በተለያዩ ክብረ በዓላት ሳምንቱን ሙሉ የተከበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰራተኞች ቀን በዛሬው ዕለት 18 ሺ የአየር መንገዱ ሠራተኞች በተጋበዙበት እንዲሁም የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ እንዲሁም የቦርድ አባላት፣ የአየርመንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ እንዲሁም ሌሎች የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በታደሙበት ታላቅ ስነ ስርአት ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ በተሠራው የአየር መንገዱ የእግር ኳስ ሜዳ ተከብሮ ውሏል።
በዝግጅቱ ላይ ከአየር መንገዱ የተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሰራተኞች ከዋና ስራ አስፈፃሚው እና ከየክፍሎቻቸው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። በዛሬው
ዕለት የተከናወነው ክብረ በዓል ለአንድ ሳምንት የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች ቀን ክብረ በዓል የመዝጊያ ዝግጅት ሲሆን በሰራተኞች ዘንድ ያለውን ቅርርብ የሚያሳድግ ነው። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #የሰራተኞችቀን2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኪጋሊ ሩዋንዳ በረራ የጀመረበትን 50ኛ ዓመት በደማቅ ስነ-ስርአት አከበረ። እ.ኤ.አ1975 ዓ.ም ወደ ኪጋሊ ሩዋንዳ በረራ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ አገልግሎታችንን በማሳደግ በአሁኑ ወቅት በሳምንት 21 የመንገደኛ እና 3 የካርጎ በረራዎችን ወደ ከተማዋ በማድረግ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን።
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ:: https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-celebrates-50-years-of-service-to-kigali-rwanda
#የኢትዮጵያአየርመንገድ