የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
🌺 የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አትጥራ!

የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት ሲባል ምን ማለት ነው? የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም የከበረ በመሆኑ እንደተገኘ የሚጠሩት፣ እንደአጋጠመ የሚናገሩት አይደለም፡፡ ይልቁንም በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በትሕትና ሆነው ሊጠሩት የሚገባ ክቡር ስም ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም ያለአግባብ በነገራቸው ሁሉ ውስጥ ሲያስገቡት፣ ሥፍራም ጊዜም ሳይመርጡ እንደፈለጉት ሲጠሩት ይስተዋላሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች እምነትና ፊሪሃ እግዚአብሔር አላቸው ለማለት አያስደፍርም፤

ከዚህ ቀጥለን ሰዎች ስሙን በከንቱ የሚጠሩባቸውን ሁኔታዎች ባጭር ባጭሩ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ሀ. መሐላ፡- መሐላ ስመ እግዚአብሔር በከንቱ ከሚጠራባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡ በዘመነ ብሉይ የአምልኮ ጣዖትን ከንቱነት ለመግለጥ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡ በስሙ እንዲምሉ ያዝዝ ነበር (ዘዳ 6&13፤ ኢሳ 45&23)፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ በእግዚአብሔር መማል ብቻ ሳይሆን መሐላ በጠቅላላው የተከለከለ መሆኑን መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ ይህ የሐዲስ ኪዳን ዘመን አረማዊነትና አምልኮ ጣዖት ጠፍቶ ወንጌል የተሰበከበት፣ ክርስትና በዓለም ሁሉ የታወቀበት ነውና መማል አላስፈለገም፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ #ከቶ አትማሉ፤… ቃላችሁ አዎን፣ አዎን ወይም አይደለም፣ አይደለም ይሁን፣ ከዚህም የወጣ ከክፉው ነው$ በማለት መሐላን ከልክሏል (ማቴ 5&34-37)፡፡ ስለሆነም በየሰበቡ የእግዚአብሔርን ስም፣ የቅዱሳንን ስም፣ የመላእክትን ስም ሁሉ እየጠሩ መማል የተከለከለ ነውና ከዚህ መቆጠብ ይገባል፡፡ በተለይም በየአጋጣሚው ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ መማል የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት መሆኑን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks