Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ፍቅራዲስ_ነቃጥበብ #አትርሳኝ
አትርሳኝ ፍቅሬ አትርሳኝ /2x
መውደድ ባታወርሰኝ ፍቅር ባታለብሰኝ
አትርሳኝ ፍቅሬ አትርሳኝ
ሄደሀል አሉኝ ብዙ ርቀህ
እንደኔ ሆነህ አንተም ናፍቀህ
ምን አለ ሆዴ ብትመጣልኝ
ብታስብልኝ አካል ገላዬ
እንዲህ በትንሹ አካል ገላዬ
እንዲህ በመጠኑ አካል ገላዬ
መቼ ይዘለቃል አካል ገላዬ
ያሳለፍነው ሁሉ አካል ገላዬ
ላንተ ይመስልሀል አካል ገላዬ
የተጓዝክ እርቀህ አካል ገላዬ
ውሎ ማደርያህን አካል ገላዬ
ልቤን መቼ ለቀህ
አንተን ልርሳህ ወይ ጉዴ
እንዴት ይሆናል መውደዴ
ይብዛም ይነስም ተዋደን
አሳልፈናል ጥሩ ቀን
ሄደህል አሉኝ ብዙ ርቀህ
እንደኔ ሆነህ አንተም ናፍቀህ
ምን አለ ሆዴ ብትመጣልኝ
ብታስብልኝ
ከመሰለህ ናልኝ ካልመሰለህ ይቅር
የምተካው የለም እኔስ ባንተ ፍቅር
ልቤ አይደነግጥም የትም ልሂድ የትም
አስመስሎ መውደድ እኔ አላውቅበትም
አትርሳኝ ፍቅሬ አትርሳኝ
መውደድ ባታወርሰኝ
ፍቅር ባታለብሰኝ
አትርሳኝ ፍቅሬ አትርሳኝ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ቴዎድሮስ_ታደሰ #በመዋደዳች
በመዋደዳች ስንቱን ችግር አየን
ለፍቅር ባደርን ስንቱን ፈተና አየን
ሀሜተኛም በአፉ ላይበትን ላይለየን
እንዳው ባሉባልታ በክፋት በሀሜት
እያደባ አጋየን ቢመች አመላችን ሰክኖ
ቢችላቸው እየለሰለሰ መሬት ቢሆናቸው
ማረሻ ሞፈሩን ተቸግረው ገጥመው
ቀንበር ሲያበጁልን ብዙ ጊዜ ደክመው
ሊያጣምዱን መጡ ቀንበር ተሸክመው
ሳይዙ ማስጠጋት ሳያርሙ ማገድ
ሳይጨብጡ መዝራት ሳያርሙ ማጨድ
እሄም ስራ ሆኖ ሀሜትን መፈትፈት
እንደሸት ሰመመን ኑሮን መከፋፈል
ሊበትኑን ካሉ ሊለዩን በወንፈል
መውደዴ የትም ቢወራ ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
ሀሜኛ ቤትም አይሰራ ተንኮልም ፍሬ አያፈራ
መውደዴ የትም ቢወራ ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
ለተንኮል ሁሉም ቢዳዳ ሀሜትም ያልቃል በጐዳ
ይሁን ይሁን ብለው ቢነሱ ለሀሜት
ያረባ ዝማሬ መች ይነካል ስሜት
ሳይተከል እሸት ሳይታረም ፍሬ
ይሰምራል እያሉ ከነገ ከዛሬ
አጥፍተዋል ብዙ በፍቅርሽ በፍቅሬ
ሲወራ ሲናፈስ ሀሜት ቢታክትም
እህ ብለሽ ተይው አፍ አይመከትም
የኔም ባንቺ ሊቀር የንችንም ልችለው
ምነው ሰውን ሁሉ ጭንቅ ጥብብ አለው
አይወድቅም አይፈርስም ለኛ ካለው
መውደዴ የትም ቢወራ ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
አፈኛ ቤትም አይሰራ ተንኮልም ፍሬ አያፈራ


Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ሳያት_ደምሴ #እስክሽር
እየታወሰኝ ነው ቃልኪዳን ስትገባ፤
አይኖችህ በእውነት ተሞልተው በእንባ።
አምኜው ሲናገር ልቤን ብረታለት፤
እሱ ተጫወተ በቃል በቀለበት።
ፍቅርህ አሸንፎኝ ተሞኘሁኝ ወይኔ፤
ጨዋታ ነው ላንተ እንደዛ መሆኔ፤
መሬት አይንካሽ ሲል እንዳልነበር ያኔ፤
የ እግ'ዜሩ ሰላምታ አጥሮህ አየሁ ለኔ፤
ለመርሳት የሚሆን አቅም ባይኖረውም (ገላዬ)3*
ላልቅስልህ ላውርድ ይፍሰስልህ እንባዬ፤
በምችለው ልካስ ላልቅስልህ ባይኔ፤
ላልቅስ ላልቅሰው ባለው በአቅሜ፤
ሳቄን ለሰው ሰጠህ ቀምተኸኝ ከኔ።
አሁን አቅም አለኝ ላንተ የሚበቃ፤
ፍቅርህ እንዲቀለኝ (ጉልበቴ ነው እንባ)2*
ይብላኝ እንጂ ላንተ ለሄድከው በባዶ፤
እኔስ ፍቅር አለኝ አልሆንኩም ጎዶሎ።
አሁንም ይወራል ትተኸኝ መሄድህ፤
ማን በነገራቸው መንገድ ነው ቅጣትህ፤
አየሁትን ፍቅርህን ከቀለበት ሾልከህ፤
እንዲያው ያወጣሀው ቃላት አልከበደህ።
ኧረኧረኧረኧረ... . ........ . . . . .
እንዴት ቀሎብህ ነው እንዴት ቢታይህ፤
የኔ መሆን ያነሰብህ ኧረኧረኧረ.... ..
ልብህ ግንድ ብቻ አያፈራ ፍሬ፤
በምችለው ባለኝ ላልቅስለህ ባይኔ።
ላውርደው እምባዬን ላልቅስ ላንጎራጉር፤
በአባ መላ ጊዜ ከህመሜ እስክሽር፤
ግን ትንሳኤው ቅርብ ነው ለተረታ በፍቅር።
እህእህእህ.......
ለመርሳት የሚሆን አቅም ባይኖረው ገላዬ፤
ላልቅስልህ ላውርድ ይፍሰስልህ እምባዬ(3*)

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አህመድ_ተሾመ #ፅጌረዳ
ስምሽን እንዳልጠራ ያቁብኛል ብዬ
ፅጌረዳ አልኩሽ አበባ አስመስዬ (2x)
ዉብ ፀዓዳሽ እርካታዬ ፅጌረዳ አበባዬ
ዉብ ቀለምሽ ቢስበኝም
እሾህሽ ግን አልፈጀኝም
የፈጣሪ ዉብ ቱርፋት ፅጌረዳ
የአንድ ዛፍ ግለዉበት ፅጌረዳ
የዉቦች ዉብ የምድር ንግስት ፅጌረዳ
ቀልብ ሳቢ ልዩ ፍጥረት ፅጌረዳ
ተናዳፊ እንደ ጓድሽ እንደ
ንቧ እንደአምሳያሽ
በኅብረ ቀለም ያሸበረቅሽ
አንበርካኪ በዉበትሽ
ይህን ሁሉ ዉበት ሰጥቶሽ
አምላክ መላ ዘየደልሽ
የተመኘሽ እንዳይቀጥፍሽ
እሾህሽን አበዛልሽ አበዛልሽ
ስምሽን እንዳልጠራ ያቁብኛል ብዬ
ፅጌረዳ አልኩሽ አበባ አስመስዬ (2x)
ዉብ ፀዓዳሽ እርካታዬ
ፅጌረዳ አበባዬ
ዉብ ቀለምሽ ቢሰበኝም
እሾህሽ ግን አልፈጀኝም
የፈጣሪ ዉብ ቱርፋት ፅጌረዳ
የአንድ ዛፍ ግለዉበት ፅጌረዳ
የዉቦች ዉብ የምድር ንግስት ፅጌረዳ
ቀልብ ሳቢ ልዩ ፍጥረት ፅጌረዳ
ደልዳይ ቀርቦ ይህን ሲያለብስ
ለፍጡር ሁሉ ሲያደርስ
ይህን ሁሉ ዉበት ሰጥቶሽ
አምላክ መላ ዘየደልሽ
የተመኘሽ እንዳይቀጥፍሽ
እሾህሽን አበዛልሽ
በዉብ ቀለም አንቆጥቁጦሽ
በአንዱ እሾህ አደረገሽ
አደረገሽ አደረገሽ አደረገሽ አደረገሽ….

Shear to your best friend for more lyrics my@ethiopian_music_lyrics
#ብዙነሽ_በቀለ #ፍቅሬ_ደህና_ሁን
አረ እንዴት ነው በሉት አረ እንዴት ነው
ቆረጠለት ወይስ አረ እንዴት ነው
አረ እንዴት ነው በሉት አረ እንዴት ነው
ተረሳ ወይ ፍቅሩስ አረ እንዴት ነው
ስንገበገብ አሃ ስናፍቀው አሃ የዘገየው
የኔስ ነገር አሃ እንዴት እንዴት አሃ ሆኖ ታየው
የራሴው ፍቅር የራሴው መውደድ ባመጣው ጣጣ
ዛሬ ስላንተ እንዴትስ ካፌ ክፉ ቃል ይዉጣ
ለማንስ ሄጄ ስሞታ ብዬ እናገራለሁ
እንደው በሆዴ እኔ ብቻዬን እችለዋለሁ
ደህና ሁን ፍቅሬ ደህና ሁን
ደህና ሁን ፍቅሬ ደህና ሁን
ደህና ሁን ፍቅሬ ደህና ሁን
አረ እንዴት ነው በሉት አረ እንዴት ነው
ቆረጠለት ወይስ አረ እንዴት ነው
አረ እንዴት ነው በሉት አረ እንዴት ነው
ተረሳ ወይ ፍቅሩስ አረ እንዴት ነዉ
ስንገበገብ አሃ ስናፍቀዉ አሃ የዘገየዉ
የኔስ ነገር አሃ እንዴት እንዴት አሃ ሆኖ ታየዉ
ታማኙ ልቤ ባንተ ትዝታ ተጨንቆልሃል
አወክበት ወይ አንተስ መለየት እንዴት አርጎሃል
እኔስ በሀሳብ ሆዴ ቢቃጠል ልቤ ቢከስልም
ስስቅ ስጫወት ያጣሁ የከፋኝ የአዘንኩ አልመስልም
ደህና ሁን ፍቅሬ ደህና ሁን
ደህና ሁን ፍቅሬ ደህና ሁን (x3)
ደህና ሁን ፍቅሬ ደህና ሁን

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ኤፍሬም_ታምሩ #መልካም_ውለታ
ብትውልም መልካም ውለታ
ስለሰው ብትንገላታ
ከሌለህ ማን አለ ደጅህ
ኪስህ ነው የቅርብ ወዳጅህ
የችግር የሀሳብ ሰቀቀን
ቢገጥመህ ባልታሰበ ቀን
ቢሆጎድል ጓዳው ማጀትህ
እርሾ ቢጠፋ ከቤትህ
ተው ተው አትሂድ ከሰው
ሆድህን እንዳታስብሰው
ሆድህን ቢርብ ቢጠማህ
ልብህን ጭንቀት ቢሰማ
አላፊ ነው እንደዋዛ
ለሰው ምፅዋት አትገዛ
ከሌለህ ማን አለህ ደጅህ
ኪስህ ነው የቅርብ ወዳጅህ
ከጎጆህ ቅሪት ብታጣ
ችግር ሰንደቁን ቢያወጣ
በሀሳብ ገላህ ቢከሳ
አንተነትህን አትርሳ
ቢለየም ሚዛን ክብደቱ
ሰው ነው ሰው በሰውነቱ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ፀሐዬ_ዮሃንስ
#የዋህ_ልቤ
የዋህ ልቤ እንግዲህ ቅመሠው
ለምን አመንክ የማይታመን ሰው
ስትከታላት በልጣብህ ከእኔ
ይህ ይመጣል መች ያልክ ያኔ (2x)
ይገርመኛል እኔ የአንተ ማንገራገር
ጊዜህ ሲጠፋ ባበቃ ነገር
ወይ አላወክበት ሰዶ ማሳደዱን
በራስህ ጥፋት የመጣውን ጦስ
በል ቻለው መንደዱን
ምነው በቀድምካት
ያን ጊዜ ሳትቀድምህ
ሠላም ሳታጣ እንዲህ ሳያምህ
የእርሷን ሳትቀበል
የአንተን ማን ስጥ አለህ
እንደ ጥፋትህ ቅጣትህ አንሷል
ልቤ እድለኛ ነህ
እንግዲህ ልቤ አደብ ግዛ
ጭንቀት ሃዘንህ አይብዛ
ያን ፍቅሯን ላታገኝ
የማይሆን ስትመኝ
እርሷን እርሷን ስትል
ልበ ቢስ አታድርገኝ
በጅምሩ ነበር እሳትን በቅጠል
ውስጥ ውስጡን ነዶ ሳይቀጣጠል
የወደደ እራሱን ይጎዳል ይባላል
ልቤ ያንተ ግን እራስን መጣል ነው
ፍቅር አይባልም
የትርታዬ ዋስ ልቤ ዋስትናዬ
ዘመድህ እኔ ነኝ ሠላም ጤናዬ
ለምን አትተዋትም እንደ እርሷ ወስነህ
ያለፈው ስትል ጊዜ ቢያልፍብህ
ተጎጂው አንተ ነህ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
አርቲስት ንዋይ ደበበ ከነባሩ ቱባ የስነቃል /ስነ ግጥም/ ውርሳችን
በአሰነኛኘት ይትባህል የዜማ ግጥሞቻቸውን ከሚቀምሩ ጥቂት
ሁለገብ ድምፃውያን መሃል ግንባር ቀደሙ ከያኒ ነው፡፡
ለዚህ ሃሳ ሁነኛ ማሳያ የምትሆነውን ይቺን ተጋበዙልኝ፡፡
"ጥላ ይዤ--"
-
እኔም አልነገርኳት-አሷም አላዘነች፤
ሄደች ለመኝታ-እየተለመነች፡፡
ከብቱም በረት ገባ-ወፉም ተባበራት፤
እንቅልፍ ሊወስደው-ለእርሷ እያበደራት፡፡
በተረት በተረት-በአጓጉል ጨዋታ፤
ቀኑ በቀልድ ያልፋል-ሌቱ በመኝታ፡፡
ተስማምቶኝ እያለ-ብትደጋግሚኝም፤
አንቺን ካልከበደሽ-ለኔ አልሰለቸኝም፡፡
-
ጥላ ይዤ ልከተልሽ፤
ዝናብ ጸሃዩ እንዳይጎዳሽ፡፡
ጋሻ ይዤ ልከተልሽ፤
የኔ ቆንጆ ላስከብርሽ፡፡
-
አመል አመሏ እኮ ነው፤
የሚያንከራትት የሚያባዝነው፡፡
መልክስ መች አንሷት እንከን ጎደለ፡፡
ወዲያው ስትል ቆጣ ወዲያው ስትል ኩርፍ፤
ይለይላት ብዬ እኔም ትቻት እርፍ፤
ከጎጆዬ ገባሁ-እጅ እግሬን ሰብስቤ፤
አጉል እልህ ገጥሞ ተጠቃ እንጂ ልቤ---
-
ንቧም ተናዳፊ- ውሻዋም ተናካሽ፤
እርሷም ሰው አስከፊ-እኔም ኩሩ ታጋሽ፡
ተስፋም አልቆርጥ እኔ-እርሷም እልኸኛ፤
በቁም ገላ ቀብራኝ -ትፎክርብኛ፡፡
አያት አሳድጓት -ለአመሏ ብትቀብጥም፤
ከመለመን በቀር -እንከን የለባትም፡፡
እንዳማራት ቀረ-እኔም ሳልሞክራት፤
ይኼ አጎል መግደርደር-ጦም እያሳደራት፡፡

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አብነት_አጎናፍር #ስሚኝ
እስካገኝሽ ችዬ እንዲገባሽ ብዬ
አምነሽ ብትመጭ እያልኩኝ
ናፍቄ እየቻልኩኝ
ስትሸሽኝ አጥፍተሸ ተከትዬ ባቅፍሽ
ምን ሊጠቅምሽ/2x
ለማለፍ ያቺን ቀን ሊደገም ቀን በቀን
ምን ሊጠቅመን /2X
ባዝንም ሌላው ቢያስከፋኝ
ማለፍ መተው መች ጠፋኝ
አንቺን አላልፍም የኔን ካላየሽ
ከፍቶሽ መጥቼ ከፍቶኝ ካልመጣሽ
የፍቅር ቅሬታዬን
የመውደድ ዝምታዬን
ደልቶኝ መቼ አቀፍኩት
እስክትመጭልኝ ነው ያፈንኩት
ዝም አልልም ደፍሬ
ባስከፋሽ እኔ አንቺን አፍሬ
የቃል ነውይ ኪሳራ
ለልብ ወዳጅ ላይሰራ
ናፍቆትሽ ቢያመኝም
ሸንግየሽ በርሽን አልከፍትም
ልቤ ይጽዳልሽ ዛሬ
ቢስምሽ ትርፍ ነው ከንፈሬ
ስሚኝ
ስሚኝ
ስሚኝ
አንዴ ስሚው ይንገርሽ
ያውቃል እውነቱን ልብሽ
የኔም ልብ ያውቃል ያንቺ የለውን
ካልሰማናቸው እንዳይለያዩን
ስሚኝ
ስሚኝ
ስሚኝ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#inspirational
1. “ዛሬ ከባድ ነው፡፡ነገ እንዲሁም ይከፋል፡፡ተነገ ወዲያ ግን ፀሐይ ትወጣለች፡፡መቼም
ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ”– Jack Ma
~
2. “ፍላጎቴ መወደድ ሳይሆን መከበር ነው፡፡ ”– Jack Ma
~
3. “ሊኖሩን ከሚገቡ እጅግ ጠቃሚ ነገሮች መካከል ትዕግስት ዋነኛው ነው፡፡”– Jack
Ma
~
4. “ከተፎካካሪህ መማር እንጂ መኮረጅ የለብህም፡፡ኮርጅ.... በኋላ ግን ትሞታለህ፡፡ ”–
Jack Ma
~
5. “ገንዘብ አላጣንም፡፡ያጣነው ህልመኛ ሰዎችን ነው፡፡ብርቅ የሆኑት ለህልማቸው
የሚሞቱ ሰዎች ናቸው፡፡”– Jack Ma
~
6. “በህይወት የሆነ ነገር ስትሞክር፣ የሆነ ነገር ላይ ጠንክረህ ስትሰራና የሆነ ነገር
ስትለወጥ መጥፎ ነገር መከሰት ያቆማል፡፡”– Jack Ma
~
7. “መሬቱ ላይ ዘጠኝ ጥንቸሎች ካሉ ፤ ያንተ ፍላጎት አንዷን ጥንቸል መያዝ ከሆነ እሷ ላይ
ብቻ አተኩር፡፡ ”– Jack Ma
~
8. “መሪ ባለራዕይ መሆን አለበት፡፡ተከታዮቹ ከሚያዩት በላይ አሻግሮ ማየት አለበት፡፡ ”–
Jack Ma
~
9. “ተፎካካሪዎችን እርሳ፡፡ዝም ብለህ ደንበኞችህ ላይ አተኩር፡፡”– Jack Ma
~
10. “ተስፋ ካልቆረጥክ አሁንም እድል አለህ፡፡ ”– Jack Ma
11. “ካልደረከው ምንም ነገር አይቻልም፡፡ ”– Jack Ma
~
12. “ሰዎች ስለአንተ በጣም አካብደው ሲያስቡ የመረጋጋት እና ራስህን የመሆን ሀላፊነት
ሊኖርህ ይገባል፡፡ ”– Jack Ma
~
13. “ጥሩ ቡድን ሆነን ምን ማድረግ እንደምንፈልግ በትክክል ካወቅን አንዳችን አስራቸውን
ማሸነፍ እንችላለን፡፡”– Jack Ma
~
14 “ምርጥ ሰዎችን ሳይሆን ትክክለኛ ሰዎችን ፈልግ፡፡ ”– Jack Ma
~
15. “በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለማሸነፍ ከፈለክ ሰዎች ከአንተ የተሻሉ እንደሆኑ በመንገር
ልታበረታቸው ያስፍለጋል፡፡ይህን ካደረክ ስኬታማ መሆንህ አይቀርም፡፡”– Jack Ma
~
16. “እውነተኛ የቢዝነስ ሰው እና የስራ ፈጣሪ ጠላት የለውም፡፡ይሄን ከተረዳ ምንም ነገር
አይገድበውም፡፡”– Jack Ma
~
17. “ሁሉም ሰው ጠላቴ ነው ብለህ ስታስብ በዙርያ ያለው ሰው ሁሉ ጠላትህ ሆኖ
ታገኘዋለህ፡፡ ”– Jack Ma
18 “የተለየ mindset ካለህ የተለየ ውጤት ታመጣለህ፡፡ ”– Jack Ma
~
19. “መስፈርቱን የሚያሟሉትን አትቅጠር፡፡እብድ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ቅጠር፡፡ ”– Jack
Ma
~
20. “ሰው ምንም ያድርግ ምንም፣ ተሳካለት አልተሳካለት ከስራው የሚያገኘው ልምድ
በራሱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡”– Jack Ma
~
21 “አፋቸውን ብቻ የሚገጠሙት ሞኞች ናቸው፡፡ብልህ ሰው አእምሮውን ጠቢብ ደግሞ
ልቡን ይጠቀማል፡፡ ”– Jack Ma
~
22. “በፍጹም በፍጹም በዋጋ አትፎካከር፡፡በአገልግሎት ጥራት እና በአዲስ ግኝት
ተፎካከር፡፡”– Jack Ma
~
23 .“ቅድሚያ ለደንበኛ ነው፡፡በመቀጠል ሰራተኛ ኢንቨስተር? ሶስተኛ፡፡”– Jack Ma
~
24. “የቱንም ያህል ጎበዝ ብትሆንም እንዴት ከሰው ጋር መስራት እንዳለብህ ካላወክ
ተሸናፊ ነህ፡፡”– Jack Ma
~
25. “የተናከርከውን ቃል አለም ላያስታውሰው ይችላል፡፡ያደረከው ነገር ግን በፍጹም
አይረሳውም፡፡”– Jack Ma
+
26.“ደንበኛ ሲወድህ መንግስትም ይወድሃል፡፡”– Jack Ma
@sera7

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
ታሪክ በዚህ ሳምንት
የቦብ ማርሌ ኢትዮጵያ ጉብኝትና አሳዛኙ የታዳሚ ተቃውሞ፤
*
"ነብይ በሀገሩ አይከበርም!"
*

በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደ እ.ኤ.አ አቆጣጠር 1978 ላይ
አንድ ያልተጠበቀ እንግዳ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ጉብኝት
ለማድረግ፤ "የተቀደሰች ምድር ናት" ብሎ ወደሚያስባት ሀገር
ኢትዮጵያ በድንገት ተከሰተ።
...
ወቅቱ በአለም እጅግ ጥንታዊና የመጨረሻ የሚባለው፤ ኢትዮጵያን
ከ2000 ዓመት በላይ ያስተዳደረ ዘውዳዊ ስርዓት ተገርስሶ፥ ደርግ
ስልጣን ከጨበጠ ገና 4 አመት ስላልሞላው፤ በዚህ ቀውጢ ጊዜ
የትኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ወደ ሀገር መግባትም ሆነ መውጣት
የማይችልበት፤ የእርስ በርስ ጦርነት የፈነዳበት ቢሆንም፥ ይህ
እንግዳ ግን የይለፍ ቪዛ ተመቶለት በቦሌ በኩል ከተፍ ብሏል።
...
ይህ እንግዳ፤ ምዕራባዊያን ሶስተኛው አለም (Third world)
ብለው ከሚመድቧቸው ሀገሮች አንዷ በሆነችው የካሪቢያኗ
ጃማይካ፤ ሳንታአና ናይን ማይል ከተሰኘች ትንሽ መንደር ተወልዶ፣
የስካ፣ ሩትና ሮክ ስተዲይ (Ska, root and rock study)
የሚባሉ ምቶችን ቀይጦ፣ ሬጌ (Reggae) የተባለ አዲስ የሙዚቃ
ስልት ፈጥሮ፣ ስድስት የህይወት ዘመን አልበሞችን አሳትሞ፣
በሚያስተላልፋቸው ምሉዑ መልዕክት ያላቸው ሙዚቆቹ አለምን
የናጠ፤ በዚያ ጊዜ ያሳተመው Exodus አልበም፤ በRolling
stone Magazine Album of the century (ዘመናዊ ሙዚቃ
ከተጀመረ አንስቶ እስከዛሬው ዘመን የምዕተ-ዓመቱ አልበም)
የተባለለት፣ "one love" የተሰኘው ሙዚ ቃሉ በ BBC, Music
of the Millennium የሚል ማዕረግ ያገኘ፣ "አለምን አንድ
ማድረግ የቻለ ማንም ሰው የለም የሱ ሙዚቆች ግን
ችለዋል" (No body unite the world but his music
does) የተባለለት፣ በአሚሪካን ራዲዮ ሙዚቃው የተለቀቀ
የመጀመሪያው ጥቁር አርቲስት፣ የነፃነት ታጋይ፣ የሬጌ ንጉስ፣
የሙዚቃ ነብይ፣ የጭቁን ህዝቦች ድምፅ፣ ዝነኛው ሮበርት ናስታ
ማርሌ (ቦብ ማርሌ) ነው።
...
ቦብ ማርሌይ ከቦሌ ኤርፓርት እንደወረደ በቀጥታ ወደተዘጋጀለት
ማረፊያ ጊዮን ሆቴል አመራ። በጊዮን ሆቴል ስዊሚንግ ፑሉ ራሱን
በሚያፍታታበት ሰአት ከሆቴሉ ባንድ የራሱ ሙዚቃ የሆነውን “No
woman, No cry” የተሰኘውን ዘፈን አንድ የሀበሻ አርቲስት
ሲጫወተው ከጆሮው ገባ፥ ማርሌ ከመዋኛው ገንዳ ወጥቶ ወደ
ባንዱ አመራ፤ የማርሌን ሙዚቃ አሳምሮ ሲጫወተው የነበረው
አርቲስት ሙሉቀን መለሠ በሪዳ ኢብራሂም ታጅቦ ነበር።
...
ማርሌ ከገንዳ ወጥቶ ወደ ባንዱ አምርቶ፥ እንደ ተራ ታዳሚ
የራሱን ሙዚቃ እያጣጣመ ሲመሰጥ ማንም ልብ ያለው
አልነበረም።
የሬጌው ንጉስ ወደ ባንዱ በማምራት ሙዚቃ ለመጫወት የባንዱን
ፍቃድ ጠየቀ፤ ተፈቀደለት። በወቅቱ አለምን የነጣውን "Get up
stand up" የተሰኘ የምንግዜም የነፃነት ሙዚቃውን ሲጫወት፤
አንድ አሳዛኝ ክስተት ተፈጠረ።
...
በቅርቡ አለም ያፈራቸውን (ፀሀዮ) የሚባሉትን ንጉስ (ቀኋሥ)
ከስልጣን ወርደው፤ በታሪካዊቷ ቮልስ ዋገን ተሳፍረው ሲጓዙ "ሌባ
ሌባ" ብሎ የጮኸ የወቅቱ መንጋ ቦብ ማርሌን "ውረድ ውረድ"
አሉት።
ማርሌ ግን እንደ ጃንሆይ የመንጋውን ጩኸት "ታዲያ ምን ያድርጉ
ንጉሳቸውን በጠራራ ፀሀይ ስትሰርቁባቸው" አይነት ንግግር፥
ለትንግርት በመናገር አላስቀየሰም። ሙዚቃው እንዳልገባቸው፣
እንዲህ ያለውን ረቂቅ ሙዚቃ ለማጣጣም እንዳልበቁ፤
ከጩኸታቸው ተረድቶ ወይም አዝኖ አልያ "ነብይ በሀገሩ
አይከብርም!" ብሎ የሬጌው ንጉስ ከሀበሻ መድረክ "ውረድ ውረድ"
ተብሎ ወረደ። ፍፁም የሚወዳት ቅድስት ነች የሚላት ሀገር
ህዝቦች "ውረድ ውረድ" ሲሉት ምን ተሰምቶት ይሆን?
...
ነብዮ (የሙዚቃ) እንግዳ ሲዘፍን ዓለም አቀፍ አርቲስት ቦብ
ማርሌይ እንደሆነ በድምፁ ያወቁት በዚያን ወቅት በጊዮን ሆቴል
ክለብ ውስጥ ሲጫወቱ የነበሩት የወርቃማው ዘመን አርቲስቶች
ሙሉቀን መለሠ፣ ኩኩ ሰብስቤ፣ ሪዳ ኢብራሂም፣ አበራ ፈይሣ፣
ዳዊት ካሣ፣ ጥላዬ ገብሬ፣ ሽመልስ በየነና ተስፋዬ ተሠማ ነበሩ።
...
ይህን አጋጣሚ ኩኩ ሰብስቤ የህይወቴ ትልቁ ቀን ባብ ማርሌ
ጊዎን ሆቴል ሲዘፍን ያየሁበት ቀን ነው ብላ ገልፃዋለች።
...
በወቅቱም ቦብ ማርሌይ የሙሉቀን መለሠ የሙዚቃ ችሎታ
አድንቆ ‹‹ሻሸመኔ›› የተሰኘ አልበም ለመሥራት ተስማምተው፤
ማርሌይ ለሙሉቀን ግጥሞች ሠጥቶት ወደ ሻሸመኔ ሄደ፡፡
ሙልቀን መለሰ ደግሞ ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ ወደ ተግባር
ሳይለውጠው እየሱስን ተቀብሎ የንብ አውራ የዋጠ ጉሮሮውን
ሰቀለ።
...
ባብ ማርሌ በኢትዮጵያ ቆይታው ሻሸመኔን እና ወንዶገነትን የጎበኘ
ሲሆን በወንዶ ገነት ቆይታው ታሪካዊውን ዙምባቡዌ የተሰኘ
ሙዚቃውን ግጥም እንደፃፈ የግለታሪኩ ፀሀፊወች መዝግበዋል።
ማርሌ ከወቅቱ ሁኔታ አንፃር በኢትዮጵያ ብዙ ባይቆይም ይህን
ስሜቱን በሙዚቃው “I know a place where we can carry
on…” በማለት ገልፆታል።
...
በሙዚቃ ስራወቹ የዘመኑ ልጥጥ የነበረው ባብ ማርሌ፤ እንደ
ሌሎቹ ሳይቀናጣ በአለባበስ እንኳን ጥቁር አፍሪካኖች በባሪያ
ንግድ ወቅት ነጮች በጀምላ የሚያለብሶቸውን ሰማያዊ ካኪ
ጨርቅ (slaves dressing) በማድረግ ጥቁር ጭቁኖችን
የሚዘክረው፤ የአባቱ ወገኖች የሆኑ ራሰ በራ እንግሊዛዊያን ሊቀ
ሰይጣኖች ስለሆኑ ከአፍሪካ ምድር ጠራርጋችሁ አውጧቸው
በማለት የሚያቀነቅነው፣ የምንግዜም የነፃነት ታጋይ ቦብ ማርሌ
በCIA ኤጀንት አማካኝነት በላብራቶሪ የተፈጠረ የካንሰር ቫይረስ
የእግር አውራ ጣቱ ላይ ተወግቶ፤ ካንሰሩ ወደ ሰውነቱ ሳይዛመት
የቀኝ እግሩን እንዲቆረጥ ቢጠየቅም (የሰው አካል ሙሉ ሆኖ
እንደተፈጠረ ሙሉ ሆኖ ማለፍ አለበት ሰው በፍቃዱ አካሉን
ሊያጎል አይገባም) የሚለውን የብልዮ ቅዱስ መፀሀፍ አንስቶ
በመሞገት አልቆረጥም ብሎ ተቃውሞ፤ ካንሰሩ ወደ አይምሮው
ተዛምቶ በተወለደ በ36 አመቱ ፤ "ገንዘብ ህይወት ሊገዛ
አይችልም" Money can't buy a life tell Ziggy um fine"
የሚል የመጨረሻ ቃል ተናግሮ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
ሙዚቆቹ ግን ህያው ሁነው ይኖራሉ።
...
የማርሌ ሙዚቆች ተፅህኖ እና ዘመን አይሽሬ ተወዳጅነትን
ያጠናው BBC Music research በአለም ዙሪያ በ24 ሰአት
ውስጥ የቦብ ማርሌ ድምፅ ሳይሰማ የሚውለው (የሚቋረጠው)
ለ4 ሰከንዶች ብቻ በመሆኑ የምንግዜም ተደማጭ አርቲስት
መሆኑን አረጋግጦለታል።
...
ማርሌ ነብሱ ከስጋው ከመለየቷ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማካኝነት በተደረገ
ስነ ስርዓት፤ ሀይማኖቱን ከራስ ተፈርያን ወደ ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ
ቀይሮ፤ ብርሃነመስቀል በሚል የክርስትና ስም
ተጠምቆ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግብዓተ መሬቱ እንዲፈፀም ተናዞ፤
የህይወት ዘመን ስራወቹን ለኛ ጥሎልን ነብሱን ይዞ አልፏል።
...
Note ለኢትዮጵያ ወደር የለለው ፍቅር አለው የሚባለው ባብ
ማርሌ፤ ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ካስተዋወቁ እና
ታሪካቸው ሲነሳ አብራ እንድትነሳ ካደረጉት ሰወች መሀል፥
የግንባር ቀደምቱን ስፍራ ሀይለ ስላሴ እና አበበ ቢቂላን
በማስከተል እንደሚቀመጥ በርካቶቹ ይስማማሉ።
***
ምንጭ
The life of Bob Marley - Rita Marley
The life, Legend and Legacy of the King of reggae,
Musical Prophet and freedom fighter Bob Marley,
Biography.
Our Africa