Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ለኢትዮጵያ ኩራት ፣ ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆነን አለምን እያገናኘን እነሆ ሰባ አምስት አመታት አስቆጠርን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ 75 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ስም በአለም ከፍ አድርጎ የሚያሰጠራ ወርቃማ ታሪክ ሀ ብሎ ተጀመረ። በ1946 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ በረራ ከአዲስ አበባ ተነሥቶ በአስመራ በኩል ካይሮ (ግብፅ) አረፈ። ዛሬ በዓለማችን ካሉ አንጋፋ አየር መንገዶች አንዱ ለመሆን የበቃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75ኛ አመቱን በማክበር ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለክቡራን ደንበኞቹና ለታታሪ ሰራተኞቹ እንኳን ለዚህ ታላቅ ቀን አደረሳቹ ይላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
እ.ኤ.አ በ 1946 ዓ.ም ወደ ግብፅ ካይሮ በረራ በማድረግ የተጀመረውን የ75 አመት የስኬት ጉዞ በማስመልከት በዛሬው ምሽት ከአዲስ አበባ ወደ ካይሮ የሚደረገው በረራችን ከመነሳቱ በፊት እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ አሸኛኘት ተደርጎለታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75ኛ አመት አከባበር በዋናው መስሪያ ቤት

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመዘገበዉ የመጀመሪያውና አየር መንገድን ለ 20 ዓመታት ያገለገለው ET-T-1 አውሮፕላን እና
አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ካሉት 16 ቅንጡ አውሮፕላኖች ውስጥ አንዱ የሆነው A350 አውሮፕላን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3.5 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ከቻይና ሻንግሃይ ከተማ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ብራዚል ሳኦ ፖሎ አጓጓዘ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ጭነት አገልግሎት እስካሁን ከ 20 ሚሊየን በላይ የኮቪድ -19 ክትባቶች ከ 20 በላይ ወደሚሆኑ ሀገራት አጓጉዟል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድን 75ኛ አመት አስመልክቶ የቦይንግ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ያስተላለፉት መልዕክት።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድን 75ኛ አመት አስመልክቶ የኤርባስ ንግድ ክፍል ዋና ሐላፊ ክርስቲያን ሺረር ያስተላለፉት መልዕክት።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
እንግዶችን በጥልቅ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እና በፈገግታ መቀበል በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ አብሮን የኖረ ልዩ ባህላችን ነው። እኛም ከዚህ ኢትዮጵያዊ ባህል ከተቀዳውና ጊዜው በሚጠይቀው ሙያዊ ክህሎት በዳበረው መስተንግዶአችን ዛሬም በክብር እናስተናግድዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በእርግጥም 75 ቁጥር ብቻ አይደለም። ታሪክም ጭምር ነው። ታላቅ ፓን አፍሪካዊ አየር መንገድ የተጠነሰሰበት እና የተቋቋመበት ታሪክ ! ለ75 አመታት በአሸናፊነት ከፍ ብለን የበረርንበት ታሪክ !
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እ.ኤ.አ ከ 1971 ዓ.ም ጀምሮ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
https://www.youtube.com/watch?v=S6UzArcl2A0 የኢትዮጵያ አየር መንገድን 75 ኛ አመት አስመልክቶ የ ጂ.ኢ አቪዬሽን ፕሬዝዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆን ስላተሪ ያስተላለፉት መልዕክት።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
https://www.youtube.com/watch?v=Lx_bKGWWwek የኢትዮጵያ አየር መንገድን 75ኛ አመት አስመልክቶ የፕራት እና ዊትኒ ካናዳ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ፕሬዝዳንት ማሪያ ዴላ ፖስታ ያስተላለፉት መልዕክት።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይናው ጉዋንግዶንግ ኤርፖርት እና በተመሳሳይ ከዚሁ ኤርፖርት ወደ ሌሎች የአለም ሀገራት እ.ኤ.አ በ 2020 ዓ.ም ባጓጓዘው የእቃ ጭነት ብዛት ከጉዋንግዶንግ ኤርፖርት ባለስልጣን የወርቅ ሽልማት ተቀዳጀ። ሽልማቱንም ኤርፖርቱ በደንበኞቹና በእቃ ጭነት ዙሪያ በጉዋንዡ ከተማ ባካሔደው ስብሰባ ላይ ተቀብሏል።
https://bit.ly/3u4AhZX
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
https://www.youtube.com/watch?v=alb7reLpNDc የኢትዮጵያ አየር መንገድን 75ኛ አመት አስመልክቶ የታሌሲ ኢንፊኒት ኤክስፕረስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፌሊፔ ካርቴ ያስተላለፉት መልዕክት።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
የልጅነት ህልምዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እውን ያድርጉ፡፡ #የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት
አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማገናኘት በትጋት እንሰራለን፡፡ #የኢትዮጵያአየርመንገድ #75የስኬትአመታት