Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
n Heritage Megazin article about Bob
Marley In Ethiopia.
ድምፃዊ ዘለቀ ገሰሰ፣ የተለያዮ ሙዚቀኞች ማናጀር አዲስ ገሰሰ፣
ሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ የሙዚቀኛው ተሾመ ምትኩ
ወንድም እና ኩኩ ሰብስቤ የባብ ማርሌን የኢትዮጵያ ቆይታ
አስመልክቶ ከተናገሩት፤
የሬጌውን ንጉስ የኢትዮጵያን ወዳጅ ቦብ ማርሌ ነብስ ይማር!
መልካም ሳምንት
#ቴዎሥ
Tewodros


Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ሐይለየሱስ_ግርማ #በይ_ሠላም_ይሁንልሽ
በይ ሠላም ይሁንልሽ አማን
በሄድሽበት ሁሉ ተማም
አትባቢ ጨክኝ አይዞሽ
ግድ ሆኖ ላይቀር መሄድሽ /2x
ይልቁን እጄን ያዢና
ቃል ይኑር በኛ ሚፀና
ይልቁን እጄን ያዢና
ቃል ይኑር በኛ ሚፀና
መድመቂየዬ አልማዜ ነሽ
ማተብ ክታነብ ያንገቴ
ማስታወሻ የምትሆኚኝ
ላየኝ ሰው ምልክቴ
ለሚያየኝ ምልክቴ
ለጠፋብኝ ግዜ ሚዛን
ትዝታሽ አያረጅም
የተናደው በኔ ናፍቆት
አንቺም ከኔ ወዲያ አትወጂም
ከኔ በቀር አትለምጂም
ኦ ኦ ኦ ዎ ዎ የይ
ይልቅ በርቺ እና አይዞህ በይና
እንገናኝ እንደገና
ይልቅ በርቺ እና አይዞህ በይና
በይ ተነሺ ጨክኚና
በይ ሠላም ሄሁንልሽ አማን
በኔድሽበት ሁሉ ተማም
አትባቢ ጨክኝ አይዞሽ
ግድ ሆኖ ላይቀር መሄድሽ
ይልቁን እጄን ያዢና
ቃል ይኑር በኛ ሚፀና
በቅፊ ዘልቀው ገብተው
ያነቡት አይኖችሽ
በፅናት ያቆዩኛል መልሼ እስካይሽ
ደግሜ እስካገኝሽ
እንግዲያው እየሳምኩኝ አላባባው ሆድሽን
የመሄጃሽ ሰአት ቀርቧል ነይ ቻይው ስለይሽ
ኦ ኦ ዎ ዎ የይ
ይልቅ በርቺ እና አይዞህ በይና
እንገናኝ እንደገና
ይልቅ በርቺ እና አይዞህ በይና
በይ ተነሺ ጨክኚና

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጎሳዬ_ተስፋዬ #የኔ_ማር_ወለላ
ማረፍያ ጌጥ ማጣቱን
ማን በነገረሽ ዓይኔ
ባንችው ናፍቆት ስብሰለሰል
ታምሚያለሁ ስሚኝ እኔ
ድምፅሽ ሲርቅ ከጆሮዬ
መጠውለጉን ባየሽልኝ
ያገራገር ሰውነቴ
እየራበኝ ሳቅ ጫወታ
አስጨነቀኝ በዝምታ
አንቺን የለመደው ቤቴ
ጠረንሽ ሁሌም አለ ከገላየጋራ ....
በሌላ ላለውጥሽ ምያለሁ እና እቱ
ካለሽበት ሰማይ ማልዶ
ባሳብ ስዋኝ ልቤ ነዶ
ስንከራተት አንቺን ወዶ
ዓይንሽን ላይ ጓጉቻለሁ
ደጀ ሰላም ውዬ አድራለሁ
ቀን ከለሊት አስባለሁ
የኔ ማር ወለላ
አልመኝም ካንቺ ሌላ
እፁብ ልጅ ነሽ አንቺ
መቼም የማትሰለቺ /2x

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#እዮብ_መኮንን #ወደ_እናቴ_ቤት_እመለሳለሁ
እንደው ሙሉ ሆኜ ተፈጥሬ
በቀቢፀ ተስፋ ታጥሬ
ያጣዉ የሌለኝ ደርሶ ቢመስለኝ
አወይ እግሬ /2x
ወስዶ አወጣኝ ከሀገሬ
ንፁህ ፍቅር እምነት ሰላም ሳይጠፋ
ነገን የሚያኖር ተስፋ
ሁሉ ሞልቶ ሳለ ከሀገር መንደሬ
ስስት ከማታውቅ ምድሬ
ልቤ እሩቅ ተመኘ በሰማዉ ተረቶ
ንቆ የራሱን ትቶ
ያሉት ከንቱ ቢያየው ቀርቦ ቢረዳ
ሆነበት የህሊና እዳ ኡሁ
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለሁ
ወደ እናቴ ቤት በቃ እሄዳለሁ
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለሁ
ከአእዋፍ አፍ ወድቆ ተዘርቶ አብቦ
ሳያለፋ መብላት ጠግቦ
ሰፊ ውድ እርስቱን የአምላኩን ፀጋ
ክብሩን ነስቶት ዋጋ
ስደት ባዶ ቅዠት ወስዶኝ ከሃገሬ
ብስሉ ሊሆን ጥሬ
ለካስአያምርብኝ ደስታም ሃዘኔ
ያለሃገር ስኖር እ
ወደ እናቴ ቤት እመለሳለሁ
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለው
ወደ እናቴ ቤት በቃ እሄዳለው
ከሞቀ እቅፋ ልኑር ብያለው

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ሄለን_በርሄ #ልቤ_ላንተ_እንጂ
ልቤ ላንተ እንጂ ለሌላው የለው ቦታ
ያልከፈለህ ገና አለ ውለታ
እኔ አንድዬን ምለምነው
ላንተ ሰላም ጤና ነው ምማፀነው
ገና በማለዳው ፈክታ
አ ሀ ሀ
ሳለች ጀምበር
ኦ ሆነ ሆነ
ጨላልሞበት አይኔ ለማየት ሲቸገር
ከልብህ አብርቶ የፍቅር ፀሐዩ
ሳልታይ አየኸኝ ልቤ ፍቅሬ ሆይ
ኖሮኝ ባላደርግልህ ዛሬም ባላኮራህ
ለኔ በቂዬ ነው መኖርህ በጤናህ
እኔ ምፈልገው ይሄን ነው /፬
ከፍቶህ አይኔ እንዳያይ ብዬ ነው /፬
ልቤ ላንተ እንጂ ለሌላው የለው ቦታ
ያልከፈለህ ገና አለ ውለታ
እኔ አንድዬን ሰለምነው
ላንተ ሰላም ጤና ነው ምማፀነው
ያንተን መልካምነት በቃላት ዘርዝሬ
መመለስ አልችልም ባፌ ተናግሬ
ውለታህን ቆጥሮ የሰማይ ንጉሱ
እኔ አቅም የለኝም ይክፈልልኝ እሱ
ኖሮኝ ባላደርግልህ ዛሬም ባላኮራህ
ለኔ በቂዬ ነው መኖርህ በጤናህ
እኔ ምፈልገው ይሄን ነው /፬
ከፍቶህ አይኔ እንዳያይ ብዬ ነው /፬

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አብዱ_ኪያር #እድሜ_ዳኛው
ክፉና ደጉን ሳናውቅ በልጅነት ህይወት
ኩልትፍትፍ ባለ አንደበት መፈንደቅ መጫወት
ግጥማችን ቤት አይመታ ስርዐቱንም አናውቀው
በጭብጨባ ነበረ ሰፈሩን ምናደምቀው
ተረሳሽ ወይ እስቲ ላስታውስሽ
እቅፍ ኣድርጌ የማጫውትሽ
እኔና አንቺን ያጣመረን
ዘፈን ነበር ያፋቀረን
አደግንና ተቀየረ
መፍራት ማፈር ተጀመረ
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
ፍቅርሽ በልጅነት ያኔ ተጀምሮ
እያሰቃየኝ ነው አድጎና ጨምሮ
የልቤን ገልጬ መናገር ጨንቆኛል
እድሜ ግልጽነቴን ከላዬ ነጥቆኛል
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
ከ ሀ ግዕዝ ለ ግዕዝ በፊት ኣሊፍ ባ ታ ሳንል
ዘፈን ነበር የምናውቀው ሳናጠና ፊደል
መቼም ከልቤ አይጠፋም ያ ምንወደው ጭፈራ
ጮክ ብለን የምንዘፍነው በነጻነት ሳንፈራ
ተረሳሽ ወይ እስቲ ላስታውስሽ
እቅፍ ኣድርጌ የማጫውትሽ
እኔና አንቺን ያጣመረን
ዘፈን ነበር ያፋቀረን
አደግንና ተቀየረ
መፍራት ማፈር ተጀመረ
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
አቅፌ ልስምሽ ልቤ ይከጅልና
እንዴት ብዬ ላርገው ሆነብኝ ፈተና
ገና አይንሽን ሳየው እጨናነቃለሁ
እድሜ ነጻነቴን ወስዶት እፈራለሁ
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
የተሰማንን ዘፍነን በየዋህነት የኖርነው
ድሮ ልብ ሳንገዛ በልጅነት እድሜ ነው
ግልጽነት እና እውነት ስሜታችን ላይ ነበር
ልብ ስንገዛ ጠፋ አቤት የግዢ ነገር
የላይኛው ፍቅር ሰጠን
ነጻነትን አለበሰን
የምድሩ የታችኛው
ፈረደብን እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
አንቺንም እንደኔ ያደርግሻል ወይ
የልብን መናገር ያስፈራሻል ወይ
ስሜቴ በሙሉ አፍቅራት ይለኛል
ውድድ ውድድ አርጋት አትተዋት ይለኛል
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው




Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ብስራት_ጋረደው #ሳላያት_ውዬ_አላድር
አያስቀረኝ ምሽት ፅልመት
እሄዳለሁ ላያት ካለችበት
ባይገታኝ አራዊቱ
ጀግና አርጎኛል ፍቅሯ ልበ ብርቱ
አልፈራሁም አላመነታ
ዓይኗን ካላየሁ የለኝም ፋታ
የሚመጣውን በውድቅት
በፍቅር አምላክ ከገዘትኩት
እሄዳለሁ አይነጋም ሌቱ
ፍቅሯ አክንፎኛል ያው ባለ መብቱ
ፋታ ነስቶኝ ፀንቶ መናፈቅ
አልጠብቅ ጀንበር እስክትፈነጥቅ
በነጎድጓድ ቢያወርደው ሰማይ ዶፉን
ማየት አይሳነውም ዐይኔም ውዱን
ተጋፍጬ አልፌ ሁሉንም ነገር
ያለ ጥርጥር ሳላያት ውዬ አላድር
ተላልፌ አራዊቱንም
ወስኛለሁ አልቀር አሁንም
አልፈራም የሌት አጋንንቱንም
ቢበረታ ቢያይል መውገድ
እሄዳለሁ ላያት ያችን የኔ ውድ
እኔን ፅልመት መቼ ይገርመኛል
አውቃለሁ ሁሉን ፍቅር ይክሰኛል
በነጎድጓድ ቢያወርደው ሰማይ ዶፉን
ማየት አይሳነው ዓይኔም ውድን
ተጋፍጬ አልፌ ሁሉንም ነገር
ያለ ጥርጥር ያለ ጥርጥር
ሳላያት ውዬ አላድር

Shear to your best friend for more lyrics@ethiopian_music_lyrics
#ሀይማኖት_ግርማ #እሽሩሩ_ማለቴ
ውሸታሙ አፍህ በማር ተቀብቶ
እወድሻለሁ ስላልክ ልቤ ተመክቶ
ለእውነተኛ ፍቅር ነበረ ምኞቴ
ሳይገባ የቀረ ያ መንከራተቴ
እኔ እኔ ምን ላውራ ምን ልበል
የፍቅር አምላክ የእጅን ይስጥህ /2x
እሹሩሩ እሽሩሩ እሽሩሩ ማለቴ
ምክንያት ይሆን ወይ አንተን ለማጣቴ /2x
የረገጥከውና ፍቅርን የገፋህው
አንተ አይደለህም ወይ ውሉን ያፈረስከው
በእውነተኛ ፍቅር ቀለድክ እንደልብህ
የመዋደድ አምላክ የስራህን ይስጥህ
ካንቺ ሳይሆን ከራሱ መቷል
በቃኝ ብሎ መሔድን መርጧል
አንቺ ሁሌም ተፈላጊ ነሽ
የት ይደርሳል አረ እሱ ቢሸሽ
እንዲህ እኮ ነው የፍቅር አባዜ
ይለቅሻል በራሱ ጊዜ
እንቢ ብሎ ለሄደ ማስረሻ
ይሰጥሻል ጥሩ መካሻ
እኔ እኔ ምን ላውራ ምን ልበል
የፍቅር አምላክ የእጅን ይስጥህ /2x
እሹሩሩ እሽሩሩ እሽሩሩ ማለቴ
ምክንያት ይሆን ወይ አንተን ለማጣቴ /2x

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ፀሐዬ_ዮሐንስ #ፍንጭቷ
ፍንጭቷ ነው ምልክቷ
ለስላሳ ነው ሰውነቷ
ሸብ ረብ አካሄዷ
ያዝ ያዝ ነው መውደዷ
ወጋ ነቀል አመለካከቷ
ከውብም ውብ ሸጋዬ የእሷስ አከላቷ
ሆድዬ- በለስላሳው አየር እንደመህር ሰብል
ሆድዬ- ንፋስ እየገራው ጸጉሯ ሲዘናፈል
ሆድዬ- ከፏፏቴው ግርጌ በተዋበው ስፍራ
ሆድዬ- ላያት ትመስላለች የጥኋት ፀሐይ ጮራ
ፍንጭቷ ነው ምልክቷ
ለስላሳ ነው ሰውነቷ
ሸብ ረብ አካሄዷ
ያዝ ያዝ ነው መውደዷ
ወጋ ነቀል አመለካከቷ
ከውብም ውብ ሸጋዬ የእሷስ አከላቷ
ሆድዬ- ከዚያ ከላይ አምባ ጎጆዋ ተሰርታ
ሆድዬ- አይን ከሚማርክ ፀጥ ካለው ቦታ
ሆድዬ- ያቺ የኔ ሸጋ ልብን የምትረታ
ሆድዬ- የምትናፈቅ ናት ጥዋት ታይታ ለማታ
ፍንጭቷ ነው ምልክቷ
ለስላሳ ነው ሰውነቷ
ሸብ ረብ አካሄዷ
ያዝ ያዝ ነው መውደዷ
ወጋ ነቀል አመለካከቷ
ከውብም ውብ ሸጋዬ የእሷስ አከላቷ
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ #ጠንበለል
ጥርት እንደ ሰማይ ልቅም እንደ ስንዴ
አጀብ የደም ግባት እንዲህም አለ እንዴ
አልሻም ብር አምባር ጉትቻ ቀለበት
የኔ ጌጥ እሱ ነው የውበቴ ውበት
ዛላው ዘለግ ያለ የባህር ማሽላ
ልቤን እንክት አርጎ በፍቅር የበላ
እሱንም ስወደው ልቡን በጣም ሰምነው
በክፉ እሚያነሣው እንዴት ያለ ሰው ነው
መላ ሆዴ ቀጭን ኩታ ለብሶ
መጣ እየጋለበ ኮርኩሮ ፈረሱን
ያውና ከማዶ መጣሲንጎማለል
አካል ሸሞንሟና ዘንካታ ጠንበለል
አሀ ጠንበለል አ…. ጠንበለል
አሀ ጠንበለል አሀሀሀ ጠንበለል
አይናማ ነው ሎጋ አየሁት ተናዞ
ልቤን ከልቡ ጋር አነባብሮ ይዞ
ቀለብ አይሆነውም አልሰጥም አንጀቴን
ያውለት እንጀራ የወዳጅነቴን
የትውልድ አገሩ እሱን የበቀለ
ሌላ አላፈራም ወይ እየቀላቀለ
ልበ ኩሩ ነበርኩ አንጀተ ደንዳና
እንስፍስፍ አልኩ እንጂ እሱን ወደድኩና
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጎሳዬ_ተስፋዬ #እናትዬ
አንቺ አጋዥ ሆነሺኝ ለህይወቴ
ውለታሸን በምን ልካስ አቴ
የምስጋና ቃላት ስላነሰኝ
ብዬ ልጥራሽ አንቺን እናቴ
በቁልምጫ ማን ልበልሽ እኔ
የኔ አለኝታ እህህ መከታዬ
ደስ እንዲለኝ በምን ልጥራሽ እኔ
እንደ ወላጅ ጠባቂዬ
ወሰንኩኝ ልጠራሽ ብዬ አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
በቁልምጫ ማን ልበልሽ እኔ የኔ አለኝታ እህህ መከታዬ
ደስ እንዲለኝ በምን ልጥራሽ እኔ...
እንደ ወላጅ ጠባቂዬ
ወሰንኩኝ ልጠራሽ ብዬ አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
እስከማውቀው ድረስ ከኔ ሳትጠብቅ
በፍቅር በፅናት በፍቅር በፅናት
የሷን ኑሮ ትታ ሰለኔ የኖረች እናቴ ብቻ ናት
እስኪደንቀኝ ድረስ በሚገርም ሁኔታ
ለፈፀምሽው ስራ ለፈፀምሽው ስራ
ታዲያ ምን ያንስሻል እናትዬ ብዬ
በፍቅር ብጠራሽ
የናቴ ምትክ ፍቅር መኩሪያዬ
የነፍሴ ፀዳል እምነት ኑሮዬ
ምን ያግደኛል ብጠራሽም ኡኡ ብዬ አይ ብዬ
እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ... እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
እናትዬ
በቁልምጫ ማን ልበልሽ እኔ
የኔ አለኝታ እህህ.... መከታዬ
ደስ እንዲለኝ በምን ልጥራሽ እኔ...
እንደ ወላጅ ጠባቂዬ
ወሰንኩኝ ልጠራሽ ብዬ አይ ብዬ
እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
በቁልምጫ ማን ልበልሽ እኔ
የኔ አለኝታ እህህ.... መከታዬ
ደስ እንዲለኝ በምን ልጥራሽ እኔ
እንደ ወላጅ ጠባቂዬ
ወሰንኩኝ ልጠራሽ ብዬ አይ ብዬ
እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
ብናገር አላፍርም ያንቺን ታላቅነት
ያንቺን ልዩ ፍቅር ያንቺን ልዩ ክብር
ሁለት እናት አለኝ እያልኩኝ ሁለቴ ልደቴን ባከብር
ማመን እሲኪያቅተኝ በፍቅርሽ ደግፈሽ
ለዚህ አብቅተሺኛል ለዚህ አድርሰሺኛል
ከናቴ በማያንስ ተጨንቀሽ አምጠሽ ዳግም ወልደሽኛል
የናቴ ምትክ ፍቅር መኩሪያዬ
የነፍሴ ፀዳል እምነት ኑሮዬ
ምን ያግደኛል ብጠራሽ ኡኡ ብዬ አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ... እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ... እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ
አይ ብዬ እናትዬ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics