በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ አህጉራዊ ትስስርን በማጠናከር እንዲሁም በሀገራት መሪዎች ዘንድ ተመራጭ በመሆን ፋና ወጊ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ፓን-አፍሪካዊ ታሪክ በማስቀጠል በዛሬው ዕለት የብሩንዲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ክቡር ፕሮስፐር ባዞምባንዛ በዓለም አቀፍ በረራዎቹ እንዲሁም በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቪ.አይ.ፒ ተርሚናል በክብር በማስተናገዱ ኩራት ይሰማዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
የአፍሪካ ኩራት የሆነው አየር መንገዳችን በዛሬው ዕለት የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሆኑትን ክቡር ፋዎስቲን አርቼንጅ ቱዋዴራ (Faustin-Archange Touadéra) በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቪ.አይ.ፒ ተርሚናል በክብር ተቀብለን ስላስተናገድናቸው ታላቅ ኩራት ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
በቀደሙት ግዜያት ስንከተለው የነበረው “አፍሪካውያንን እርስ በርስ ማስተሳሰር” የተሰኘው መርሀችን ዛሬም በድምቀት ቀጥሎ ለ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በአፍሪካዋ መዲና አዲስ አበባ የተገኙ 20 የአፍሪካ አገራት መሪዎችን በግዙፉ እና ዘመናዊው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በክብር ተቀብለን አስተናግደናል። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በአፍሪካ ከሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎች አንዱ ሲሆን በውስጡም 1024 ክፍሎች አሉት። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል እንደ አህጉራችን አፍሪካ ሁሉ በህብረ ቀለማት አሸብርቆ እንግዶቹን በክብር አስተናግዶ ሸኝቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ፓንአፍሪካዊ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ፓንአፍሪካዊ
በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ክቡር ሙሳ ፋኪ ማህማትን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀብለን በክብር አስተናግደናል። ክቡር ሊቀ መንበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቅጥር ግቢ እና የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከአየር መንገዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከፍተኛ የአመራር አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታና ስኬት ጋር ቅርብ ቁርኝት ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በምስረታው ወቅት የህብረቱ መስራች የነበሩ ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎችን ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በማጓጓዝ የተጫወተውን ቁልፍ ሚና ዛሬም አፍሪካውያንን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር ይበልጥ በማስተሳሰር አይተኬ ሚናውን በትጋት እንደሚወጣ ይገልፃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲሺየልስ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዋቭል ራማካላዋን፣ ቀዳማዊት እመቤት ክብርት ሊንዳ ራማካላዋን እንዲሁም ልዑካኖቻቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመብረራቸው ክብር ይሰማዋል። ፓን አፍሪካዊው አየር መንገዳችን በተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች ተመራጭ አየር መንገድ ሆኖ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
የኡጋንዳ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ጄሲካ አሉፖ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ ለመካፈል የኢትዮጵያ አየር መንገድን መርጠው ከእኛ ጋር ስለተጓዙ ክብር ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
ፓን አፍሪካዊው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተካፈሉ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቀዳሚ ምርጫ በመሆኑ ክብር ይሰማዋል!
በዛሬው ዕለት የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ጆሴፍ ቦካይ፣ ክቡር ኤቭራስቴ ንዳሺሚዬ የብሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት፣ ክቡር ፎውስቲን ታውዴራ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እንዲሁም ክቡር ሙሃማድ ጃሎው የጋምቢያ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝደንት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ምርጫቸው በማድረግ ወደየሀገሮቻቸው ተመልሰዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠውን የላቀ አገልግሎት በማጠናከር አፍሪካውያንን እርስበርስና ከተቀረው ዓለም ጋር የማገናኘት ተልዕኮውን በትጋት ይወጣል።

የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ትሶኮአኔ ሳሙኤል እንዲሁም የካሜሩን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ጆሴፍ ንጎቴ የኢትዮጵያ አየር መንገድን መርጠው ከእኛ ጋር ስለተጓዙ ክብር ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ