" እመቤታችንን ሳስብ
➡️ ከህሊናት ሁሉ በላይ የሆነ ለዚህ አንክሮ ይገባል ፤ ምድራዊት ሴት ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ "" ( ቅዱስ ኤፍሬም )
➡ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው። እመቤታችን ከልጇ ጋር አብራ 30 አመታት አብራ በአንድ ቤት ስትኖር የነበራቸው ንግግር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደመሆኑ ጸሎትም ጭምር ነው ። በዚህን ሁሉ ጊዜ ምን ይነግራት
ይሁን ? ስለ የትኛው ሚስጥር ሲገልጥላትስ ነበር ? ጌታችን ሚስጢርን ለወዳጆቹ በነገራቸው ጊዜ ፦ " እርስ በርሳቸውም። በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን #ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።"
(የሉቃስ ወንጌል 24:32) ታዲያ እመቤታችን እንዴት በልጇ ፍቅር ሚስጢር ይቃጠል ነበር ?
➡ እመቤታችን ቅድስት የሆነችው አምላክን ስለወለደች ብቻ ሳይሆን አምላክን የወለደችው ቅድስት ስለሆነች ጭምር ነው።
➡ እመቤታችንን የጭንቅ አማላጅ እንላታለን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን በተሰደደ ጊዜ
ማለትም አይሁዶች ሊገሉት ባስጨነቁት ጊዜ በእመቤታችን እቅፍ እንደተሸሸገ እኛም ሲጨንቀን በእመቤታችን እቅፍ ውስጥ ሹጉጥ እንላለን ምክንያቱም በዮሐንስ በኩል እናት ትሆነን ዘንድ ተሰጠናለች።
➡ ጌታችን ገና ሲወለድ በአይኑ ያያት እመቤታችንን ነው። እንዲሁ ተፈጸመ ብሎ ከዚህ ዓለም ሲሄድ በመስቀል ስር ያያት እመቤታችንን
ነው።
➡ እመቤታችንን እንደ አንድ ክርስትያን ምእመን ማየት የለብንም ምክንያቱም ጌታችን ስትጸንሰው የጸነሰችው ክርስትናን ነውና።
➡ የሔዋን እግዚአብሔርን መጠራጠርና ወደ ዲያብሎስ
ማዘንበል ሞትን ማምጣቱን የሚያምን ሁሉ የእመቤታችን በእግዚአብሔር ላይ የነበራት ፍጹም እምነት ሕይወትን ወደ ዓለም ( ወደ ሰው ሁሉ ) እንዲገባ በር መክፈቱን ማመን ግድ ይለዋል። ይህን አለማመን ኢምክንያታዊም ኢፍትሐዊም ነው።
➡ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ
( ይሁንልኝ እንደቃልህ ይደረግልኝ ) ፦ በመጀመሪያ እግዚአብሔር በጥቅጥቁ ጨለማ ብርሃን ይሁን እንዳለ እመቤታችንም ብርሃነ ዓለም ክርስቶስን ሥጋን
እንዲዋሀድ ይሁንልኝ ያለችው እመቤታችን ነች።
እንኳን ለእመቤታችን አመታዊ በዓል አደረሳችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉@ethiopianorthodoxbooks 👈
👉@ethiopianorthodoxbooks👈
👉@ethiopianorthodoxbooks 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆