Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.8K subscribers
3.87K photos
146 videos
2 files
416 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ላለፉት በርካታ ዓመታት በታታሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው በጡረታ ለተሰናበቱ እና አየር መንገዱን ለ20፣ 25፣ 30፣ 35 እና 40 ዓመታት እያገለገሉ ለሚገኙ በአጠቃላይ 384 ሠራተኞች ዕውቅና የመስጠት መርሀ ግብር ተካሔደ።

በእውቅና አሰጣጥ መርሀግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ሰራተኞች፣ የሰራተኞች ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ላበረከቱት የረጅም ዓመት አገልግሎት ዕውቅና ከተሰጣቸው መካከል በአየር መንገዱ የተለያዩ ሀገራት ቅርንጫፎች ያገለገሉ የውጪ ሀገራት ዜጎች የሚገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተመሳሳይ የዕውቅና እና የማበረታቻ መርሀግብር በየዓመቱ ያደርጋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍279👏5