Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በየትኞቹ የአውሮፐላኖቻችን አይነቶች ተጉዘው ያውቃሉ? #የኢትዮጵያአየርመንገድ
Anonymous Poll
54%
ዲ. ኤች-8 (Q-400)
49%
ቦይንግ -737
39%
ቦይንግ -777
38%
ቦይንግ -787 ድሪም ላይነር
40%
ኤርባስ A350
ከአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ተቋም የተውጣጣ የምሁራን ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ጉብኝት አደረገ።
የምሁራን ቡድኑ “የሲቪል አቪዬሽን ትራንስፎርሜሽን” በተሰኘ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ከአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት እንዲሁም የአየር መንገዱን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። የምሁራን ቡድኑ አጠቃላይ የአቪዬሽን ሴክተርን የማዘመን ስራ ላይ በማተኮር እየሰራ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለሌሎች አየር መንገዶች ከሚሰጠው የአውሮፕላን ጥገና አገልግሎት በተጨማሪ የተለያዩ የአውሮፕላን አካላት የሚያመርት “የኤሮስፔስ ማኒውፋክቸሪንግ” ክፍል በስሩ ይዟል። የዛሬው የኢትዮጵያ መርሀግብር ይህን የአውሮፕላን አካላት የሚያመርተውን የስራ ክፍል እንቅስቃሴ ያስቃኛችሗል፤ አብራችሁን ቆዩ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ደህና መጡ! ዘመናዊ እና ምቹ በሆኑት አውሮፕላኖቻችን በድንቅ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአስደሳች ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ልናገለግልዎ እና ወደ መዳረሻዎ በልዩ እንክብካቤ ከፍ ብለን ልንበር ዝግጁ ነን!
ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ይቁረጡ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ከምርጥ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ጋር!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በስኬት የደመቀ የስራ ሳምንት ይሁንልዎ!!!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ውብ ወደሆኑ በርካታ መዳረሻዎች በምርጥ መስተንግዶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ
ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት አቋርጧል።
በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የምትጓዙ መንገደኞቻችን በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ እንድትሳፈሩ ከታላቅ አክብሮት ጋር እያሳሰብን ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የምንቀጥል መሆኑን እናስታውቃለን። ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርሻለር ከአውሮፕላን ፓይለት ጋር ምን እየተነጋገሩ ያለ ይመስልዎታል? #የኢትዮጵያአየርመንገድ
Anonymous Quiz
15%
ሀ. ለመብረር ተዘጋጅ
80%
ለ. ቁም
2%
ሐ. ወደ ግራ ታጠፍ
1%
መ. ወደ ቀኝ ታጠፍ
2%
ሠ. ወደ ኋላ ተመለስ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መንደር (ET-Village) ሕፃናት እና ታዳጊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝታቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ልቆ እንዲቀጥል ያስቻሉትን የተለያዩ የስራ ክፍሎች እና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሕፃናትና ታዳጊዎቹ በተለያዩ የአየር መንገዱ ባልደረቦች ገለፃና ማብራሪያ የተደረገላቸው ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዙሪያ የተዘጋጀ ጥያቄና መልስ ውድድርና መሰል አስተማሪና አዝናኝ መርሐግብሮች ተሳትፈው የተዘጋጀላቸውን የማስታወሻ ሽልማቶች ተቀብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መኖሪያ መንደር (ET- Village) አየር መንገዱ ለሰራተኞች ምቹ የስራ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ለ5ሺህ ሰራተኞች የምዕራፍ ሁለት የመኖሪያ መንደር ግንባታ እያካሄደ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ