ታቦት፣ እሳትን የተመላች ታቦት፣ የቅዱስ ቃል ታቦት” በማለት እያብራራ ያስተማረው የነገረ መለኮት ትምህርት እጅግ ጥልቅ ነው ፡፡
[የአምላክ ታቦት እመቤታችን ሆይ እንወድሻለን]

" እመቤታችንን ሳስብ
➡️ ከህሊናት ሁሉ በላይ የሆነ ለዚህ አንክሮ ይገባል ፤ ምድራዊት ሴት ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ "" ( ቅዱስ ኤፍሬም )
➡ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው። እመቤታችን ከልጇ ጋር አብራ 30 አመታት አብራ በአንድ ቤት ስትኖር የነበራቸው ንግግር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደመሆኑ ጸሎትም ጭምር ነው ። በዚህን ሁሉ ጊዜ ምን ይነግራት
ይሁን ? ስለ የትኛው ሚስጥር ሲገልጥላትስ ነበር ? ጌታችን ሚስጢርን ለወዳጆቹ በነገራቸው ጊዜ ፦ " እርስ በርሳቸውም። በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን #ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።"
(የሉቃስ ወንጌል 24:32) ታዲያ እመቤታችን እንዴት በልጇ ፍቅር ሚስጢር ይቃጠል ነበር ?
➡ እመቤታችን ቅድስት የሆነችው አምላክን ስለወለደች ብቻ ሳይሆን አምላክን የወለደችው ቅድስት ስለሆነች ጭምር ነው።
➡ እመቤታችንን የጭንቅ አማላጅ እንላታለን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን በተሰደደ ጊዜ
ማለትም አይሁዶች ሊገሉት ባስጨነቁት ጊዜ በእመቤታችን እቅፍ እንደተሸሸገ እኛም ሲጨንቀን በእመቤታችን እቅፍ ውስጥ ሹጉጥ እንላለን ምክንያቱም በዮሐንስ በኩል እናት ትሆነን ዘንድ ተሰጠናለች።
➡ ጌታችን ገና ሲወለድ በአይኑ ያያት እመቤታችንን ነው። እንዲሁ ተፈጸመ ብሎ ከዚህ ዓለም ሲሄድ በመስቀል ስር ያያት እመቤታችንን
ነው።
➡ እመቤታችንን እንደ አንድ ክርስትያን ምእመን ማየት የለብንም ምክንያቱም ጌታችን ስትጸንሰው የጸነሰችው ክርስትናን ነውና።
➡ የሔዋን እግዚአብሔርን መጠራጠርና ወደ ዲያብሎስ
ማዘንበል ሞትን ማምጣቱን የሚያምን ሁሉ የእመቤታችን በእግዚአብሔር ላይ የነበራት ፍጹም እምነት ሕይወትን ወደ ዓለም ( ወደ ሰው ሁሉ ) እንዲገባ በር መክፈቱን ማመን ግድ ይለዋል። ይህን አለማመን ኢምክንያታዊም ኢፍትሐዊም ነው።
➡ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ
( ይሁንልኝ እንደቃልህ ይደረግልኝ ) ፦ በመጀመሪያ እግዚአብሔር በጥቅጥቁ ጨለማ ብርሃን ይሁን እንዳለ እመቤታችንም ብርሃነ ዓለም ክርስቶስን ሥጋን
እንዲዋሀድ ይሁንልኝ ያለችው እመቤታችን ነች።
እንኳን ለእመቤታችን አመታዊ በዓል አደረሳችሁ

የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ
ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ ለማግኘት ሲፈልጉ ቻናላችንን ይጎብኙ::
ለመቀላቀል ከስር ሰማያዊውን ይጫኑ
JOIN OUR CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር

በአንድ ጊዜ አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር በመሆን ለአደን ይወጣሉ አደኑም ይሳካላቸውና ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማደናቸውን ይቀጥላሉ ታዲያ በሦስተኛው እለት ንጉሱ የማደኛ ጦሩን ሊወረው ሲል ጦሩ የጋዛ እጁን ይቆርጠዋል በዚህ ጊዜ አብሮት የነበረው አሽከር ወደ ንጉሱ ቀረብ ብሎ ንጉስ ሆይ ለበጎ ነው ይለዋል ንጉሱም በጣም ይናደድና እንዴት ብትዳፈረኝ ነው እጄ ተቆርጦ እያየህ ለበጎ ነው የምትለኝ ይልና ያንን አሽከር ወደ እስር ቤት ይወረውረዋል ከዚያም በማግስቱ ለአደን ለብቻው ይወጣል ትንሽ ወደ ደኑ እንደተጓዘም ከየት ወጡ ያላላቸው ሽፍቶች ይይዙትና ለጌታቸው አርደው ሊሰዉት ይወስዱታል ታዲያ መስዋዕቱን የሚፈፅወው ሠውዬም ንጉሱን ሲመለከት እጁ እንደተቆረጠ ያስተውላል ሽፍቶቹ ለጌታቸው የሚሰዉት ሙሉ አካል ያለውን ነበርና ንጉሱ እጁ ስለተቆረጠ በሰላም እንዲሄድ ያደርጉታል በዚ ጊዜ ንጉሱ በቀጥታ ወደዛ ወደአሳሰረው አሽከሩ ጋር ይሄድና አንተ ልክ ነበርክ ያ ነገር የሆነው ለበጎ ነው እኔ ግን አንተን አሳሰርኩህ ይለዋል አሽከሩም ቀበል አድርጎ ንጉስ ሆይ መታሰሬም ለበጎ ነው ባልታሰር ሙሉ አካል ስላለኝ ሽፍቶቹ እርሶን ለቀው እኔን ይሰዉኝ ነበር በማለት መለሰ፡፡
በህይወታችን ብዙ ፈተና ሊገጥመን ይችላል ያውም እኛ መልካም ነገር ከምናስብላቸው ከምንመኝላቸው የኛ ከምንላቸው ሰዎች ሊሆን ይችላል ፈተናው የሚመጣው ግን ሁሉ ለበጎ ነው ፡፡
Send this Address to your Friends to JOIN OUR CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
በህይወታችን ብዙ ፈተና ሊገጥመን ይችላል ያውም እኛ መልካም ነገር ከምናስብላቸው ከምንመኝላቸው የኛ ከምንላቸው ሰዎች ሊሆን ይችላል ፈተናው የሚመጣው ግን ሁሉ ለበጎ ነው ፡፡
Send this Address to your Friends to JOIN OUR CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
አንዲት ወጣት እንስት እናትዋን ዝሙት ትፈፅም ዘንድ ታስፈቅዳታለች እናትየዉም በእርግጥም የፈለግሽዉን ነገር ከመፈፀምሽ በፊት ለአንድ ሳምንት የማዝሽን መፈፀም ይኖርብሻል ስትል አቆሙዋን ታሳዉቃለች። እናትየዉም እንዲህ ስትል ታዛታለች ወደ ንጉሱ ቤተ መንግስት ሂጂና ልክ ንጉሱ ከቤተ መንግስት ሲወጣ እራሱን እንደሳተ ሰዉ ዉደቂ ልጅየዉም ልክ እንደተባለችዉ እራስዋን ስታ ትወድቃለች ንጉሱም እራሱ ከሰረገላዉ ላይ ወረደና ሙሉ እንክብካቤ እንዲደረግለትና እቤትዋ እንዲያደርስዋት አዘዘ በሚቀጥለዉ ቀንም ንጉሱ ከቤተመንግስት ሲወጣ ዳግም እራስዋን ስታ ወደቀች ንጉሱም ችላ ብሎት አለፈ ዞር ብሎ እንኯን አልተመለከታትም ጠቅላይ ሚኒስትሩm ከወደቀችበት ያነሳታል በሶስተኛዉ ቀን እሱም ይተዋትና የዘበኞች አለቃ ያነሳታል በአራተኛዉ ቀን አለቃዉም ትቶዋት አንድ ተራ ወታደር ይነሳታል በስድስተኛዉ ቀን ግን እሱም ቀርቶ ሰዋች እየገፉ ወደ ዳር ያወጥዋታል። እንደተለመደዉ በሰባተኛዉ ቀንም እራሱን እንደሳተ ሰዉ ወደቀች ይኸኔ ግን ፊትዋን ከሚልሳት ዉሻ ዉጪ ምንም ነገር አላገኝችም። ከዚያም እናቷ ተግባር የታከለበት ምክሯን እንዲህ ለገሰች። በማሕበረሰቡ ዉስጥ ክብሯን ያጣች ሴት ምሳሌም ይኼዉ ነዉ በመጀመርያ የተከበረች ሴት በመሆንዋ ሁሉም ይንሰፈሰፍላታል። ክብርዋን ስታጣ ግን ፈላጊዋ ይጠፋል፥ ሁሉም እንዳሻዉ ይጫወትባታል በመጨረሻ ግን ማንም የማይፈልጋት ርካሽ እቃ ትሆናለች ስትል ልጅዋን በጥበብ አስተማረቻት!!!
ድንግልና ክብር ነው ድንግልናችንን በአግባቡ እንጠብቅ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘንድም ዋጋው ከፍ ያለ ነውና::
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ድንግልና ክብር ነው ድንግልናችንን በአግባቡ እንጠብቅ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘንድም ዋጋው ከፍ ያለ ነውና::
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👉 @ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
አንድ 60ሰዎችን የገደለ ወንበዴ ወደ አንድ አባት መጥቶ ንስሃ ስጡኝ 60 ሰው ገድያለው አላቸው እሳቸው አንተማ ሰይጣን ነህ ከኔ ራቅ ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸውና ሄደ። : ሌላ ቄስ አገኘ "አባቴ ንስሀ ይስጡኝ 60 ሰው ገድያለው ይህንንም ብየ የጠየክዋቸው ካህን ሰይጣን ብለውኝ እሳቸውንም ገድያለው "ካህኑም አንተ አረመኔ እኔንም ልትገድለኝ ነውን? ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸው በዚህ ሁኔታ ሌላ ሁለት ካሀህናትንም ገድሎ ወደ ለመደው ውንብድናው እየሄደ ሳለ አንድ ሽማግሌ መነኩሴ ውሃ ሊቀዱ እየሄዱ አገኘና አንቱ ሽማግሌ ይቁሙ አላቸው። : "አቤቴ 60 ሰዎቹን ገድየ ንስሃ ልገባ ብጠይቅ አልፈቅድ ብለውኝ 4 ካህናትን ገድያለው እርሶንም ንስሃ
ማይሰጡኝ ከሆነ እገድሎታለው "አላቸው። : አሳቸውም ስቅስቅ ብለው አለቀሱለት "በእውነት እግዚአብሄርን በድለሃል አስከፍተሀል ግን መሃሪ አምላክ ነው" አሉት ከዛም ወደ ጉድጉዋድ ወሰዱትና : "ላንተ እጸልይልህ ዘንድ የጸሎት መጸሃፌ እዚ ወድቆዋልና አውጣልኝ "አሉት ከዛ ወደ ጥልቁ በገመድ አንጠልጥለው አስገቡት መግባቱን ሲያረጋግጡ ገመዱን ቆረጡ።
ወንበዴውም አንተ ሽማግሌ እገድልሃለው እያለ መዛት ጀመረ ትተውት ሄዱ። ከ 9 ሰአት በወኋላ ቂጣ እና ውሃ ይዘው መጥተው
"ልጄ እንዴት ነህ "አሉት እገድልሀለው አለ ምግቡን ሰጥተውት ሄዱ። : ከ12 ሰአት በውሃላ ተመለሱ "ልጄ እንደምን አለህ "
ደከም ባለ ድምጽ እገድልሀለው አለቅህም ምግብ ሰጥተውት ሄዱ። : 1ቀን ቆይተው መጡ "ልጄ እንደምን አለህ " "እ..ገ..ድል..ሀለው" አለ እጅግ በደከመ ድምጽ ምግቡን ሰጥተውት ሄዱ አንድ ቀን ቆይተው ተመለሱና "ልጄ እንደምን ዋልክ" ሲሉት """እግዚአብሄር ይመስገን""" አለ ትዕቢቱ በጾም ተሸነፈ ነብስ ስጋን አሸነፈች እሳቸውም በገመድ አውጥተው ንስሃን ሰጡት የአምላክ ባርያ ሆኖም ኖረ''
የተባረከ ፃም ይሁንልን!
Share this Address with your Friends to JOIN OUR CHANNEL

እሳት የእግዚአብሔር #የወርቅ_ማዕጠንት የእመቤታችን ወርቅ የንጽሕናዋ ማዕጠንቱ እሳቱን እንደተሸከመ እመቤታችንም ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ የመሸከሞ ምሳሌ
JOIN OUR CHANNEL
@ethiopianorthodoxbooks