Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ፀሐዬ_ዮሐንስ #ፍንጭቷ
ፍንጭቷ ነው ምልክቷ
ለስላሳ ነው ሰውነቷ
ሸብ ረብ አካሄዷ
ያዝ ያዝ ነው መውደዷ
ወጋ ነቀል አመለካከቷ
ከውብም ውብ ሸጋዬ የእሷስ አከላቷ
ሆድዬ- በለስላሳው አየር እንደመህር ሰብል
ሆድዬ- ንፋስ እየገራው ጸጉሯ ሲዘናፈል
ሆድዬ- ከፏፏቴው ግርጌ በተዋበው ስፍራ
ሆድዬ- ላያት ትመስላለች የጥኋት ፀሐይ ጮራ
ፍንጭቷ ነው ምልክቷ
ለስላሳ ነው ሰውነቷ
ሸብ ረብ አካሄዷ
ያዝ ያዝ ነው መውደዷ
ወጋ ነቀል አመለካከቷ
ከውብም ውብ ሸጋዬ የእሷስ አከላቷ
ሆድዬ- ከዚያ ከላይ አምባ ጎጆዋ ተሰርታ
ሆድዬ- አይን ከሚማርክ ፀጥ ካለው ቦታ
ሆድዬ- ያቺ የኔ ሸጋ ልብን የምትረታ
ሆድዬ- የምትናፈቅ ናት ጥዋት ታይታ ለማታ
ፍንጭቷ ነው ምልክቷ
ለስላሳ ነው ሰውነቷ
ሸብ ረብ አካሄዷ
ያዝ ያዝ ነው መውደዷ
ወጋ ነቀል አመለካከቷ
ከውብም ውብ ሸጋዬ የእሷስ አከላቷ
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics