Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
91.1K subscribers
3.87K photos
146 videos
2 files
416 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የአፍሪካ አየር መንገዶች ህብረት (AFRAA) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ስልጠና ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ። ለተጨማሪ መረጃ ማስፈንጠሪያውን (link) ተጭነው ይመልከቱ።
http://www.logupdateafrica.com/afraa-ethiopian-airlines...
Continuing what we do best, connecting Africa to the rest of the world. #FlyEthiopian #Connectingtheworld
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ፣ በሚያምር ኢትዮጵያዊ ፈገግታ በታጀበው መስተንግዶአችን ይደሰቱ።
መልካም ሳምንት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
1
የእያንዳንዱ ቀን ጅማሬ የአዲስ ጉዞ መነሻ ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
@abonthecliff ምስሉን ስላጋሩን, እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አህጉር የመሪነቱን ስፍራ የያዘው በሁለተኛነት ከሚከተለው አየር መንገድ እጥፍ አቅም በመያዝም ጭምር ነው። አየር መንገዱ እድገት ያስመዘገበበት ፍጥነት ሌሎች የአሕጉሪቱ ምርጥ 10 አየር መንገዶች ካስመዘገቡት አጠቃላይ የእድገት ፍጥነት የተሻለ ነው። የዚህ ስኬት ምክንያት ምንድነው? Simple Flying ትንታኔውን እንደሚከተለው አስነብቧል።
https://bit.ly/2OZzydc
በውጭ አገር ከሚገኙት የአየር መንገዱ ቢሮዎች አንዱ በየመን ኤደን በ1950 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ይህን ይመስል ነበር። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
እ.ኤ.አ ከ2011 እስከ 2019 ባሉት አመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ በጣም ፈጣን እድገት ያስመዘገበ ሲሆን ይህም ሌሎች አስር ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገዶች ካስመዘገቡት ድምር እድገት የላቀ ሆኖ ተመዝግቧል።
ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ ። https://bit.ly/2OZzydc
@Simpleflying
“The Engine Is The Heart Of An Airplane But The Pilot Is Its Soul.”
Walter Alexander Raleigh
#EthiopianAirlines #FlyEthiopian
Ethiopian offers you comfort and care on your journey to your dream destination. #EthiopianAirlines #FlyEthiopian
መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለውድ ደንበኞቻችን በበረራ ላይ እንዲሁም በእያንዳንዱ የጉዞ ክፍል ውስጥ የበለጠ የደንበኝነት ተሞክሮ ለመስጠት በትጋት እንሰራለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ልክ የዛሬ አመት የመጀመሪያውን በመንገደኛ አውሮፕላን መቀመጫዎች ላይ እቃዎችን በመጫን ማጓጓዝ የጀመርንበት እለት ነው። የመጀመሪያ በረራውንም ያደረግነው ከአዲስ አበባ ወደ ኪኒሻሳ ሲሆን ከ 16 ቶን በላይ የህክምና መርጃ ቁሳቁሶችን እና ሌሎች ጭነቶችን አጓጉዘናል።

የኮሮና ቫይረስ የፈጠረውን ቀውስ ለመቋቋም በአጭር ግዜ ውስጥ ስልታችንን በፍጥነት በመቀየር የመንገደኞች አውሮፕላኖቻችንን ለእቃ ጭነት በመጠቀም በተለይም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደተለያዩ ሀገራት አጓጉዘናል። ይህም ፈጣን ውሳኔ አየር መንገዳችን ከጥቂት ፈር ቀዳጅ አየር መንገዶች አንዱ እንዲንሆን ያደረገ ሲሆን አየር መንገዳችንም በስኬታማነቱ እንዲቀጥል አስችሎታል።
ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-marks-one-year-since-the-first-preighter-operation-on-passenger-aircraft
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“ባልተጠበቀ ሁኔታ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያስከተለውን ቀውስ ለመቋቋም የመንገደኛ አውሮፕላኖቻችንን ለእቃ ጭነት አገልግሎት መጠቀም ከጀመርን እነሆ አንድ አመት ሆነን።
የመጀመሪያውም በረራ የተደረገው የዛሬ አመት ሲሆን በረራውም አየር መንገዳችን እስከአሁን የኮሮና ቫይረስ ያስከተለውን ቀውስ እንዲወጣ አስችሎታል ። ኮቪድ-19 ከተከሰተ ጀምሮ ደንበኞቻችንን እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ወቅትም ጭምር ማገልገል በመቻላችን ትልቅ ክብር ይሰማናል።
የአየር መንገዳችን የካርጎ እና የሎጀስቲክስ ክፍልም የኮቪድ መከላከያ ግብአቶችንና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በማጓጓዝ ወረርሽኙን ለመግታት በሚደረገው አለም አቀፍ ጥረት ላይ እጅግ የላቀ ሚና ተጫውቷል።”
አቶ ተወልደ ገብረማርያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ
የመንገደኛ አውሮፕላኖቻችንን የእቃ ጭነት አገልግሎት ላይ ማዋል ከጀመርንበት የዛሬ አመት ጀምሮ 5,645 የእቃ ጭነት በረራዎችን በማድረግ ከ 121,750 ቶን በላይ የካርጎ ጭነት በአለም አቀፍ ደረጃ አጓጉዘናል። እነዚህ በመንገደኛ አውሮፕላኖቻችን የተደረጉ የካርጎ ጭነት በረራዎች በመደበኛ የእቃ ጭነት አውሮፕላኖቻችን እ.ኤ.አ ከ ማርች 25, 2020 እስከ ማርች 25,2021 በ33,182 አጠቃላይ በረራዎች ባጓጓዝነው 735,869 ቶን ጭነት ላይ እጅግ በጣም ትልቅ አስተዋፅዖ ነበረው።
ከመንገደኛ ወደ እቃ ጭነት የተቀየረ B737-800 አውሮፕላን GA Telesis ከተባለ የአቪየሽን ድርጅት ተረክበናል። አውሮፕላኑም የካርጎ አገልግሎታችንን በማጎልበት ወደ ተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ጨምሮ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ ያግዘናል ይህም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እየሰጠን ያለነውን የእቃ ጭነት አገልግሎት አቅም ያሳድጋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) ጋር በመተባበር "Travel Pass" የተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ጥቅም ላይ ማዋል ጀመረ።
አገልግሎቱ መንገደኞች ከበረራ በፊት የሚያቀርቡትን ከኮቪድ ጋ ተያያዥ የሆኑ የጤና ማስረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሲሆን ለመንገደኞች የጤና ደህንነት መጠበቅም ትልቅ እገዛ የሚያደርግ ነው።
1
ለጤናዎ መጠበቅ ለሚደረጉ ቅድመ ጥንቃቄዎች ሁሉ ቅድሚያ በመስጠት በኢትዮጵያዊ መስተንግዶ አስደስተን ወዳሰቡት ስፍራ እናደርስዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ