Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.75K photos
141 videos
2 files
411 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ወደ መዳረሻዎ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ታጅበው ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀርመን ሀምቡርግ በተካሄዱ ሁለት መርሃግብሮች “በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ” ሽልማት እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች “Cabin Concept of the Year 2025” ሽልማት መቀዳጀቱን ስናበስር በደስታ ነው። እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያጎናፀፉና በዓለም ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያጠናክሩ ናቸው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-wins-prestigious-titles-at-two-award-events-in-hamburg-germany
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የመስኮትምልከታ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታዊው የኢትዮጵያ ፕሮግራማችን በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ነው። ይከታተሉን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ይመኛል። መልካም በዓል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የማዕድ ማጋራት መርሀግብር አካሄደ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ኢቲ ፋውንዴሽን” በተሰኘው የስራ ክፍሉ አማካኝነት ማህበራዊ ሀላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል በዚህ ማዕከል በቋሚነት በየዕለቱ የሚያደርገው የምገባ መርሀግብር ይገኝበታል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄርያዋ ሌጎስ ከተማ እያደረገ ያለውን 7 ሳምንታዊ በረራ ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ 14 ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ ለደንበኞቹ ይበልጥ ምቹ የበረራ አማራጭ መስጠት የሚጀምር መሆኑን በደስታ ያበስራል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡዳቢ ከተማ በሚያደርገው የመጀመሪያ በረራ ላይ ከ904 ዶላር ጀምሮ ለሶስት ምሽቶች እና አራት ቀናት የሚቆይ ልዩ የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቷል:: በዚህ ልዩ ቅናሽ አሁኑኑ ተጠቃሚ ይሁኑ።ለተጨማሪ መረጃ ድረ ገፃችንን ETHolidays@ethiopianairlines.com ይጎብኙ፤ አልያም በስልክ ቁጥሮቻችን 0115174203/4204/4207 ይደውሉ።
ደንብና እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አቡዳቢ
ምቹ እና አስደሳች በረራ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ