Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ዛሬ የተቀበልነው ቦይንግ 777F እቃ ጫኝ አውሮፕላንም የካርጎ ጭነት አገልግሎት አድማሳችንን ለማሳደግ የራሱ አስተዋፅዖ ከማበርከቱም በተጨማሪ እያደገ የመጣውን የካርጎ አገልግሎት ለማስተናገድ የራሱ አስተዋፅዖ ይኖረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የላቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ ይህ አዲስ የካርጎ አውሮፕላን አየር መንገዱ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን የሚያግዙና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ተቋማት የሚለገሱ ቁሳቁሶችንም ወደ ሀገር ውስጥ ይዞ መጥቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ የመንገደኞች በረራ ከጀመረባቸው መዳረሻዎች መካከል የላይቤሪያዋ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ ትገኝበታለች። የመጀመሪያ በረራውንም የሀገሪቱ ፕሬዝደንት በክብር መቀበላቸው የሚታወስ ነው። የዛሬው የኢትዮጵያ መርሀግብር በዚህ ላይ ያተኮረ ነው፤ እንድትከታተሉን በአክብሮት ጋብዘናችሗል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ @FanaBroadcastingCorporate https://www.youtube.com/watch?v=fCPN7vau6-E
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከ Heart Attack Ethiopia Inc “ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ Heart Attack Ethiopia Inc የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ለልብ እና ስትሮክ ህመም የሚሰጠውን የበጎ ፍቃድ ህክምና አገልግሎት ብሔራዊ አየር መንገዳችን በተለያዩ መንገዶች እገዛ እንዲያደርግ ያስችለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተፈራረመው ይህ ስምምነት የበጎ ፍቃድ የህክምና አገልግሎቱ የበለጠ እንዲጠናከር እና ተደራሽ እንዲሆን የሚያግዝ ሲሆን አየር መንገዳችን ከመደበኛ የስራ እንቅስቃሴው በተጨማሪ የማሕበራዊ አገልግሎት በመስጠት ረገድም ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ባልተቋረጠ ትጋት እና ስኬት እርስዎን ማገልገላችንን እንቀጥላለን! አጓጊ የበረራ አማራጮቻችንን ይቃኙ!
https://www.ethiopianairlines.com/et
https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
 
ምቹ እና አስደሳች የበረራ ግዜ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር!
 
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይና አዲስ አመትን በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በድምቀት አከበረ። ይህን በዓል አስመልክቶ በተካሄደው መርሃግብር ላይ ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቻችን ለሚጓዙ መንገደኞቻችን ልዩ ልዩ ስጦታዎች የተበረከተ ሲሆን ወደ ቻይና መዳረሻዎቻችን በሚያቀኑ በረራዎቻችንም ላይ በድምቀት ይከበራል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ